Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"ከ94 ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት መድረክ ቅዳሜ ይካሄዳል" - የደቡብ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ክልል 94 ሺህ 200 ወጣቶች የሚሳተፉበት ክልል አቀፍ የውይይት መድረክ ሚያዚያ 8/2014 እንደሚካሄድ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
የሊግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰንበቶ አባባ፣ ወጣቱ በብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን በአግባቡ ተረድቶ ወደቀጣዩ ተግባር በእውቀት እንዲገባ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል፡፡
መድረኮቹ ለወጣቱ የተሻለ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችሉ፣ መካተትና መሻሻል አለባቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች በነጻነት የሚያነሱባቸውና የወጣቱን ወሳኝ ችግሮች ለመፍታት እንደመነሻ የሚሆኑ ሀሳቦች የሚገኙበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ያለወጣቱ ተሳትፎ የትኛውም ጉዳይ ግቡን እንደማይመታ ያምናል ያሉት አቶ ሰንበቶ የጉባኤው ውሳኔዎች ወደተግባር የሚቀየሩት በወጣቱ ስለሆነ ሁሉም ወጣቶች በመድረኮቹ በንቃት እንዲሳተፉም አሳስበዋል፡፡
በመድረኮቹ የፓርቲዉ አባል ያልሆኑ ወጣቶችም ጭምር እንደሚሳተፉ ያስታወቁት ጽህፈት ቤት ሃኃፊው፣ የውይይት መድረኮቹ በ157 አካባቢዎች እንደሚካሄዱና ለዚህም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
ወጣቱ ለአካባቢው፣ለክልሉና ለአገሪቱ ይበጃሉ የሚላቸውን ሀሳቦች በቅንነት በማንሳት ዘላቂ ሰላም ያለው፣ የበለጸገ አገርና ህዝብ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት የራሱን ሚና እንዲጫወትም አቶ ሰንበቶ ጠይቀዋል፡፡
የኑሮ ውድነቱን ለማስተካከልና የምርት አቅርቦቱን ለማሳደግ የሚያስችል የከተማ ግብርና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የሚካሄድ ሲሆን በከተማ ግብርና መልካም ተሞክሮ ያላቸው ግለሰቦች ጥረትም ጉብኝት ይካሄዳል ብለዋል፡፡
የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከ840 ሺህ በላይ አባላት እንዳሉት ያመለከቱት አቶ ሰንበቶ በቀጣይ እስከ ገጠር ቀበሌያት የሚገኙ ሁሉንም ወጣቶች በጉባኤው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ለማወያየት እቅድ መያዙን አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደቡብ አፍሪካ የጎርፍ አደጋ ባደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ አፍሪካ በጣለው ከባድ ዝናብና ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ባለፉት ጥቂት ቀናት በጣለው ከባድ ዝናብና በተከሰተው ጎርፍ ለተጎዱ ደቡብ አፍሪካውያን መጽናናትን ተመኝተዋል።
በደቡብ አፍሪካ የጣለው ከባድ ዝናብና ባስከተለው ጎርፍ በንብረት እና በሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
“አካባቢየን በመጠበቅ ኃላፊነቴን እወጣለሁ” በሚል ሀሳብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት አካሄዷል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ፣ የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ማስቻል ነው። ለዚህም ስኬታማነት የከተማዋ ነዋሪዎች የጋራ ራዕይና ትብብር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ሁላችንም ለሠላም ዋጋ በመስጠት የአካባቢያችንን ሁለንተናዊ ሠላም ለማረጋገጥ ከጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀንዓ ያዴታ በከተማዋ መልካቸውን በመለዋወጥ የሚያጋጥሙ የወንጀል እንቅስቃሴዎችን በመከለከል ዘላቂ ሰላምና ደሕንነትን ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የፀጥታ ተቋማትን ሁለንተናዊ አቅም በማሳደግ ወንጀልና የደንብ ጥሰትን መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል ኃላፊው ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አራጋው መንግሥት በሁሉም ረገድ የፀጥታ ተቋማትን ወቅቱ በሚጠይቀው መልኩ ሪፎርም ለማድረግ መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ማህበረሰብ እቅፍ የፖሊስ ስራዎች ወንጀልን በመከላከል ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ማጠናከር ይገባል ተብሏል።
ያለሕብረተሰቡ ተሳትፎ በዘላቂነት ሠላምን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ ፤የከተማችን ነዋሪ ፖሊስ የሚፈልገውን የመረጃ ድጋፍ በመስጠት በአጋርነት መቆም ይጠበቅበታል ብለዋል ።
የሐይማኖት አባቶች ፣ወጣቶች ፣የብሎክ አደረጃጀት ተወካዮች ፣የፀጥታ አካላት፣ታወቂ ግለሰቦች በውይይቱ መሳተፋቸውን ቢሮው አሰታውቋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየአመቱ ለህንጻ ኪራይ የሚያወጣውን ከፍተኛ ገንዘብ ለማስቀረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ ቢሮዎቹ በየአመቱ ለህንጻ ኪራይ የሚያወጣውን አንድ ቢሊየን ብር ለማስቀረት እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ የሱፍ ኢብራሂም የተቋሙ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በቀረበበት ወቅት እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት ከተማ አስተዳደሩ በአመት አንድ ቢሊየን ብር ለህንጻ ኪራይ እያወጣ ይገኛል።
ህንጻዎችን በማስገንባት ይህንን ወጪ ለማስቀረትና ከኪራይ ነጻ ለማድረግ መሬት ተዘጋጅቶ እንቅስቀሴ ተጀምሯል። የህንጻዎቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ መንግስትን ከወጪ በመታደግ ገንዘቡን ለሌሎች ልማቶች እንዲያውል የሚጠቅመው ይሆናል።
የሚገነቡት ህንጻዎች በአንድ አካባቢ በመሆኑ በተቋማት መካከል የሚኖርን የስራ ግንኙነት የሚያፋጥንና ለመረጃና ለቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሁ ለትራንስፖርት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ይሆናል ብለዋል። ከከተማ መስተዳድሩ አገልግሎት የሚፈልጉ ተገልጋዮችም ተቋማቱን በአንድ አካባቢ የሚያገኟቸው በመሆኑ ከውጣ ውረድ ይድናሉም ነው ያሉት።
ባለስልጣኑ ባለቤት አልባ ህንጻዎችን እየለየ መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስኪያጁ እስካሁንም ባለቤት አልባ ህንጻዎች መለየታቸውን በመጠቆም በፍርድ ቤት አሳውጆ ተረክቦ ለማስተዳደር በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በራስወርቅ ሙሉጌታ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
አሪፍ ፔይ የተሰኘ የኦንላይን ክፍያ ስርዓት ከብሄራዊ ባንክ ፍቃድ አገኘ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
አሪፍ ፔይ የተሰኘ የኦንላይን ክፍያ ስርዓት ከብሄራዊ ባንክ ፍቃድ አግኝቶ ወደ ስራ መግባቱን አሰታወቀ።
ነጋዴዎች፣ የቢዝነስ ሰዎችና ማንኛውም ተጠቃሚ በኦንላይን ክፍያ መፈፀም የሚያስችላቸውና ደረሰኝ ማግኘት የሚችሉበት የክፍያ ስርዓት ነው ተብሏል።
በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለድርሻነት በ3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር የመነሻ ሃብት ነው ስራውን የጀመረው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ እንደ አሪፍ ፔይ ያሉ የኦንላይን ክፍያ ስርዓቶች የኤሌክትሮኒክስ ንግድን ለማሳለጥ ትልቅ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።
ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የኦንላይን ክፍያ አማራጮች መበራከት አለባቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በኢኖቬሽን የታገዘ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እንዲበራከቱ የስታርት አፕ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለመጽደቅ የሚያስችለው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በኦንላይን ክፍያ እየፈፀሙ ያሉት ዜጎች ከአጠቃላይ ህዝብ ቁጥር 2 ከመቶው ብቻ መሆናቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 47 ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ መጓዛቸው ተገለፀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ተጨማሪ ሰብአዊ እርዳታ የጫኑ የተባባሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም የምግብ ፕሮግራም 47 ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ ማቅናታቸው ተገለጸ።
እነዚህ ተሽከርካሪዎች ምግብ፣ ምግብ ነክና ሌሎች ህይወት አድን ዕርዳታ መጫናቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አስታውቋል።
በተጨማሪም ሶስት ቦቴ ነዳጅ የጫኑ መኪናዎችም ወደ መቀሌ ተጉዘዋል ያለው ድርጅቱ፤ ተሽከርካሪዎቹ ያለምንም ችግር እየተጓዙ መሆኑንም ጨምሮ አስታውቋል።
በሀይማኖት ከበደ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️