Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአፋር በደረሰ የእሳት አደጋ መኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች ከበርካታ ሀብት ጋር ወድመዋል
****************
(ኢ ፕ ድ)
ትናንት ከሰአት 11 ሰአት ገደማ በሰሙሮቢ ወረዳ ኮማሚ ቀበሌ በተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በርካታ ንብረት በመውደሙ ለህብረተሰቡ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀሰን ሀንድዬ ጥሪ አቀረቡ።
ለህብረተሰቡ አልባሳት፣ ምግብ ነክ ነገሮች፣ መጠለያና የመጠጥ ውሃ በአፋጣኝ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።
የእሳት ቃጠሎው በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። 80 የንግድ ቤቶች ውስጥ የነበሩ 500 ሺህ ብር በላይ ሸቀጣ ሸቀጥና ጥሬ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን በ80 መኖሪያ ቤቶችም የነበሩ እቃዎችና ጥሬ ገንዘብ እያንዳንዳቸው 200 ሺህ ብር ገደማ መውደሙን ተናግረዋል።
በንብረት ላይ ማለትም የቤቶችን ግምት ሳያካትት በቤት ውስጥ የነበረ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ እቃዎችና ጥሬ ብር የደረሰው አደጋ 56 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ እንደሆነ አቶ ሀሰን ገልጸዋል።
በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ተናግረዋል።
በአቅራቢያቸው በሚገኙት ሸዋሮቢትም ሆነ ደብረብረሃን ከተሞች አንድም የእሳት አደጋ መከላከያ ባለመኖሩ ምክንያት ይህን ውድመት መቀነስ እንዳልተቻለም ገልጸዋል።
የአደጋው መነሻው በቀዳሚነት በቤንዚን ነው ተብሎ ታስቦ የነበረው ትክክል አልነበረም ያሉት አስተዳዳሪው በተደረገው ማጣራት የኤሌክትሪክ ንክኪ ተፈጥሮ ወደ ቤንዚን ቤት ማምራቱን አያይዘው ተናግረዋል።
በመጨረሻም ወረዳ አስተዳዳሪው በአሁኑ ወቅት የአደጋው ሰለባ የሆነው ህብረተሰባችን ከፍተኛ የሆነ ችግር ውስጥ በመሆኑ በአፋጣኝ ልንደርስለት ይገባል በማለት የድጋፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ለመተከል ዞን ተፈናቃዮች 5ኛው ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በመተከል ዞን በተለያዩ መጠለያ ጣቢዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 5ኛው ዙር ሰብዓዊ ድጋፍ በመቅረብ ላይ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
በዞኑ በተፈጠረው አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚቀርበው ሰዓብዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ኮሚሽኑ ከአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከ42ሺ 3 መቶ ኩንታል በላይ የሰብዓዊ ድጋፍ በመጠየቅ በአሁኑ ሰዓት ለተፈናቃዮች እየቀረበ መሆኑን በኮሚሽኑ የምላሽ ፍላጎትና እርዳታ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዘውዱ ተሾመ አስታውቀዋል።
እስካሁን በዞኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሚገኙ 282 ሺህ የሚደርሱ የህብረተሰብ ክፍሎች በየወረዳ ባለው መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በ5ኛው ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ በዞኑ ስር በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎች በመጓጓዝ ላይ መሆኑን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አትክልትና ፍራፍሬን ለህብረተሰቡ በቀጥታ ለማቅረብ እየሰራን ነው -አርሶ አደሮች
*******************
(ኢ ፕ ድ)
አትክልትና ፍራፍሬን ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በቀጥታ በማቅረብ ገበያን ለማረጋጋት እየሰሩ መሆኑን በከተማ ግብርና የተሰማሩ የአዳማ ከተማ አርሶ አደሮች ገለጹ።
አርሶ አደር ነገዎ ወርጂ እንደገለጹት በ12 ሄክታር መሬት ላይ ቃሪያ፣ ሽንኩርትና ቲማቲም እያለሙ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን ላይ ምርቱ እየደረሰ በመሆኑ ደላላ ጣልቃ ሳይገባ ለሸማቹ ህብረተሰብ በቀጥታ ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በመጭዎቹ 10 ቀናት ውስጥ የቲማትምና የቃሪያ ምርት ለገበያ ማቅረብ እንደሚጀምሩ አመላክተዋል ።
ምርታቸውን ለምግብነት ከመጠቀም አልፈው ለህብረተሰቡ በቀጥታ በማቅረብ የዋጋ ንረቱን ለማቃለል የመሸጫ ቦታ ከመስተዳድሩ እየጠየቁ መሆኑን ገልጸዋል።
“ወደ ከተማ ከተካለልን ወዲህ ብዙ እገዛ ተደርጎልን በከተማ ግብርና ተሰማርተን የጓሮ አትክልት እያለማን ነው” ያሉት ደግሞ የአዳማ ከተማ መልካ ሂዳ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ለገሰ ጉደታ ናቸው።
በአሁኑ ወቅት ለራሳቸው ለምግብነትም ሆነ ለከተማው ህብረተሰብ ለማቅረብ ቃሪያና ቲማቲም እንዲሁም ፓፓያ እያለሙ መሆኑን ተናግረዋል።
ቀደም ብሎ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ያመርቱ የነበረውን አሁን በዓመት ሶስት ጊዜ እያመረቱ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ምርታቸውን በቀጥታ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ገበያን ለማረጋጋት እየተጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አርሶ አደሩ ከአትክልት በተጨማሪ በበጋ ስንዴ ልማት ተሰማርተው ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
የአዳማ ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ሂርጶ በበኩላቸው “በአሁኑ ወቅት በመንግስት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በከተማዋ ከ627 ሄክታር በላይ መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ስንዴን በመስኖ እያለማን ነው” ብለዋል።
በተጨማሪም 10 ትምህርት ቤቶች ላይ በ6 ሄክታር መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ እየለማ መሆኑንም አቶ ጌታቸው መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
“ምግባችን ከጓሮአችን” በሚል መሪ ሃሳብ አብዛኛው የከተማው ነዋሪ ቶሎ የሚደርስ አትክትልና ፍራፍሬ እንዲያለማ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከላት በዘርፉ ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንዳለባቸው ተጠቆመ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በሆቴልና ቱሪዝም ሙያ ስልጠና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያበረታታ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጀርመን ልማት ትብብር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መድረክ ሚኒስትር ዴኤታ በከር ሻሌ (ዶ/ር) በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ትብብርን አጠናክሮ ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ምቹ ሥራ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡
የኢንዱስትሪው ባለድርሻ አካላት ሥርዓተ ስልጠናውን በጋራ በመቅረፅ ፣ በማሰልጠንና በመመዘን ጭምር ከሆቴልና ቱሪዝም ኢንስቲትዩት ማሰልጠኛ ማዕከላት ጋር ትኩረት ሰጥተው በጋራ መሥራት አለባቸው።
በቀጣይም በጋራ በመሥራት የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን ማሳደግ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
የጀርመን መንግስት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እያደረገ ካለው ድጋፍ ባሻገር ይህንን ውይይት በማዘጋጀቱ አመስግነዋል፡፡
የጀርመን ትብብር ልማትን ወክለው ንግግር ያደረጉት ቤንጃሚን ሀከር ኢትዮጵያ በቱሪዝም ብዙ ሀብት ያላት በመሆኑ ዘርፉን በብቁ ባለሞያዎች በማሳደግ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል የጀርመን መንግስት ድጋፉን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ቱሪዝም ኢንስቲትዩት፣ ኃይሌ ሪዞርት፣ሃያት ሪጀንሲ፣ ኩሪፍቱ ሪዞርት፣ ኢትዮጵያ ሼፍ ማህበር፣ ኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ለብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል አባላት የማዕረግ ማልበስና የእውቅና መስጠት መርሃ-ግብር ተካሄደ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የኮማንዶ ሰልጣኞች በተደረገው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ለማሰልጠኛ ማዕከሉ አባላት የማዕረግ ማልበስና የእውቅና መስጠት መርሃ-ግብር ተከናውኗል፡፡
በስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቦጃ አጋ የሃገርን ደህንነት ከውስጥና ከውጭ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ትንኮሳዎችን የሚመክት ዘመናዊ የሆነ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠንና መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።
ሰልጣኝ ኮማንዶዎች በማሰልጠኛ ማዕከሉ የሚሰጡ ስልጠኛዎችን በጀግንነት፣ በታታሪነት መወጣት አለባችው ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቦጃ አጋ የማዕረግ እድገትና እውቅና ላገኙ ለማሠልጠኛ ማዕከሉ አባላት በቀጣይ የሚሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በቆራጥነት መወጣት አለባቸው። ለሰልጣኞችም አርያዓያ ሆነው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የቀድሞ አየር ወለድ ሰራዊት አባል መሰረታዊ ወታደር ፈቀደ ሃብተወልድ እኔ እያለሁ ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ የሀገርን ጥሪ ተቀብሎ በማሠልጠኛ ማዕከሉ የአሰልጣኝነት ሚናውን ተወጥቷል። ላበረከተው አስተዋፅኦ የተሰጠው ሽልማት ለቀጣይ ስራ መነሳሳትን እንደፈጠረለት መግለጹን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️