የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው የወረኢሉ ወረዳ አርሶ አደሮች ድጋፍ አደረገ
*********************
(ኢ ፕ ድ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በወረኢሉ ወረዳ በጦርነቱ ለተጎዱ በሶስት ቀበሌዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች 100 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ፣ 10 የውኃ መሳቢያ ጀነሬተሮችና 4 መለስተኛ ዘመናዊ ትራክተሮችን ድጋፍ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እንደገለጹት ወረኢሉ በታሪክ የምናውቀው፣ በአገሩ ክብር የማይደራደር ጀግና ህዝብ ነው።
በቅርቡ በተደረገው የህልውና ጦርነት ተጋድሎ በማድረግ ተዋግቷል፣ ጀብድም ፈጽሟል ብለዋል።
በወረዳው የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት የከፋ ቢሆንም ማህበረሰቡ ለሥራ ካለው ጥንካሬና የአካባቢው ሰብል አምራችነትን ታሳቢ በማድረግ ባንኩ ተገቢውን የግብዓትና ቴክኖሎጅ ድጋፍ እያደረገ ወረኢሉን ሞዴል አድርጎ ለማስቀጠል እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
የወረኢሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አይቸው፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ላደረገው ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ለመስኖም ሆነ ለመኸር እርሻ ምቹ መሬትና ውኃ ባለው ወረኢሉ ግብርናውን ለማዘመን ልማት ባንክ በጀመረው ሁኔታ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተግተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ም/ አስተዳዳሪ አቶ ተስፋ ዳኛው በበኩላቸው የአካባቢው ህዝብና አመራር ያገኘውን ዕድል በሚገባ ተጠቅሞ በዘርፉ ሥኬታማ ውጤት በማምጣት የባንኩን ጥረትና ድጋፍ በተግባር በማሳየት ለበለጠ ዕድገት እንዲነሳሳ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄዳ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድሩን አሰጀምራለች።
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ጨምሮ የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሳራ ሀሰን፣ የጽ/ቤት ተወካይ አቶ ዮሐንስ እንግዳ፣ የሱማሌ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ መሐመድ አብዱራህማን እና የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ ም/ል ሐላፊ መሐመድ መኸዲ ተገኝተዋል።

"የአፈርና ውኃ ጥምረት ለግብርና ምርታማነት ወሳኝ ነው:: እንደ ሀገር ለውኃ እና ለአፈር አያያዝ አሠራሮቻችን ትኩረት ሰጥተን መሥራት አስፈላጊ ነው:: በዓለም በውኃ አቅርቦት ማነስና በአፈር መሸርሸር የተነሣ የመሬት መራቆት እየተባባሰ ነው። #አረንጓዴዐሻራ ጥረታችን የግብርና ምርታማነትን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲቻል በርካታና ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ነው። "
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ክፍል ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለጸ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ውድመት ደርሶበት የነበረው የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከረጂ ድርጅቶ በተገኘ ድጋፍ የቀዶ ጥገና አገልግሎት ክፍሉከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለጸ።
የሆስፒታሉ ስራ አሰኪያጅ ዶክተር ሀይማኖት አየለ ለፋና እንደተናገሩት፥ ሆስፒታሉ ከዚህ በፌት 8 የሚደርሱ የቀዶ ጥገና ማሽነሪዎች የነበሩት ቢሆንም ቡድኑ ባደረሰው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
የቀዶ ጥገና ክፍሉ አስፈላጊነት ላቅ ያለ መሆኑን የገለጹት ስራ አስኪያጇ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት 5 ሚሊየን እንዱሁም ዮ ኤስ ኤይድ ትራንስፎርም የተባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ባደረጉት ድጋፍ አሁን ላይ 7 ማሸነሪዎች የገጠማ ሰራቸው ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብለዋል።
አሁን ላይ ስራ የሚጀምረው የቀዶ ጥገና ክፍሉ ከዚህ በፌት አገልግሎት ይሰጥበት ከነበረው በተሻለ መልኩ የተደራጀ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሆስፒታሉ በመልሶ ግንባታ ሂደቱ በተሻለ መንገድ እየተገነባ ነው ያሉት ስራ አስኪያጇ የተገልጋዮች ማረፊያ ግንባታም እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በመልሶ ግንባታ ሂደቱ ረጂ ድርጅቶች እና ማህበረሰቡ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት ስራ አስኪያጇ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ከአምራች ኢንዱስትሪው ከ390 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
*******
(ኢ ፕ ድ)
ለአምራች ኢንዱስትሪው ትኩረት በመስጠት አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በመሳብ፣ ነባሮቹን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተሻለ የሀገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተሠራ መሆኑን የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ።
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከአምራች ኢንዱስትሪው ምርት ለውጪ ገበያ በማቅረብ 390 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። የእቅዱንም 87 በመቶ መፈፀሙን ነው የተገለጸው።
በዘርፉ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ እና ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ሀገሪቷ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ የሚመለከታቸው አካላት በትጋት ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል።
የኢትዮጵያን እናምርት በሚል መሪ ሐሳብ የሌሎች ውጤታማ ሀገራት ተሞክሮ ተቀምሮበት አምራች ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪና ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ሚኒስትሩ መናገራቸውን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል።
የፌዴራል እና የክልሎች የሥራ ኀላፊዎች በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ ነባር ኢንቨስትመንቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ምክር ቤቱ አገራዊ ምክክሩ አካታችና ግልጽ እንዲሆን በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አሳሰበ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
አገራዊ ምክክሩ አካታችና ግልጽ ሆኖ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅቡልነት እንዲኖረው በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሳሰበ።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሔል ባፌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አገራዊ ምክክሩ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውን ችግር በመፍታት የሁሉም ነገር መፍትሔ ይሆናል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። በመሆኑም ሂደቱ ግልጽና አካታች ሆኖ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘንድ ቅቡልነት እንዲያገኝ መሥራት ይገባል ።
አገራዊ ምክክሩ ገና ጅምር ዝግጅት ላይ ይገኛል ያሉት ዶክተር ራሔል፤ የተጠበቀውን ውጤት እንዲያመጣ ከአሁን ጀምሮ ለሁሉም ግልጽ ሆኖ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በንቃት የሚሳተፉበት እንዲሆን መሠራት እንዳለበት
https://www.press.et/?p=71094