Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ለበዓላቱ ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ መሆኑን የፊቤላ ዘይት ፋብሪካ አስታወቀ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

በመጪዎቹ የፋሲካ እና የኢድ አል ፈጥር በዓላት የዘይት እጥረት እንዳያጋጥም ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ መሆኑን የፊቤላ ዘይት ፋብሪካ ገለጸ፡፡

የፋብሪካው ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ለመጪዎቹ የፋሲካ እና የኢድ በዓላት ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ ነው፡፡

ድርጅቱ ለቀጣዮቹ በዓላት የምርት አቅርቦት እጥረት በገበያው እንዳይፈጠር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ ዘይት ለህብረተሰቡ በፍጥነት እንዲቀርብ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

በተለይ በእነዚህ ሁለት በዓላት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በበዓል ወቅት እንዳይቸገሩና የዘይት አቅርቦት እጥረት ገበያው ላይ እንዳይፈጠር ድርጅቱ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

እንደ አቶ በላይነህ ገለጻ፤ በዚህም በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ በሰባት ክልሎች እና በአንድ ከተማ አስተዳደር ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለህብረተሰቡ እንዲከፋፈል እየተደረገ ነው፡፡ የፋብሪካው ሠራተኞች በቀንና በምሽት እየሠሩ ነው። በየቀኑ ከ15 በላይ የዘይት ምርት የጫኑ ተሸከርካሪዎች ምርቱን እያጓጓዙ ይገኛሉ፡፡

በቀጣይም መንግሥት ዘይት ከወጭ እንዲገባ ለድርጅቱ የፈቀደውን የውጭ ምንዛሬ በመጠቀም ምርቱ ሳይቆራረጥ ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡

በየጊዜው አዋጭ የድፍድፍ ዘይት ዋጋን በማገናዘብ የዘይት ምርት በአገር ውስጥ ማምረት የጀመረው ፊቢላ የዘይት ፋብሪካ፤ በአምስት ዙር 116 ሺ ሜትሪክ ቶን ድፍድፍ ፓልም ዘይት ግዥ ፈጽሟል፡፡ በዚህም 75 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በማምረት ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መንግሥት በመደበው ኮታ መሰረት እየተከፋፈለ ነው ብለዋል፡፡

እንደ አገር ባለፉት ዓመታት ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዘይት ምርት ከውጭ ይገባ እንደነበር ያወሱት አቶ በላይነህ፤ ፋብሪካው ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት የቢዝነስ ጥናት በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል፡፡

የፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሆነው ሲሆን በ31 አከፋፋዮች አማካኝነት በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የዘይት ምርት ለህብረተሰቡ እየተሰራጨ ይገኛል ብለዋል፡፡

በጀማል ታመነ
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጋቢት ወር ብቻ ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል

👉 ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ780 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፤

👉 ግድቡ ከተጀመረ እስካሁን 16.5 ቢሊዮን ብር በላይ ከህዝብ ተሰብስቧል፣
********************************
(ኢ ፕ ድ)

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘው የበጀት አመት መጋቢት ወር ብቻ 108 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ደግሞ ለግድቡ ግንባታ ከ780 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።

ከተሰበሰበው ብር ውስጥ 399 ሚሊዮን የሚሆነው ከሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ የተገኘ ሲሆን፤ 243 ሚሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ደግሞ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢና ልገሳ መሆኑ ታውቋል።

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ በሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ 14 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር፤ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢ፤ እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ልገሳ ደግሞ አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል ።

በተመሳሳይ በ8100 A አጭር የፅሁፍ መልዕክት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 128 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

በወይንሸት ካሳ

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስሩ ከራሺያ ማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ኤቭጅኒ ፔትሮቭ ጋር በበየነ መረብ ውይይት አደረጉ
******************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮ-ራሺያን የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክ፣ የቴክኒካልና የንግድ ትብብር ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽንን በጋራ ሊቀመንበርነት የሚመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና የማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ኤቭጅኒ ፔትሮቭ በበየነ መረብ ውይይት አደረጉ።

ኢትዮጵያና ራሺያ በዲፌንስ፣ በትምህርት፣ በኢነርጂ፣ በጤና፣ በንግድና ኢንቨስትመንት በትብብር ይሰራሉ።

ሰባተኛው ኢትዮ-ራሺያ ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽን ውይይት ፒተርስበርግ ከተማ እ.አ.አ.በጥቅምት 2019 መካሄዱ ይታወቃል። ውይይቱም በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያሉትን የሁለትዮሽ የንግድ፣ የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክና የቴክኒካል ትብብሮችን ስለማጠናከር ነበር።

ኢትዮጵያና ራሺያ በትብብር ከሚሰሩባቸው ዘርፎች ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የራሺያ መንግስት አቶሚክ ኢነርጂ ትብብር እ.አ.አ. በጥቅምት 2019 የተፈረመ ሲሆን በኒውክለር ኢነርጂ ስልጠና ለመስጠት በሚያዚያ 15/ 2021 እ.አ.አ. የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
"የበጋ የስንዴ ምርታማነት በአማራ ክልል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ
“በሚዲያዎች ላይ የሚታየውን ጠቃሚ ያልሆነ ውድድር ማስቀረት ይኖርብናል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ውስጥ በየሰፈሩ ያሉ ሚዲያዎች ላይ የሚታየውን ጠቃሚ ያልሆነ ውድድር ማስቀረት ይኖርብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ‹‹አዲስ ፖለቲካዊ እይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ›› በሚል መሪ ሐሳብ ለብልጽግና ፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሰጡት ሥልጠና እንደገለጹት፤ በየሰፈሩ ያለ ሚዲያዎች ውስጥ ጥሩ ያልሆነ ውድድር አለ። ይህ ጠቃሚ ያልሆነ ውድድር ለማንም የማይበጅ በመሆኑ መስተካከል ይኖርበታል።

ለአብነት ኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክ /ኦቢኤን/ ብንመለከት አርሲ ውስጥ ስንዴ እንዴት ተመርቶ ምን ለውጥ አመጣ? የሚለውን ማሳየት ሲገባው፤ ጣቢያው ግን በየጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በዚህ ተገኙ ነገ በዚያ ብሎ ዜና ይሰራል ብለዋል።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንም በተመሳሳይ ብንመለከተው ስለጎርጎራና ስለአካባቢው ሥራዎች መናገር ሲገባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ብሎ ያወራል ያሉት ዶክተር ዐቢይ፤ አዲስ ቲቪም ሆነ ሌላው የፌዴራል ያልሆኑ በሌሎች የክልሎች መገናኛ ብዙሃን ላይ ችግሩ ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲስ ቲቪ ስለአዲስ አበባ መረጃዎች ቢያቀርብ፤ ኦሮሚያም፣ ደቡብም ሆነ አማራ ያሉ መገናኛ ብዙሃኑ በተመሳሳይ ስለክልላቸው ጉዳዮች ቢዘግቡ ውጤት ያመጡ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

ምክንያቱም ሰው ስለክልሉ መረጃ ሲፈልግ አማራጭ ካቀረብንለት...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71356

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች‼️
👉 ከ3 ሺህ በላይ የጤና ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል፣

👉 በሕወሓት ከወደሙ 42 ሆስፒታሎች 36 ያህሉ ወደሥራ ተመልሰዋል፣

👉 ከ708 ሚሊዮን በላይ ብር ለክልል ጤና ተቋማት ድጋፍ መቅረቡ ተገልጿል፣
*****
(ኢ ፕ ድ)

ግጭት በነበረባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች በአጠቃላይ ከ3 ሺህ በላይ የጤና ተቋማት ጉዳት እንደደረሰባቸው ባደረገው የጉዳት ዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ግጭቶች በነበሩባቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ጥፋት ከመድረሱ በተጨማሪ ሕዝብ የሚገለገልባቸው የጤና ተቋማት፤ የሕክምና ግብዓት ማከማቻዎች እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት መውደማቸው ተጠቁሟል።

የህክምና መሣሪያዎች እና ሌሎች ግብዓቶችንም አገልግሎት እንዳይሰጡ ከጥቅም ውጪ መደረጋቸውንና ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው መግለጫውን የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር አየለ ተሾመ ተናግረዋል።

ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች እንዲሁም የህክምና ግብዓት ማከማቻ ተቋማት ላይ በግጭቱ ምክንያት መጠነ ሰፊ ውድመት መድረሱ በተለይ ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን የመሰረታዊና ድንገተኛ ሕክምና...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71358

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ከመንግሥት በተረከበው ቦታ ላይ ሁለገብ የሕክምና ማዕከል ሊገነባ መሆኑን ድርጅቱ አስታወቀ
******
(ኢ ፕ ድ)
የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ከመንግሥት በነፃ በተረከበው ቦታ ላይ ሁለገብ የሕክምና ማዕከል ገንብቶ ለኩላሊት ታካሚዎች አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ።

በጎ አድራጎት ድርጅቱ ከኩላሊት ሕመምተኞች ጋር በተያያዘ ለሚያከናውናቸው ሥራዎች በነፃ ለተሰጠው 1ሺህ 410 ካሬ ሜትር መሬት ለመንግሥት ምስጋና አቅርቧል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሰለሞን አሰፋ እንደገለፁት፤ መንግሥት ለድርጅቱ በነፃ የሰጠው መሬት ላይ ሁለገብ ህንፃ በመገንባት የኩላሊት ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷል።

በተረከብነው ቦታ ላይ የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ለገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆን ህንፃ ለመገንባት አቅደናል። በአጠቃላይም ለህመምተኞች ሁለገብ ድጋፍ መስጠት የሚያስችል ማዕከል ለመገንባት ውጥን ተይዟል ብለዋል።

የሚገነባው ማዕከል በኢትዮጵያ የሚገኙና በችግር ውስጥ ያሉ በርካታ የኩላሊት ህመምተኞችን ለማገልገል ይረዳል ያሉት ዶክተር ሰለሞን፤ በተገኘው መሬት ላይ ከ17 እስከ 20 ወለል የሚደርስ ህንጻ በአምስት ዓመት ውስጥ ለመገንባት መታቀዱን ገልጸዋል።

እስከዚያው ድረስ ግን አፋጣኝ እርዳታ የሚሹ የኩላሊት ህመምተኞችን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71378

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
በከተማዋ ተግባራዊ የተደረገው ህጋዊ ካዳስተር ስርዓት አበረታች ውጤቶች አስገኝቷል
*****
(ኢ ፕ ድ)

በሀዋሳ ከተማ ህጋዊ የካዳስተር ስርዓት ተግባራዊ በመደረጉ በከተማዋ መሬት አጠቃቀም ላይ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለጸ፡፡ህጋዊ ካዳስተር ለከተሞች ዕድገትና ልማት ወሳኝ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አመልክቷል።

ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከሰሞኑ ህጋዊ ካዳስተርን ተግባራዊ ያደረጉ ከተሞችን ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ተዘዋውሮ በጎበኘበት ወቅት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ እንደገለጹት፤ በሀዋሳ ከተማ ህጋዊ የካዳስተር አሰራር ተግባራዊ በመደረጉ በከተማዋ መሬት አጠቃቀም ላይ አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ይህም ለከተማ ዕድገትና ልማት ወሳኝ ነው።

‹‹መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት ነው›› ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህን ውስን ሃብት ዘመናዊ በሆነ መንገድ በህጋዊ የካዳስተር ስርዓት መዝግቦ መያዝ ለከተሞች ዕድገትና ልማት የጎላ ሚና አለው ። ከተሞች ዘመናዊ ሆነው እንዲያድጉና እንዲለሙ ህጋዊ ካዳስተር ስርዓት ዝርጋታ አስፈላጊና ወሳኝ ነው ብለዋል።

የህጋዊ ካዳስተር ስርዓት ለከተሞች የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋጽኦ በመገንዘብ ካዳስተርን ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ የክልል ከተሞች መካከል ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቀዳሚ እንደሆነች ረዳት ፕሮፌሰሩ ገልጸው፤ በተለይም በ2013 እና 2014 ዓ.ም ብቁ በሆኑ አመራሮችና ባለሙያዎች አማካኝነት ህጋዊ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71377

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
መገናኛ ብዙሃን ለአገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
****
(ኢ ፕ ድ)

መገናኛ ብዙሃን ለአካታች አገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት ሰፊ ሽፋን ከመስጠት ጀምሮ ሙያዊ ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙሃን ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ትላንት ውይይት አካሂዷል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በመድረኩ ባደረጉት ገለጻ፤ መገናኛ ብዙሃን ትክክለኛውን የውይይት ጽንሰ ሀሳብ፣ የአጀንዳ ቀረጻ አካሄድ፣ የውይይት ሂደትና ትግበራ፣ በየቋንቋዎቻቸው ለሕዝቡ በየወቅቱ ተደራሽ በማድረግ የኮሚሽኑ አጋር እንዲሆኑና ለምክክሩ ስኬታማነት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ኮሚሽነሩ፤ ሚዲያ እውቀትን፣ እውነትን፣ ፍቅርን፣ ሠላምን፣ እድገትንና መተባበርን በቀላሉ በአፍ መፍቻ ቋንቋው በተዓማኒነት ለህዝብ የሚያደርስ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአካታች አገራዊ ምክክሩ ላይም ይህንኑ ኃላፊነት ለመወጣት ከኮሚሽኑ ጋር በአጋርነት እንዲሰራ ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የኮሚሽኑን ማቋቋሚያ አዋጅን፣ የምክክርን ጽንሰ ሀሳብና አስፈላጊነት በህትመት፣ በቴሌቪዥን፣ በራዲዮና በማህበራዊ ሚዲያ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ መገናኛ ብዙሃን ሲሰሩ እንደነበር ጠቅሰው፤ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይ ሚዲያው ህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ የማስተማር ሚናቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በአዋጅ ለኮሚሽኑ ተቆጥሮ የተሰጡ ኃላፊነትና ተግባር በአይነቱ ለአገሪቱ አዲስ ሲሆን፤ ለውጭውም ተምሳሌታዊ ነው ብለዋል።

አገራዊ ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት የሚዲያ አጋርነት ሚና አይተኬ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ለሕዝቡ ተደራሽ እንዲሆን እያንዳንዱ የሚዲያ ተቋም ከምክክር ኮሚሽኑ የሚዲያና ተግባቦት ዘርፍ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71362

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ