Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የእሥራኤል የጤና ቡድን በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ጉብኝቱን ማካሄድ ጀመረ
*************
(ኢ ፕ ድ)
የእሥራኤልን ሦስት የፓርላማ አባላት ያካተተው የጤና ባለሙያዎች ቡድን፤ ሀገሪቱ ውስጥ በተከሰተው የጦርነት የተጎዱ የጤና ተቋማት የሚያካሂደውን ይፋዊ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ጀመረ፡፡
በኢትዮጵያ በሚኖረው የሦስት ቀናት ቆይታው፤ ለጦርነት ተጋላጭ ሆነው በቆዩት ክልሎች ውስጥ የሚገኙትን የተጎዱ የጤና ተቋማት እንደሚጎብኙ የቡድኑ መሪ ሚስተር ጋዲ ባርከን አስታውቀዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ (ዶ/ር)፤ የልዑካን ቡድኑን ዛሬ ጠዋት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገኝተው አቀባበል አድርገዋል።
የእሥራኤል የፓርላማ አባል እና የቀድሞው የሀገሪቱ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ምክትል ሚኒስትር የነበሩት ሚስተር ጋዲ ባርከን በዚሁ ወቅት፤ የልዑካን ቡድኑ የአሁኑ ጉብኝት፣ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቶ ድጋፍ ለማድረግ እና እሥራኤል በችግር ጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ጎን መሆኗን ለማሳየት የታለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት በጦርነቱ የተጎዳው ሕዝብ ሕክምና እንዲያገኝ የሚረዳ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ በበኩላቸው፤ የልዑካን ቡድኑ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ጎብኝቶ ድጋፍ ለማድረግ በመምጣቱ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ሰብሳቢው አያይዘውም፤ ቡድኑ በሦስት ቀናት ቆይታው ከጉብኝት በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት ለወደሙ የጤና ተቋማት ድጋፍ ለማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ለመወያየት መዘጋጀቱንም በአድናቆት ተመልክተዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች የምክር ቤት አባል አቶ ባያብል ሙላትም በበኩላቸው፤ በእሥራኤል የፓርላማ አባል በተበከበሩ ሚስተር ጋዲ ባርከን አነሳሽነት የልዑካን ቡድኑ መምጣቱ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ተግባር መሆኑን አመላክተዋል፡፡
አቶ ባያብል ሌሎች የጤና ባለሙያዎችም ከዚህ በፊት መምጣታቸው እና አሁንም ተመሳሳይ ጉብኝት መደረጉ ሀገራችን ከእሥራኤል ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነት እንደሚያመላክት አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
"ዓለም አቀፍ ተቋማትና የረድኤት ድርጅቶች በአፋርና አማራ ክልል ያለውን ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ዘንግተውታል"
-አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን
*************************
(ኢ ፕ ድ)
ዓለም አቀፍ ተቋማትና የረድኤት ድርጅቶች በአፋርና በአማራ ክልል ያለውን ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ሊገነዘቡና አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ስትል አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን ተናገረች።
ሂዩማን ራይትስዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ተከስቷል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያወጡት የጋራ ሪፖርትም ፖለቲካዊ ይዘት አለው ብላለች።
አን ጋሪሰን በኢትዮጵያ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ያደረገችውን ጉብኝት አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር በነበራት ቆይታ ጦርነቱ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ማስከተሉን ገልጻለች።
አሸባሪው ሕወሓት በሰው ህይወት ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ማውደሙንና ይህም በርካታ ሰዎች በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ እንዲቆዮ አድርጓቸዋል ብላለች።
ይህንንም ተከትሎ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በሕዝቡ ላይ የፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እጅግ አሰቃቂ መሆኑን ተዘዋውራ በተመለከተቻቸው ሥፍራዎች ባደረገችው ምልከታ ማረጋገጧን ጠቁማለች።
ያም ሆኖ ዓለም አቀፍ ተቋማትና የረድኤት ድርጅቶች በአማራና በአፋር ክልል ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ ዘንግተውታል፤ የሚያደርጉትም ድጋፍ ከሚጠበቀው በታችና ሁሉን አቀፍ አለመሆኑን አመልክታ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በአፋርና በአማራ ክልል መኖሩን በማወቅ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ትናግራለች።
በሌላ በኩል ሂዩማን ራይትስ ዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ተከስቷል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያወጡት የጋራ ሪፖርትም ፖለቲካዊ ይዘት አለው ብላለች።
ሪፖርቱ የወጣው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ላይ ያጠናውን ሪፖርት ከመለቀቁ ከቀናት በፊት መሆኑን አንስታ፤ ይህም አንድ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በማለም የተደረገ መሆኑን ገልጻለች።
ከዚህም በላይ ሪፖርቱ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ማዕቀብ እንዲጥሉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ማዕቀብ ካልተጣለ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ሊባባስ ይችላል የሚል እምነት በሰዎች ውስጥ እንዲያድር ያለመ መሆኑንም ነው ያነሳችው።
ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል በአሜሪካን መንግሥት ውስጥ ያሉ የአንዳንድ ግለሰቦች ፍላጎትን ለማስፈጸም እየሰሩ መሆኑንም ጠቁማለች።
በተለይም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለ ትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ብቻ በተደጋጋሚ የሚያደርጉት ውግንና የፖለቲካ አቋማቸውን አመላካች ነው፣ይህም ገለልተኛ በመሆን ድርጅቱን ለመምራት ከገቡት ቃል ጋር የሚጻረር ነው ብላለች።
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስና ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃዎች በማሰራጨት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን እውነታ እንዲረዳ የበኩሏን እንደምትሰራ አን ጋሪሰን ተናግራለች።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በሀረሪ ከመጪው አርብ ጀምሮ በሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት ከ56 ሺህ በላይ ህፃናትን ለመከተብ ታቅዷል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በሀረሪ ከመጪው አርብ ጀምሮ በሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት ከ56 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑ ህፃናትን ለመከተብ ማቀዱን የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።
በክልሉ ከሚያዝያ 7 እስከ ሚያዝያ 10 በሚካሄደው የፖልዮ ክትባት በሁሉም ወረዳዎች ለሚገኙ ጤና አስተባባሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የወረዳ ጤና ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማጎልበቻ መድረክ እየተሰጠ ይገኛል።
በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥርና ክትትል ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ቱፋ እንዳሉት ክትባቱ ከዚህ ቀደም ለወሰዱም ሆነ ላልወሰዱ እድሜያቸው ከአምሰት አመትና ከዛ በታች ለሆኑ ህፃናት ይሰጣል። በክልሉ 56 ሺህ 394 ህፃናትን ለመከተብ መታቀዱን ገልፀዋል።
ክትባቱም ቤት ለቤትና በትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ የጠቆሙት አቶ አሰፋ ለዚህም ዝግጅት አየተደረገ ነው ብለዋል።
በመሆኑም ለክትባት ዘመቻው በተለይም የትምህርት ቤት ማህበረሰብ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አመራሮችና ባለሙያዎች የክትባት ዘመቻው ውጤታማ እንዲሆን ከማስቻል አንፃር ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የፖሊዮ በሽታን በሚመለከት እንዲሁም ስለሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት የተመለከቱ ፅሁፍች ቀርበው ውይይት መደረጉን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በላሊይበላ ገዳም ለሚተዳደሩ አገልጋዮችና ለአከባቢው ነዋሪዎች ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና የከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ በቤተክህነት በሰጡት መግለጫ፣ በሮሃ ቅዱስ ላሊይበላ ገዳም የሚተዳደሩ አገልጋዮችና የአከባቢው ነዋሪዎች ችግር ላይ መውደቃቸውን አሰታወቁ።
በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
ከባለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝና በጦርነቱ ምክንያት ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ባለመኖሩ ምክንያት ለችግር በመጋለጣቸው የቱሪዝም ገቢው እስኪጀመር ድረስ ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
ካህናት፣ የአብነት ተማሪዎች፣ አረጋውያንና መነኮሳት እንዲሁም ወላጅ አልበ ህፃናትን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በገዳሙ የቱሪዝም ገቢ የሚተዳደሩ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የአከባቢው ህብረተሰብና የገዳሙ አገልጋዮች ከሐምሌ ጀምሮ በሰሜን ወሎ እና በዋግኽምራ በደረሰው ውድመትና ከቱሪስት ገቢ የሚገኘው በመቋረጡ ተደራራቢ ችግር ውስጥ መሆኑንም ገልፀዋል።
በከባቢው በጦርነቱ የወደሙ የውሃ የመብራት የህክምና እና የሌሎች መሠረተ ልማቶች የቅርሱ ጠባቂዎች መሰደድ ምክንያት እየሆነ በመሆኑ የማይዳሰስ ቅርስ የሆነውን መንፈሳዊ አገልግሎት በማየት ይመጡ የነበሩ ቱሪስቶች አየቀሩ መሆኑ ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል።
ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም ቅርስ ሆኖ ከተመዘገበ ጊዜ ጀምሮ አገልግሎት አየሰጠ የሚገኘው ገዳም ነው።
በኃይሉ አበራ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
አምባሳደሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ጎበኙ
****
(ኢ ፕ ድ)
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው አምባሳደሮች ቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አሰጎበኘ።

በአለም ሀገራት የተሾሙ አምባሳደሮች በኢትዮጵያ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮችን ተመልክተው በሚሄዱባቸው የአለም ሀገራት በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ እንጂችሉ የተደረገ ጉብኝ ነው ተብሏል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ አምባሳደሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለአለም ለማስተዋወቅ መስራት አለባቸው ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎችን፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችንና የወደፊት ስራዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ቀርቧል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለአለም ለማስተዋወቅ እንደሚረዳቸው አምባሳደሮቹ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ