Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ወታደራዊ መረጃ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
***********************
(ኢ ፕ ድ)
የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ወታደራዊ መረጃ መድረክ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የመከላከያ ህብረት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ በውይይት መድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ ፎረሙ ድንበር ተሻጋሪ የደህንነት ስጋቶችን በትብብር ለመፍታት የሚያስችል ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የምስራቅ አፍሪካን ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ በጋራ መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል።
በጸጥታ ዙሪያ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በየአገራቱ የመረጃና ልምድ ልውውጥ ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት የመምሪያው ኃላፊ፤ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ወዳጅነትን በማጠናከር በትብብር መሥራት እንደሚገባና ኢትዮጵያ ለዚህ ቁርጠኛ አቋም እንዳላት አመላክተዋል።
በመድረኩ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት የመከላከያ ጄኔራሎች እየታሳተፉ ሲሆን፤ ውይይቱ ቀጠናዊ የመረጃ ልውውጥና ልምድ የሚሰጠበት እንደሆነ፤ እንዲሁም የተለያዩ የሥራ ዘገባዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።
በአዲሱ ገረመው
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በመረጃ ክልከላና በባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት ለመፍታት ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተገለጸ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በመረጃ ክልከላ፣ በመገናኛ ብዙሃን እና ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት መፍታት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ከፋና ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅባቸውን የምርመራ ስራዎች እና መረጃዎችን ተደራሽ እንዲያደርጉ ቁርጠኝነት ቢኖረውም የመረጃ ፍሰቱ ላይ ከትናንት የተረከብናቸው ከፍተኛ ችግሮች አሉ ብለዋል።
የስራ ሃላፊዎች እና ተቋማት በአብዛኛው ለቦታው አዲስ ነኝ፤አይመለከተኝም እና ሌሎች ምክንያት በማቅረብ ለመገናኛ ብዙሃኑ ተግበራት ማነቆ ይሆናሉ ነው ያሉት።
ይህን በአገሪቱ በስፋት የሚስተዋልን ችግር ለመቅረፍ የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ውይይት ተደርጎበት ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
መመሪያው ከፌደራል ጀምሮ እስከ ታችኛው የኮሙኒኬሽን እርከን የግንኙነት አሰራር የሚፈጥር ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎች ተቋማቸውን የሚያስተዋውቁበት እንዲሁም ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ያላቸው ግንኙነት የሚጠናክሩበትን እድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎችን በስልጠናዎች የማገዝ፣ የአቅም ግንባታ ስራዎች እና ሌሎች ተግባራትም በቀጣይ በትኩረት የሚሰራባቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በንብ ማነብ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ምርታቸውን እያሳዩ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል አራት ዞኖች ስምንት ወረዳዎች በንብ ማነብ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች በዘመናዊ የአመራረት ዘዴ ተጠቅመው አጣርተውና አሽገው ያዘጋጅትን የማር ምርት በቡኖ በደሌ ዞን በበደሌ ከተማ በተዘጋጀው የማር ፌስቲቫል ላይ በማቅረብ እያስተዋወቁ ይገኛሉ።
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ፣ ቡኖበደሌ፣ ኢሉአባቦራ እና ጅማ ዞኖች በስምንት ወረዳዎቸ ውስጥ በንብ ማነብ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው 48 ማህበራትና 8 ሞዴል አርሶአደሮች የማር ምርታቸውን በማስተዋወቅ ላይ ናቸው።
በአራቱ ዞኖች በስምንት ወረዳዎች በንብ ማነብ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው 14 ሺህ 200 ወጣቶች ናቸው።
ፌስቲቫሉን በጋራ ያዘጋጁት በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የሚታገዘው ዓለም አቀፍ የሥነ ነፍሳት ምርምር ማዕከል ሞይሽ ፕሮግራም፣ የቡኖበደሌ ዞን ግብርና ቢሮና የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ሲሆኑ የዞኑ እና የወረዳው አመራሮች ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዓለምአቀፍ የሥነ ነፍሳት ምርምር ማዕከል የሞይሽ ፕሮግራም የኦሮሚያ ተጠሪ አቶ ተሾመ ኩመላ እንደገለጹት የሥራ ዕድሉ የተፈጠረላቸው በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ 188ሺ ቶን ማር በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የክልሉ አራቱ ዞኖች በማር ሀብት የሚታወቁ መሆናቸውን ከፕሮግራሙ ለመረዳት ተችሏል።
በለምለም መንግስቱ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ኤጀንሲው በዘጠኝ ወራቱ 705 ሺህ የህግ ጥሰት በፈጸሙ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ
👉 አዲስ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የደንብ ልብስ ይፋ አድርጓል፣
****************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በበጀት ዓመቱ ባለፋት ዘጠኝ ወራት 705 ሺህ 047 ሕግን በተላለፈው አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አሰታወቀ።
ኤጀንሲው አዲስ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የደንብ ልብስን ይፋ አደርጓል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ በግንዛቤ የተደገፈ ጥብቅ የትራፊክ ቁጥጥር በማድረግ በትራፊክ ግጭት አደጋ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስና ለማስቀረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የትራፊክ ቁጥጥር ስራውን በመገምገም ያጋጠሙ ችግሮችን በቀሪ ሶስት ወራት ለመፍታት እንደሚሠራም አመልክተዋል።
አዲሱ የትራፊክ ቁጥጥር የደንብ ልብስ የቁጥጥር ስራውን ለማጠናከርና ተመሣሣይ አንፀባራቂ ልብስ በመልበስ የተሽከርካሪ ዘረፋና ሌብነት ተግባርን ለመቅረፍ የሚያግዝ መሆኑም ተመልክቷል።
የብሉምበርግ ኢኒሺየቲቭ የዳታ ምርመራ ባለሙያ ወይዘሮ ሜሮን ጌታቸው፣ የትራፊክ ሞት አደጋ ከሐምሌ 2014 እስከ ታህሳስ 2014 ባለፉት ስድስት ወራት ከ2013 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አንፃር በአምስት በመቶ መጨመሩን ባቀረቡት ሪፖርተር አመላክተዋል።
በኃይሉ አበራ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በዓለም የሥራ ድርጅት የፀደቁ የሠራተኛ ፍልሰት ስምምነቶች በኢትዮጵያ ተግባራዊ እንዲደረጉ ተጠየቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በዓለም የሥራ ድርጅት /ILO/ የፀደቁ የሠራተኛ ፍልሰት ስምምነቶች በኢትዮጵያም የሕግ አካል ሆነው እንዲተገበሩ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን(ኢሰማኮ) ጠየቀ።
የሠራተኞች ፍልሰትን በተመለከተ የጸደቁ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በኢትዮጵያ ተግባራዊ እንዲደረጉ የሚገፋፋ የግንዛቤ ማስጨበጫ የዘመቻ ፕሮግራም ትናንትና ተጀምሯል።
በወቅቱት የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፤ ለፍልሰት የተጋለጡና በአገር ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች መብቶቻቸው ሊጠበቁ እንደሚገባ ጠቁመው፤ መንግሥት ስምምነቶቹን በማጽደቅ መብታቸውን እንዲያስከብር ጠይቀዋል።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ሠራተኞች፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት በቤት ሠራተኝነት የሚያገለግሉ ጥቃትና ትንኮሳ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70976
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የአምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች የጋራ ሪፖርት ፍጹም ሐሰት መሆኑን በወልቃይትና አካባቢው በመገኘት ለማየት ችያለሁ
********************
(ኢ ፕ ድ)
አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች በወልቃይት ዙሪያ ያወጡት የጋራ ሪፖርት ፍጹም ሐሰት መሆኑን በቦታው ላይ ተገኝቼ ለማየት ችያለሁ ስትል ትውልደ-ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ቤቲ ተከስተ ገለጸች።
በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የተገኙትን የጅምላ መቃብሮች መመልከቷንና አሁንም ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግራለች።
በቨርጂኒያ ግዛት የምትኖረው የፑሽ ስታርት ሚዲያ ጋዜጠኛ ቤቲ ተከስተ ከአሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን እንዲሁም አሜሪካዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ጀማል ካውንተስ ጋር በመሆን በአማራ ክልል በጦርነቱ የደረሰውን የጉዳት መጠንና ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች መጓዟን ገልጻለች።
በጉዟቸውም ‘በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያወጣው ሪፖርት አለ’ የሚል መረጃ ደርሷቸው ወደ ሥፍራው እንዳቀኑ ተናግራለች።
በአካባቢው የተገኙትን የጅምላ መቃብሮች በአካል እየተመለከቱ እንዲሁም ሕዝቡን እያናገሩ በነበሩበት ወቅት የአምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች የጋራ ሪፖርት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70959
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በህገወጥ መንገድ ሊጓጓዝ የነበረ አራት ሺህ 476 ሊትር በላይ የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሸቀጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ልዩ ስሙ ሞቢል ማደያ አካባቢ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከአይሱዙ መኪና ላይ ወደ ኮንቴይነር ተሸካሚ 2 ሎቤድ ተሽከርካሪዎች ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በመጫን ላይ ሳለ በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ሎቤድ መኪኖቹ ላይ በተደረገ ፍተሻም አራት ሺህ 476 ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት እንዲሁም 12 ኬሻ ቡና፣ 39 ካርቶን ፈሳሽ የምግብ ዘይት መገኘቱና ምርመራውም በሚመለከተው የህገ አካል እንደቀጠለ ጽ/ቤቱ አስታውቋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ሽፈራው አለሙ እንደገለፁት ህጋዊ ሂደታቸውን ያልተከተሉ ምርቶችን ከተለያዩ ህጋዊ ደረሰኝ ካላቸው ምርቶች ጋር በመቀላቀል ህጋዊ አስመስሎ ለማሳለፍ እየተደረገ የነበረውን ሂደት በአካባቢው የተመለከቱ ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ገልፀዋል።
ህብረተሰቡ መሰል ሕገወጥ ተግባራትን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኝ የህግ አካል ወይም በስልክ በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል የንግድ ክትትልና ቁጥጥር ቡድን መሪው አቶ ሽፈራው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️