Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
302 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ገንዘብ እናባዛለን ብለው ከአንድ ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ለማጭበርበር የሞከሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ቦሌ ሆምስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ገንዘብ እናባዛለን ብለው ከአንድ ግለሰብ ላይ ከአንድ ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ብር ለማጭበርበር የሞከሩ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በበዓላት መዳረሻ ወቅቶች ሃሰተኛ ገንዘቦች በገበያው ውስጥ ሊሰራጩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
አንድ ግለሰብ በአጋጣሚ ለተዋወቁት ሰው ገንዘብ እንደቸገራቸው ከነገሩትና ይህ ሰውም "ገንዘብ የሚያባዛ ሰው አውቃለሁ ችግር የለም ያባዛሎታል" ካላቸው በኋላ ነበር የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው፡፡
ገንዘብ ቸግሮኛል ያሉት ግለሰብ እንዲባዛልኝ ብለው ለተጠርጣሪዎቹ 2 ሚሊዮን ብር ስለመስጠታቸው በምርመራ ወቅት መግለፃቸውን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ገንዘብ እንዲባዛ አደርጋለሁ ያለው ተጠርጣሪ የናይጄሪያ ዜግነት ካለው ግብራበሩ ጋር በመሆን የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እያሉ ፖሊስ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ገንዘብ ይባዛበታል በተባለው ቤት ውስጥ በህግ አግባብ ብርበራ ማከናወኑን ገልጿል፡፡
በተደረገው ብርበራም እንዲባዛላቸው ግለሰቡ ሰጥቻለሁ ካሉት 2 ሚሊዮን ብር ውስጥ 1 ሚሊዮን 555 ሺህ 8 መቶ ብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በተጨማሪም በብር መጠን የተቆራረጠ በርካታ ወረቀት፣ ኬሚካል እና ማተሚያ ማሽን ተይዟል፡፡
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው የቀጠለ ሲሆን ፖሊስ ገንዘብ ይባዛበታል ወደ ተባለው ቤት ለብርበራ በሄደበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ ማስረጃ ለማጥፋት በማሰብ በብር መጠን ተቆራርጦ የተቀመጠውን ወረቀት በእሳት ለማቃጠል እና የጣራ ቆርቆሮ ገንጥለው ለማምለጥ መሞከራቸውን አስታውቋል፡፡
ህገ-ወጥ ተግባራት በህብረተሰቡ እና በፀጥታ አካላት ትብብር እየከሸፉ እንደሚገኙ የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለይም ከበዓላት መቃረብ ጋር ተያይዞ ሃሰተኛ ገንዘቦችን ወደ ገበያ ውስጥ ለማሰራጨት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በተቀናጀ መንገድ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚገባ እና ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅበት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችንና አስቸኳይ የምግብ ድጋፎችን የያዘ ቡድን መቀሌ ደርሷል
********************
(ኢ ፕ ድ)

በዚህ ወር ለሁለተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ አስቸኳይ የምግብ ድጋፎችን አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን የያዘ ቡድን መቀሌ መግባታቸውን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አሰታወቀ።

ለሁለተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ አስቸኳይ የምግብ ድጋፎችን፣ የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችንና አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን የያዘ ቡድን ዛሬ ሚያዝያ 6፣ 2014 ዓ.ም መቀሌ ገብተዋል።

በተጨማሪም ድጋፉ ለአካል ተሃድሶ ማዕከል አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችንም ያካተተ መሆኑንም የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አሰታውቋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ባለፉት ሁለት ቀናት 50 ምግብና ነዳጅ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ ትግራይ ክልል ተልከዋል

👉 ተጨማሪ 10 የምግብ እርዳታን የያዙ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ጉዞ ጀምረዋል፣

👉 በመጀመሪያው ዙር የምግብ ድጋፍን የያዙ 21 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ገብተዋል፣
****************
(ኢ ፕ ድ)

መንግስት በትግራይ ክልል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ በተገቢው መንገድ አንዲደርስ ለማስቻል የግጭት ማቆም ውሳኔን ማሳለፉ የሚታወስ ነው።ይህንን ተከትሎም የሰብአዊ እርዳታን ወደ ክልሉ ለማድረስ በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

ከእነዚህም መካከል በየቀኑ የሚደረግ የአየር ትራንስፖርትን በማመቻቸት የእርዳታ አቅራቢ ተቋማት አቅም የፈቀደውን ያህል የመድሃኒት፤ የህክምና ቁሳቁስና አልሚ ምግብ እንዲያጓጉዙ ሁኔታዎችን አመቻችቷል።

በየብስ ትራንስፖርትም በመጀመሪያው ዙር የምግብ ድጋፍን የያዙ 21 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እንዲገቡ ተደርጓል።
ባለፉት ሁለት ቀናት ደግሞ 47 የምግብ ድጋፍ የያዙና 3 ነዳጅ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች በድምሩ 50 የጭነት መኪኖች ከሰመራ ተነስተው ወደ መቀሌ ጉዞ እያደረጉ ነው።

ተጨማሪ 10 የምግብ እርዳታን የያዙ የጭነት ተሽከርካሪዎችም ከሰመራ ጉዞ ጀምረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ የገባውን ቃል በማክበር ምቹ የሰብአዊ ርዳታ ማጓጓዣ ሁኔታን ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል።

አለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህንን መንግስት ያቀረበውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወደ ትግራይ የሚደርሰውን የእርዳታ መጠን ከፍ ሊያደርግ ይገባል።

በሌላ በኩል በአስቸጋሪ ሁኔታ ወስጥ የሚገኙት የክልሉ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ወራሪው ሃይል አሁንም ከያዛቸው የአፋርና አማራ ክልል አካባቢዎች እንዲወጣና ምቹ የእርዳታ ማስተላለፊያ መስመርን መዘርጋት እንዲቻል አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን
ከሳዑዲ ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን በቤተ መንግስት የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ተካሄደ
****
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ከሳዑዲ አረቢያ ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን በቤተ መንግስት የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሳዑዲ ዓረቢያ ለተመለሱ 250 ኢትዮጵያውያን የኢፍጣር እራት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለብዙ ወራት በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ እየመለሰ ይገኛል። ዜጎቹ ተጠቃልለው ወደ ሀገራቸው እስኪመለሱ ድረስ ይህን ሥራ ይቀጥላል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ