Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በሀረሪ ከመጪው አርብ ጀምሮ በሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት ከ56 ሺህ በላይ ህፃናትን ለመከተብ ታቅዷል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በሀረሪ ከመጪው አርብ ጀምሮ በሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት ከ56 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑ ህፃናትን ለመከተብ ማቀዱን የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።
በክልሉ ከሚያዝያ 7 እስከ ሚያዝያ 10 በሚካሄደው የፖልዮ ክትባት በሁሉም ወረዳዎች ለሚገኙ ጤና አስተባባሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የወረዳ ጤና ሀላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማጎልበቻ መድረክ እየተሰጠ ይገኛል።
በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥርና ክትትል ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ቱፋ እንዳሉት ክትባቱ ከዚህ ቀደም ለወሰዱም ሆነ ላልወሰዱ እድሜያቸው ከአምሰት አመትና ከዛ በታች ለሆኑ ህፃናት ይሰጣል። በክልሉ 56 ሺህ 394 ህፃናትን ለመከተብ መታቀዱን ገልፀዋል።
ክትባቱም ቤት ለቤትና በትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ የጠቆሙት አቶ አሰፋ ለዚህም ዝግጅት አየተደረገ ነው ብለዋል።
በመሆኑም ለክትባት ዘመቻው በተለይም የትምህርት ቤት ማህበረሰብ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አመራሮችና ባለሙያዎች የክትባት ዘመቻው ውጤታማ እንዲሆን ከማስቻል አንፃር ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የፖሊዮ በሽታን በሚመለከት እንዲሁም ስለሚሰጠው የፖሊዮ ክትባት የተመለከቱ ፅሁፍች ቀርበው ውይይት መደረጉን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በላሊይበላ ገዳም ለሚተዳደሩ አገልጋዮችና ለአከባቢው ነዋሪዎች ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠየቀ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና የከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ በቤተክህነት በሰጡት መግለጫ፣ በሮሃ ቅዱስ ላሊይበላ ገዳም የሚተዳደሩ አገልጋዮችና የአከባቢው ነዋሪዎች ችግር ላይ መውደቃቸውን አሰታወቁ።
በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
ከባለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝና በጦርነቱ ምክንያት ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ባለመኖሩ ምክንያት ለችግር በመጋለጣቸው የቱሪዝም ገቢው እስኪጀመር ድረስ ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
ካህናት፣ የአብነት ተማሪዎች፣ አረጋውያንና መነኮሳት እንዲሁም ወላጅ አልበ ህፃናትን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በገዳሙ የቱሪዝም ገቢ የሚተዳደሩ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የአከባቢው ህብረተሰብና የገዳሙ አገልጋዮች ከሐምሌ ጀምሮ በሰሜን ወሎ እና በዋግኽምራ በደረሰው ውድመትና ከቱሪስት ገቢ የሚገኘው በመቋረጡ ተደራራቢ ችግር ውስጥ መሆኑንም ገልፀዋል።
በከባቢው በጦርነቱ የወደሙ የውሃ የመብራት የህክምና እና የሌሎች መሠረተ ልማቶች የቅርሱ ጠባቂዎች መሰደድ ምክንያት እየሆነ በመሆኑ የማይዳሰስ ቅርስ የሆነውን መንፈሳዊ አገልግሎት በማየት ይመጡ የነበሩ ቱሪስቶች አየቀሩ መሆኑ ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል።
ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም ቅርስ ሆኖ ከተመዘገበ ጊዜ ጀምሮ አገልግሎት አየሰጠ የሚገኘው ገዳም ነው።
በኃይሉ አበራ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
አምባሳደሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ጎበኙ
****
(ኢ ፕ ድ)
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በቅርቡ ሹመት ለተሰጣቸው አምባሳደሮች ቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አሰጎበኘ።

በአለም ሀገራት የተሾሙ አምባሳደሮች በኢትዮጵያ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮችን ተመልክተው በሚሄዱባቸው የአለም ሀገራት በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ እንጂችሉ የተደረገ ጉብኝ ነው ተብሏል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ አምባሳደሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለአለም ለማስተዋወቅ መስራት አለባቸው ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎችን፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችንና የወደፊት ስራዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ቀርቧል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለአለም ለማስተዋወቅ እንደሚረዳቸው አምባሳደሮቹ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የኤችአር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎችን በመቃወም በቤልጂየም የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ
*************
(ኢ ፕ ድ)

የኤችአር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ ህጎች በመቃወም በቤልጂየም የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ።

ሰልፈኞቹ የአሜሪካ መንግስትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከኢትዮጵያ ጎን እንሲሰለፉም ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያውያኑ የአሸባሪው የህወሃት ቡድን በአፋር እና የአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል በመገንዘብ የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት አባላት ያረቀቋቸውን ህጎች እንዲሰርዙም የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ ከአሜሪካ መንግስት በተጨማሪም ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ በመገንዘብ ከኢትዮጵያውያን ጎን እንዲሰለፉም ጥሪ አቅርበዋል።

በቤልጂየም የተካሄደው ሰልፍ አስተባባሪ አቶ ኤፍሬም ምትኩ እንዲህ ያሉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተለያዩ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት የኢፍጣር ዝግጅት አደረጉ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለተለያዩ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት የኢፍጣር ዝግጅት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ማምሻውን ለተለያዩ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት የኢፍጣር ዝግጅት አድርገዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ