Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ የመረጃ ተቋማት ሽብርተኝነትን ለመከላከል በትብብር እንደሚሠሩ ገለጹ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ የመረጃ ተቋማት ሽብርተኝነትን ለመከላከልና የቀጣናውን ዘላቂ ሠላም ለማስጠበቅ በትብብር እንደሚሠሩ ገለጹ።
የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ወታደራዊ መረጃ መድረክ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ትናንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል ብርሀኑ በቀለ፤ ምሥራቅ አፍሪካ የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ አሸባሪዎች፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እንዲሁም ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ያለበት መሆኑን ጠቅሰዋል። እነዚህ ሁሉ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ የጸጥታና የደህንነት ስጋቶችን ለመከላከል አገራት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ቀጣናውን እየፈተኑ ያሉ እንደ አልሻበብ፣ አይ ኤስ አይ ኤስና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሽብርተኞችን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71036
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ማኅበሩ በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰውን የውጭ ጫና በመሞገት ላበረከተው አስተዋጽዖ ምስጋና ተቸረው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለውን የውጭ ጫና በመሞገት ላበረከተው አስተዋጽዖ ከተለያዩ ተቋምት ምስጋና ተቸረው።
መንግስት በቀጣይም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በትብብር እንደሚሠራም ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ትላንትና ለቀድሞ የማኅበሩ አመራሮቹና አጋር አካላት የዕውቅና መርሐ ግብር አካሂዷል። በወቅቱ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ እንደገለጹት፤ ማኅበሩ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለውን የውጭ ጫና በመሞገት ረገድ ሙያዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ የሙያ ማኅበር ነው፡፡
ማኅበሩ ምዕራባውያን ሐሰተኛ መረጃን መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን ጫና በመሞገት ረገድ ያበረከተው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እንደ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገለፃ፤ የማኅበሩ ሙያዊ ስነምግባርን የጠበቀ ሙግት ኢትዮጵያ በውጭው ዓለም የተከፈተባትን የተቀናጀ ዘመቻ በመቋቋም ሂደቷ ውስጥ ሚናው የጎላ አለው፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር የሚያወጣቸውን መግለጫዎችና የሰጣቸውን ስልጠናዎች.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71053
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው የወረኢሉ ወረዳ አርሶ አደሮች ድጋፍ አደረገ
*********************
(ኢ ፕ ድ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በወረኢሉ ወረዳ በጦርነቱ ለተጎዱ በሶስት ቀበሌዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች 100 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ፣ 10 የውኃ መሳቢያ ጀነሬተሮችና 4 መለስተኛ ዘመናዊ ትራክተሮችን ድጋፍ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እንደገለጹት ወረኢሉ በታሪክ የምናውቀው፣ በአገሩ ክብር የማይደራደር ጀግና ህዝብ ነው።
በቅርቡ በተደረገው የህልውና ጦርነት ተጋድሎ በማድረግ ተዋግቷል፣ ጀብድም ፈጽሟል ብለዋል።
በወረዳው የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት የከፋ ቢሆንም ማህበረሰቡ ለሥራ ካለው ጥንካሬና የአካባቢው ሰብል አምራችነትን ታሳቢ በማድረግ ባንኩ ተገቢውን የግብዓትና ቴክኖሎጅ ድጋፍ እያደረገ ወረኢሉን ሞዴል አድርጎ ለማስቀጠል እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
የወረኢሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አይቸው፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ላደረገው ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ለመስኖም ሆነ ለመኸር እርሻ ምቹ መሬትና ውኃ ባለው ወረኢሉ ግብርናውን ለማዘመን ልማት ባንክ በጀመረው ሁኔታ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተግተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ም/ አስተዳዳሪ አቶ ተስፋ ዳኛው በበኩላቸው የአካባቢው ህዝብና አመራር ያገኘውን ዕድል በሚገባ ተጠቅሞ በዘርፉ ሥኬታማ ውጤት በማምጣት የባንኩን ጥረትና ድጋፍ በተግባር በማሳየት ለበለጠ ዕድገት እንዲነሳሳ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄዳ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድሩን አሰጀምራለች።
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ጨምሮ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሳራ ሀሰን፣ የጽ/ቤት ተወካይ አቶ ዮሐንስ እንግዳ፣ የሱማሌ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ መሐመድ አብዱራህማን እና የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ ም/ል ሐላፊ መሐመድ መኸዲ ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
"የአፈርና ውኃ ጥምረት ለግብርና ምርታማነት ወሳኝ ነው:: እንደ ሀገር ለውኃ እና ለአፈር አያያዝ አሠራሮቻችን ትኩረት ሰጥተን መሥራት አስፈላጊ ነው:: በዓለም በውኃ አቅርቦት ማነስና በአፈር መሸርሸር የተነሣ የመሬት መራቆት እየተባባሰ ነው። #አረንጓዴዐሻራ ጥረታችን የግብርና ምርታማነትን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲቻል በርካታና ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ነው። "

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ