Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት እንዲኖር የሐኪሙን ብቃት ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቆመ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት እንዲኖር ከተፈለገ የሐኪሙን ብቃት ማሳደግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ተግባር ይግዛው በትናንትናው ዕለት የማኅበሩ 58ኛ ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤ ሲካሄድ እንደገለጹት፤ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት እንዲኖር ከተፈለገ የሐኪሙን ብቃት ማሳደግ ይገባል፤ ለዚህም ሲባል ማኅበሩ ከተመሠረተ ጀምሮ የሐኪሞችን ሙያ ማጎልበቻ ሥርዓት ዘርግቶ እየሠራ ይገኛል።
ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ኅብረተሰቡ እንዲያገኝ ማስቻል የማኅበሩ ዋና ዓላማ ነው ያሉት ዶክተር ተግባር፤ የሙያ ማኅበር እንደመሆኑ ለሐኪሞች ድምፅ የመሆንና የሐኪሞችን ጥቅም ማስከበር ሥራም ይሠራል። በተጨማሪም ምርምር በማድረግና የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ የሕክምናን ሙያ እያሳደገ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።
21ኛው ክፍለ ዘመን አዳዲስና ያልታሰቡ ፈተናዎችን ይዞ እየመጣ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70979
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ወታደራዊ መረጃ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
***********************
(ኢ ፕ ድ)
የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ወታደራዊ መረጃ መድረክ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የመከላከያ ህብረት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ በውይይት መድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ ፎረሙ ድንበር ተሻጋሪ የደህንነት ስጋቶችን በትብብር ለመፍታት የሚያስችል ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የምስራቅ አፍሪካን ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ በጋራ መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል።
በጸጥታ ዙሪያ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በየአገራቱ የመረጃና ልምድ ልውውጥ ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት የመምሪያው ኃላፊ፤ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ወዳጅነትን በማጠናከር በትብብር መሥራት እንደሚገባና ኢትዮጵያ ለዚህ ቁርጠኛ አቋም እንዳላት አመላክተዋል።
በመድረኩ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት የመከላከያ ጄኔራሎች እየታሳተፉ ሲሆን፤ ውይይቱ ቀጠናዊ የመረጃ ልውውጥና ልምድ የሚሰጠበት እንደሆነ፤ እንዲሁም የተለያዩ የሥራ ዘገባዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።
በአዲሱ ገረመው
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በመረጃ ክልከላና በባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት ለመፍታት ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተገለጸ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በመረጃ ክልከላ፣ በመገናኛ ብዙሃን እና ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት መፍታት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ከፋና ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅባቸውን የምርመራ ስራዎች እና መረጃዎችን ተደራሽ እንዲያደርጉ ቁርጠኝነት ቢኖረውም የመረጃ ፍሰቱ ላይ ከትናንት የተረከብናቸው ከፍተኛ ችግሮች አሉ ብለዋል።
የስራ ሃላፊዎች እና ተቋማት በአብዛኛው ለቦታው አዲስ ነኝ፤አይመለከተኝም እና ሌሎች ምክንያት በማቅረብ ለመገናኛ ብዙሃኑ ተግበራት ማነቆ ይሆናሉ ነው ያሉት።
ይህን በአገሪቱ በስፋት የሚስተዋልን ችግር ለመቅረፍ የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ውይይት ተደርጎበት ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
መመሪያው ከፌደራል ጀምሮ እስከ ታችኛው የኮሙኒኬሽን እርከን የግንኙነት አሰራር የሚፈጥር ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎች ተቋማቸውን የሚያስተዋውቁበት እንዲሁም ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ያላቸው ግንኙነት የሚጠናክሩበትን እድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎችን በስልጠናዎች የማገዝ፣ የአቅም ግንባታ ስራዎች እና ሌሎች ተግባራትም በቀጣይ በትኩረት የሚሰራባቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በንብ ማነብ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ምርታቸውን እያሳዩ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል አራት ዞኖች ስምንት ወረዳዎች በንብ ማነብ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች በዘመናዊ የአመራረት ዘዴ ተጠቅመው አጣርተውና አሽገው ያዘጋጅትን የማር ምርት በቡኖ በደሌ ዞን በበደሌ ከተማ በተዘጋጀው የማር ፌስቲቫል ላይ በማቅረብ እያስተዋወቁ ይገኛሉ።
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ፣ ቡኖበደሌ፣ ኢሉአባቦራ እና ጅማ ዞኖች በስምንት ወረዳዎቸ ውስጥ በንብ ማነብ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው 48 ማህበራትና 8 ሞዴል አርሶአደሮች የማር ምርታቸውን በማስተዋወቅ ላይ ናቸው።
በአራቱ ዞኖች በስምንት ወረዳዎች በንብ ማነብ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው 14 ሺህ 200 ወጣቶች ናቸው።
ፌስቲቫሉን በጋራ ያዘጋጁት በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የሚታገዘው ዓለም አቀፍ የሥነ ነፍሳት ምርምር ማዕከል ሞይሽ ፕሮግራም፣ የቡኖበደሌ ዞን ግብርና ቢሮና የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ሲሆኑ የዞኑ እና የወረዳው አመራሮች ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዓለምአቀፍ የሥነ ነፍሳት ምርምር ማዕከል የሞይሽ ፕሮግራም የኦሮሚያ ተጠሪ አቶ ተሾመ ኩመላ እንደገለጹት የሥራ ዕድሉ የተፈጠረላቸው በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ 188ሺ ቶን ማር በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የክልሉ አራቱ ዞኖች በማር ሀብት የሚታወቁ መሆናቸውን ከፕሮግራሙ ለመረዳት ተችሏል።
በለምለም መንግስቱ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ኤጀንሲው በዘጠኝ ወራቱ 705 ሺህ የህግ ጥሰት በፈጸሙ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ
👉 አዲስ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የደንብ ልብስ ይፋ አድርጓል፣
****************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በበጀት ዓመቱ ባለፋት ዘጠኝ ወራት 705 ሺህ 047 ሕግን በተላለፈው አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አሰታወቀ።
ኤጀንሲው አዲስ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የደንብ ልብስን ይፋ አደርጓል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ በግንዛቤ የተደገፈ ጥብቅ የትራፊክ ቁጥጥር በማድረግ በትራፊክ ግጭት አደጋ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስና ለማስቀረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የትራፊክ ቁጥጥር ስራውን በመገምገም ያጋጠሙ ችግሮችን በቀሪ ሶስት ወራት ለመፍታት እንደሚሠራም አመልክተዋል።
አዲሱ የትራፊክ ቁጥጥር የደንብ ልብስ የቁጥጥር ስራውን ለማጠናከርና ተመሣሣይ አንፀባራቂ ልብስ በመልበስ የተሽከርካሪ ዘረፋና ሌብነት ተግባርን ለመቅረፍ የሚያግዝ መሆኑም ተመልክቷል።
የብሉምበርግ ኢኒሺየቲቭ የዳታ ምርመራ ባለሙያ ወይዘሮ ሜሮን ጌታቸው፣ የትራፊክ ሞት አደጋ ከሐምሌ 2014 እስከ ታህሳስ 2014 ባለፉት ስድስት ወራት ከ2013 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አንፃር በአምስት በመቶ መጨመሩን ባቀረቡት ሪፖርተር አመላክተዋል።
በኃይሉ አበራ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️