Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
301 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት አያያዙ ቢስተካከልም የፍትህ አሰጣጡ መሻሻል እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ይታዩ የነበሩ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች ቢስተካከሉም የፍትህ አሰጣጥ ሥርዓቱ ግን መሻሻል እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ትናንት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው የታራሚዎችን ሰብዓዊ አያያዝ በተመለከተና የማረሚያ ቤት አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታዎችን ቃኝቷል።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች ለቋሚ ኮሚቴው በሰጡት አስተያየት ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች እንደሌሉ ጠቁመው፤ ከፍርድ አሰጣጥ መዘግየትና ፍትህ መዛባት ችግሮች መኖራቸውን ግን ተናግረዋል።
በተለይም ፍርድ ቤቶች የሚወስኑትን ውሳኔዎች ተፈፃሚ ያለማድረግ፣ የይቅርታ አሰጣጥ ሥርዓት ተገቢው የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶለት በግልፀኝነት አለመመራቱ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70901
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ባለስልጣኑ 150 ሺህ የቀበሌ ቤቶችን ኦዲት እንደሚያደርግ አስታወቀ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በከተማዋ የሚገኙ 150 ሺህ የቀበሌ ቤቶችን ኦዲት ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ የሱፍ ኢብራሂም ትናንት የተቋሙን የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳስታወቁት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚገኙ 150 ሺህ የቀበሌ ቤቶች ላይ የኦዲት ሥራ ያከናውናል።
የኦዲቱ ሥራው የቀበሌ ንግድ ቤቶችንና መኖሪያ ቤቶችን የሚያካትት ሲሆን፤ የማጣራት ሥራው የሚከናወነው በየክፍለ ከተሞች ካሉ አመራሮች ጋር ነው ብለዋል።
የቀበሌ ቤቶች ጉዳይ ሰፊ የፍትህ ጥያቄና ቅሬታ የሚቀርብበት ነው ያሉት አቶ የሱፍ፤ ሥራው ሲጠናቀቅ ግልጽነት ያለው አሠራር ለመዘርጋት ይረዳል። በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩም ምን ያህል ቤት በምን ዓይነት ሁኔታ..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70913
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የኢትዮጵያ ሐኪሞች ማህበር 58ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባኤውን እያካሄደ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሐኪሞች ማህበር 58ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ ዓወደ ርዕይ እየተካሄደ ነው።
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ተግባር ይግዛው (ዶክተር) ያለፈው ዓመት በጦርነትና በኮቪድ 19 ምክንያት ለጤና ሴክተሩ ፈታኝ ነበር ብለዋል።
በጦርነት ምክንያት የወደሙ በርካታ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባትና በሌሎች አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ለሰጡት ሙያዊ አገልግሎት የጤና ባለሙያዎችን አመሥግነዋል።
የ21ኛው ክፍለ ዘመን ያልተጠበቁና አደገኛ የሆኑ የጤና ቀውሶች ሊፈጠሩ የሚችሉበት ወቅት በመሆኑ የጤና ባለሙያዎች በሙያዊ እውቀትና በሥነልቦና ራሳቸውን ሊያዘጋጁ ይገባል ብለዋል።
ማህበሩ የጤና ባለሙያዎችን ብቃት ለማሳደግና ህይወት ለመቀየር ሲሠራ ቆይቷል። ይህን ተግባሩን አጠናካሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
በውብሸት ሰንደቁ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በሊባኖስ ያለህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 32 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በሊባኖስ ያለህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 32 ዜጎቻች ወደ አገራቸው በሰላም ገብተዋል ።
ጉዳያቸው በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት በኩል ከሊባኖስ የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር እንዲያልቅ ከተደረገ በኋላ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
በቤይሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በቅርበት በመነጋገር ያለምንም መጉላላትና እንግልት እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያን አዘጋጅቶ እንዲጠቀም ለማስቻል እየሠራ መሆኑን ቢሮው አስታወቀ
********************
(ኢ ፕ ድ)
አርሶ አደሩ በስፋት የተፈጥሮ ማዳበሪያን አዘጋጅቶ እንዲጠቀም ንቅናቄ በመፍጠር በትኩረት እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ክትትል ዳይሬክተር አቶ አለባቸው አሊጋዝ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሁን ካለው የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እጥረትና የዋጋ ንረት ጋር በተያያዘ አርሶ አደሩ ምርት ማምረት እንዲችል የተፈጥሮ ማዳበሪያን በስፋት አዘጋጅቶ እንዲጠቀም በትኩረት እየተሠራ ነው።
የክልሉ አርሶ አደሮች እንደ ኮምፖስት፣ አረንጓዴ ማዳበሪያና ሌሎች የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን እንዲያዘጋጅ የማድረግ ሥራ ከፍተኛ ንቅናቄ በመፍጠር በስፋት እየተሠራ ስለመሆኑ የሰብል ልማትና ክትትል ዳሬክተሩ ገልጸዋል።
እንደ አቶ አለባቸው ገለጻ፤ የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ውድነቱ እንደ አገር ብሎም እንደ ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጫና ነው።ይህን ጫና ለመቋቋም አርሶ አደሩን የተፈጥሮ ማዳበሪያ እንዲጠቀምና ምርታማነቱን በሚፈለገው ልክ እንዲያሳድግ በሰፊው እየተሠራበት ነው።
ቀደም ሲል ባሉት ዓመታት አርሶ አደሩ የሰው ሠራሽ ማዳበሪያ የሚያገኝበት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70896
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
አለም አቀፍ የሠራተኞች ስምምነት በኢትዮጵያ የህግ ስርዓት ውስጥ ተካተው እንዲተገበሩ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ
************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የሠራተኞች ፍልሰትን አስመልክቶ በአለም የሥራ ድርጅት በኩል የወጡት አለም አቀፍ ስምምነቶች በኢትዮጵያ የህግ አካል ሆነው ተግባራዊ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሐግብር አካሄደ።
በመረሐግብሩ ላይ በስራ ቦታ ላይ የሚደርስ ጥቃትንና ትንኮሳን መከላከል ስምምነት ቁጥር 190፤ የቤት ሠራተኞች ላይ የሚደርስ የመብት ጥሰትና እንግልትን ስለማስቆም ስምምነት ቁጥር 189፣ ከሰራተኛዉ መብት ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ስምምነት ቁጥር 97 እና 143 ተዋውቀዋል።
እነዚህ ህጎቹ ተቀባይነት አግኝተው በመጽቃቸው በአገሪቱ ስራ ቦታ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በመቅረፍና የሰራተኛውን መብት በማስከበር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በመድረኩ ተገልጿል።
ለመንግስትም ሰራተኛ ተቀባይ ከሆኑ ሀገራት ጋር ለመደራደር ትልቅ አቅም እንደሚሆነም ተገልጿል።
በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ የሠራተኞች ፍልሰትን በአገር ውስጥም የሚሰሩ ሰራተኞችም መብታቸዉ ሊጠበቅ ይገባል። መንግስት ኮንቬንሽኖቹን በማጽደቅ ከኢሠማኮ ጎን እንዲሆን ጠይቀዋል።
በአለም አቀፍ የሥራ ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር አሌክሶ ሙሴንዶ በበኩላቸው፣ የኮንቬንሽኖቹ መጽደቅ የሰራተኛውን መብት በማስከበር ትልቅ አስተዋጾ እንደሚኖረዉ ተናግረዋል።
የአለም ስራ ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር አሌክሶ ሙሲንዶ፣ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽኖች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ታደሰ ይመር እና የሚመለከታቸዉ አካላት በጋራ በይፋ አስጀምረውታል።
በመዓዛ ማሞ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በሀረሪ ክልል የፖሊዮ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሉ ሁለተኛው የፖሊዮ ክትባት በዛሬው እለት መሰጠት ተጀምሯል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢብሳ ሙሳ በአቦነ እንድሪያስ ካቶሊክ ትምህርት ቤት የክትባት ዘመቻውን አስጀምረዋል።
በክልሉ በሚሰጠው የክትባት ዘመቻ ከ56 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑ ህፃናትን ለመከተብ መታቀዱን ገልፀዋል።
ክትባቱም በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ቤት ለቤትና በትምህርት ቤቶች እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት በማስከተብ የፖሊዮ በሽታ ለጥፋት በሚከናወኑ ተግባራት ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️