የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ከክልሉ መንግስት ጋር ያደረገው የሰላም ስምምነት የያዛቸው ዋና ዋና ነጥቦች
+++++++++
✍️ የአማራ ህዝብ በማንነቱ እንዳይገደል፣ እንዳይሳደድ እና እንዳይፈናቀል፤
✍️ የተፈናቀሉ ዜጎች እንዲመለሱ ማድረግ፤
✍️ የአማራ ክልል እኩል የመልማትና የመጠቀም መብት እንዲኖረው ማድረግ፤
✍️ በፋኖ ስም በፌደራልም ሆነ በክልል ማረሚያ ቤት ያሉ አባላት እንዲፈቱ፤
✍️ የቆሰሉ ሰዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ እንዲሰራ፤
✍️ አቅምና እውቀት ያላቸው አባላት እንዲሁም የወታደር ቁመና ያላቸው የጸጥታ ሃይሉን እንዲሁም ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ ማስቻል፤
✍️ የመንግስት ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱና የቀረባቸው ጥቅማ ጥቅም እንዲከፈላቸው፤
✍️ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚሉ ጉዳዮች ላይ ከመግባባት ተደርሷል፤
ምንጭ:- ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የውጪ ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ

❤25👏4
20ኛው የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን
"ዲሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት"
የ20ኛው የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ታዳሚዎች - ሆሳዕና

❤1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
'ብሄራዊ ጥቅም' የምንፈልገው ፣ የምንሞትለትና የምንታገልለት ጉዳይ ነው- ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ
👉 https://youtu.be/ayTJYUFkmYM?si=YO-2yPTpz8ldvffQ

❤2
ጅማ ከተማ 21ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንድታዘጋጅ ተመረጠች
+++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ጅማ ከተማ 21ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንድታዘጋጅ ተመረጠች።
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል “ዴሞክራሲያዊ መግባባት፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
በዚሁ መርሃግብር ላይ ጅማ ከተማ በቀጣይ ዓመት 21ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።
በልጅዓለም ፍቅሬ
+++++++++++++++++
#Gazetteplus #ጋዜጣፕላስ #ጅማ

❤5
“ማንኛውም ትንኮሳና ፈተና ኢትዮጵያን ከብልጽግና ጉዞ ማስቆም አይችልም”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ ⵏ ማንኛውም ትንኮሳና ፈተና ኢትዮጵያን ከብልጽግና ጉዞ ማቆም አይችልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ማንኛውም ፈተና፣ ትንኮሳና ክፉ ሃሳብ ኢትዮጵያን ከብልጽግና ማቆም አይችልም።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ጠላቶች አንድ በአንድ እናራግፋለን ብለዋል።
ከአባቶቻችን በደም የወረስነውን ነጻነት በብልጽግና ማጽናት ከዚህ ትውልድ እንደሚጠበቅ ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ በሁሉም መመዘኛ ከጨለማ ወደ ንጋት እየተሸጋገረች መሆኑን ገልጸዋል።
ብልጽግናን ማሳካት ፈታኝ መሆኑን በመግለጽ፤ የወረስነውን ነጻነት ብቻ ሳይሆን የተሸከምነውን የትውልድ አደራ ማሰብ አለብን ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ችግሯን ብቻ ሳይሆን አቅሟን ማየት አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ትውልድ ችግሯን ብቻ ሳይሆን አቅሟን ፍልፍሎ የማየትና የማውጣት ብቃት አለው ብለዋል።
ከኢትዮጵያ መቀበል ብቻ ሳይሆን መስጠትም እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ የጸናች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የአገርን መሻትና የባዳን ክፋት መለየት እንደሚያስፈልግ በመግለጽ፤ ኢትዮጵያዊያን ለባዳ ፍላጎት መሳሪያ መሆን እንደሌለባቸው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያዊያን ቀልብ ገዝተን ሰላማችንን እናጽና ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የአገርን ክብርና የዜጎችን ጥቅም እናስከብር ብለዋል።
ኢትዮጵያ በብዙ ተስፋ የተመላች አገር መሆኑኗን ጠቅሰው፤ አስደናቂ ጅማሮና ውጤት እያሳየች መሆኑንም ገልጸዋል።
በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ብሔርብሔረሰቦች #በዓል #ሆሳዕና #ዐቢይ_አሕመድ
#ጠቅላይ_ሚኒስትር

👍8❤5👏1
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች
++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | በጄኔቫ ስዊዘርላንድ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ድርጅታዊ ስብሰባ ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የቢሮ አባል በመሆን ተመርጣለች።
በዚህም ኢትዮጵያ አፍሪካን በመወከል ለአንድ ዓመት ያህል በመሪነት ሚና እንደምታገለግል ተመላክቷል።
የኢትዮጵያን መመረጥ ተከትሎ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋብ ክበበው ዳካ እና በስዊዘርላንድ የሚገኙ ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
በአማን ረሺድ

❤4👎1👏1
የኢትዮጵያን የአየር ክልል ከማንኛውም ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል አቅም ተገንብቷል
+++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያን የአየር ክልል ከማንኛውም ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል አቅም መገንባቱን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጀነራል መሰረት ጌታቸው ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የአየር ኃይሉ ዋነኛ ተልዕኮ የኢትዮጵያን የአየር ክልል በማንኛው ሰዓት ከማንኛውም ሁኔታ መጠበቅና መከላከል ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት አገርና መንግሥት የሰጠንን ተልዕኮና ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ታጥቀናል ያሉት ብርጋዴል ጀነራል መሰረት፣ አየር ኃይሉ ማንኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ሁኔታ መወጣት የሚችል፣ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ መፍጠር፤ መታጠቅና መጠቀም የሚችል ነው ብለዋል፡፡
ቴክኖሎጂን መሸከም፣ ማፍለቅና መጠቀም የሚችል የሰው ኃይል ማፍራት ላይ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ ቴክኖሎጂዎችን የራስ ማድረግና በራስ አቅም መጠቀም መቻሉንም ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያን አየር ክልል የማስጠበቅ ጉዳይ የ24 ሰዓት ሥራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
የውጊያ መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋትና የመገንባት ሥራ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ ከለውጡ ወዲህ አየር ኃይል የውጊያ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን አስረድተዋል፡፡
አየር ኃይሉ ጥራት ያለው የሰው ኃይል በማፍራት ግዳጅን የመወጣት አቅሙን የተሻለ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በ2030 ከአፍሪካ ምርጥ አየር ኃይሎች አንዱ ለማድረግ መታቀዱንም ገልጸዋል፡፡
በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazetteplus #አየር_ኃይል #ውጊያ #ኢትዮጵያ
#አየር_ክልል #ብርጋዴል_ጀነራል #አዛዥ