Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስአንጀለስ ከተማ የ’ኤች አር 6600’ እና የ'ኤስ 3199' ረቂቅ ሕጎች የሚቃወም ሰልፍ ተካሄደ
****
(ኢ ፕ ድ)
የ’ኤች አር 6600’ እና የ'ኤስ 3199' ረቂቅ ሕጎች የሚቃወም ሰልፍ በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ ተካሄደ።

ሰልፉ የተካሄደው የ'ኤችአር 6600' ረቂቅ ሕግን በተባባሪነት ያዘጋጁት የካሊፎርኒያ የኮንግረስ አባል ብራድ ሼርማን ቢሮ ፊት ለፊት ነው።

በሰልፋ ላይ ኢትዮጵያውያን፣ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ’ኤች አር 6600’ እና 'ኤስ 3199 ረቂቅ ሕጎች' እንደሚቃወሙትና ሕጎቹ ኢትዮጵያን እንዲሁም በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚጎዳውን ሕግ ውድቅ እንዲደረግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

"ማዕቀብ ይገድላል ይጎዳል "፣"ረቂቅ ሕጎቹ የምስራቅ አፍሪካን ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸዉ" እና ሕጎቹ በየትኛውም አይነት ሁኔታ የኢትዮጵያንና አሜሪካን ጥቅምና ፍላጎት አያስጠብቁም" የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ተደምጠዋል።

በተጨማሪም "ብራድ ሼርማን በኮንግረስ ምርጫው ድምጽ አንሰጥዎትም" የሚል መልዕክት መተላለፋን ኢዜአ ከሰልፋ አስተባባሪዎች ያገኘው መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል።

‘ኤች አር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ትናንት በዋሺንግተን ዲሲ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት መካሄዱ የሚታወስ ነው።

በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ሕጎቹ በሕግ አውጪው አካል ድምጽ ተሰጥቶባቸው እንዳይጸድቁ ለማድረግ ሴናተሮችና የኮንግረስ አባላትን በማናገር፣ደብዳቤ በመጻፍ፣ፊርማ በማሰባሰብና በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ በማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የሞጁላር መረጃ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያሰችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮ ቴሌኮም ለአማራ ባንክ ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማዕከል ገንብቶ አገልግሎት ላይ ማዋሉ ይታወቃል። ከፍተኛ አቅም ያለውን የመረጃ ማዕከል አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል ስምምነት ከአማራ ባንክ ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱ የባንኩን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርዓት ውስጥ አግልግሎት መስጠት እንደሚያስችል የኢቲዮ ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።
ስምምነቱ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን በጠበቀ የመረጃ ማዕከል አማካኝነት አስተማማኝ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለመስጠት እንደሚያስችለውም ተናግረዋል።
በዳግማዊት ግርማ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ከ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አሰታወቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ውጭ ከላካቸው ምርቶች ከ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ 11 ሸዶችን ይዞ ስራ ከጀመረ አንድ ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን አሁን ላይ አምስት ኩባንያዎች በአቮካዶ ዘይት፣ በማር፣ ወተትና ቡና ምርቶች ላይ ተሰማርተው ለውጭ ገበያ በማቅረብ ገቢ በማስገኘት ላይ ናቸው።
በፓርኩ ዙሪያ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መምሩ ሞኬ፤ ፓርኩ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ከ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘቱን ገልጸዋል።
ገቢው በፓርኩ በሚሰሩ ሁለት የአቮካዶ ዘይት አምራች ኩባንያዎች ከተላኩ ምርቶች የተገኘ መሆኑንም አብራርተዋል።
ኢንዱስትሪዎችን ከገበሬዎች እና ህብረት ስራ ማህበራት ጋር በቀጥታ በማስተሳሰር የጥሬ እቃ ግብዓትና የምርት የግብይት ሰንሰለት መፈጠር መቻሉንና በፓርኩ ውስጥ ከሚገኙ ሁለት ፋብሪካዎች ጋር በተፈጠረ የገበያ ትስስር ከ135 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይ ፓርኩ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት ትኩረት እንደሚያደርግ ገልጸው፤ እሴት ተጨምሮባቸው ወደ አገር የሚገቡ የቡና እና የወተት ምርቶችን ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተሟላ መሰረተ ልማት ያላቸውና አንድ መቶ ሃምሳ ኩባንያዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሼዶች ተዘጋጅተው ባለሃብቶችን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።
ለፋብሪካው ግብአት የሚሆኑ የግብርና ምርቶች በስፋት ስለሚመረቱ፤ በርካታ የሰው ሃይል እና አስተማማኝ ሰላም ያለበት አካባቢ በመሆኑ ባለሃብቶች በፓርኩ ተጨማሪ ስራዎችን እንዲጀምሩም ጥሪ አቅርበዋል።
በሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ስር የሚተዳደረው የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመርቆ ወደ ስራ የገባው መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል።
በአፋር በደረሰ የእሳት አደጋ መኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች ከበርካታ ሀብት ጋር ወድመዋል
****************
(ኢ ፕ ድ)
ትናንት ከሰአት 11 ሰአት ገደማ በሰሙሮቢ ወረዳ ኮማሚ ቀበሌ በተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በርካታ ንብረት በመውደሙ ለህብረተሰቡ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀሰን ሀንድዬ ጥሪ አቀረቡ።
ለህብረተሰቡ አልባሳት፣ ምግብ ነክ ነገሮች፣ መጠለያና የመጠጥ ውሃ በአፋጣኝ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።
የእሳት ቃጠሎው በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። 80 የንግድ ቤቶች ውስጥ የነበሩ 500 ሺህ ብር በላይ ሸቀጣ ሸቀጥና ጥሬ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን በ80 መኖሪያ ቤቶችም የነበሩ እቃዎችና ጥሬ ገንዘብ እያንዳንዳቸው 200 ሺህ ብር ገደማ መውደሙን ተናግረዋል።
በንብረት ላይ ማለትም የቤቶችን ግምት ሳያካትት በቤት ውስጥ የነበረ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ እቃዎችና ጥሬ ብር የደረሰው አደጋ 56 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ እንደሆነ አቶ ሀሰን ገልጸዋል።
በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ተናግረዋል።
በአቅራቢያቸው በሚገኙት ሸዋሮቢትም ሆነ ደብረብረሃን ከተሞች አንድም የእሳት አደጋ መከላከያ ባለመኖሩ ምክንያት ይህን ውድመት መቀነስ እንዳልተቻለም ገልጸዋል።
የአደጋው መነሻው በቀዳሚነት በቤንዚን ነው ተብሎ ታስቦ የነበረው ትክክል አልነበረም ያሉት አስተዳዳሪው በተደረገው ማጣራት የኤሌክትሪክ ንክኪ ተፈጥሮ ወደ ቤንዚን ቤት ማምራቱን አያይዘው ተናግረዋል።
በመጨረሻም ወረዳ አስተዳዳሪው በአሁኑ ወቅት የአደጋው ሰለባ የሆነው ህብረተሰባችን ከፍተኛ የሆነ ችግር ውስጥ በመሆኑ በአፋጣኝ ልንደርስለት ይገባል በማለት የድጋፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ለመተከል ዞን ተፈናቃዮች 5ኛው ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በመተከል ዞን በተለያዩ መጠለያ ጣቢዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 5ኛው ዙር ሰብዓዊ ድጋፍ በመቅረብ ላይ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
በዞኑ በተፈጠረው አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚቀርበው ሰዓብዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ኮሚሽኑ ከአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከ42ሺ 3 መቶ ኩንታል በላይ የሰብዓዊ ድጋፍ በመጠየቅ በአሁኑ ሰዓት ለተፈናቃዮች እየቀረበ መሆኑን በኮሚሽኑ የምላሽ ፍላጎትና እርዳታ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዘውዱ ተሾመ አስታውቀዋል።
እስካሁን በዞኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሚገኙ 282 ሺህ የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎች በየወረዳ ባለው መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በ5ኛው ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ በዞኑ ስር በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎች በመጓጓዝ ላይ መሆኑን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።