Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከሳዑዲ ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን በቤተ መንግስት የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ተካሄደ
****
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ከሳዑዲ አረቢያ ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን በቤተ መንግስት የኢፍጣር ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሳዑዲ ዓረቢያ ለተመለሱ 250 ኢትዮጵያውያን የኢፍጣር እራት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለብዙ ወራት በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ እየመለሰ ይገኛል። ዜጎቹ ተጠቃልለው ወደ ሀገራቸው እስኪመለሱ ድረስ ይህን ሥራ ይቀጥላል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
አቶ ደመቀ መኮንን የፓርላማ አባላትንና የሕክምና ባለሙያዎችን ካካተተው የእስራኤል የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የፓርላማ አባላትንና የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተውን የእስራኤል የልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በእስራኤል የፓርላማ አባል አቶ ጋዲ ይባርከን የተመራው የልዑክ ቡድኑ የፓርላማ አባላትንና የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።

የልዑካን ቡድኑ በጎንደር አካባቢ ጉበኝት በማድረግ በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ደመቀ መኮንን የልዑካን ቡድኑ በዚህ ወሳኝ ወቅት በአገራችን ጉብኝት ማድረጉን አድንቀዋል።

ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት ታሳቢ ያደረገው ይህ የእስራኤል የልዑካን ቡድን ውቅታዊ ጉብኝት፥ የሁለቱን ሀገራት የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑንም ነው አቶ ደመቀ የገለጹት።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የልዑካን ቡድኑ በአጭር ጊዜ እቅዱ ቅድሚያ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቆማት መልሶ መገንባት እና ማደረጃት ላይ ሊሆን እንደሚገባ በውይይታቸው ላይ ትኩረት ሰጥተው አንስተዋል።

የልዑካን ቡድኑ ዘለቄታነት ባለው ዕቅዱ ከጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል እና ከሌሎች የኢትዮጵያ የጤና ተቋማት ጋር በቅርበት የመስራት ፍላጎት እንዳለው መግለጹንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የእስራኤል ፓርላማ አባላትንና የሕክምና ባለሙያዎች ልዑክ ጋር ተወያዩ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በእስራኤል የፓርላማ አባል አቶ ጋዲ ይባርከን የተመራውን የፓርላማ አባላትንና የሕክምና ባለሙያዎችን ካካተተው የልዑክ ቡድንን ተቀብለው አነጋግረዋል።

የፓርላማ አባላትንና የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተውን የእስራኤል የልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ፣ የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ጠንካራ መሠረት ላይ ያስቀምጠዋል ብለዋል።

ሁለቱ ሀገራት በጤና፣በግብርና: በኢንቨስትመንት የበለጠ ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸው ተገልጸዋል።

የልዑካን ቡድኑ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት የወደሙ የጤናና የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት፣ ሥልጠና ለመስጠት: ዘላቂ ድጋፍ ለማድረግ ያስችላቸው ዘንድ የመስክ ጉብኝት ማድረጋቸውን ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ