Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች‼️

👉 በለውጥ ጎዳና ላይ በመጓዝ ዴሞክራሲን የሚገነቡ ሀገራት በሁለት ጫፍ መካከል የሚቆም ፈተና ይገጥማቸዋል፤

👉 በአንዱ ዴሞክራሲያዊ ባህልን መገንባት ሲሆን ሌላ የሀገርንና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በጥብቅ ርምጃዎች ማስከበር ነው፣

👉 ዴሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት ስንነሣ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስከብሩ ጥብቅ ዕርምጃዎች በነጻነትና በመብት ስም እንዳይላሉ በሚዛን መንቀሳቀስ ይገባል፣

👉 ሁለቱን በሚዛን ለማከናወን ደግሞ የእያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ ፓርቲ፣ ቡድን፣ ወገን፣ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት፤ የህግና የጸጥታ ተቋማትም ሕገ መንግሥታዊና ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፣

👉 ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት ሕዝብና ሀገርን ሰላም የሚነሡ አካላትን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሕዝብን ሰላም የሚነሡና በተላላኪነት የሚያገለግሉ ቡድኖችን በጥናትና በመረጃ በመለየት አስፈላጊው ሁሉ ሕግ የማስከበር ርምጃ እንዲወሰድ የደኅንነት ምክር ቤቱ ወስኗል፣

👉 የምግብና ልዩ ልዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በሕገ ወጥመንገድ ምርት የሚያከማቹ፣ በኮንትሮባንድ መልክ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚያሾልኩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል፣

👉 ወላጆች ልጆቻችሁን፣ ሽማግሌዎች ወጣቶቻችሁን፣ የሃይማኖት አባቶች ምእመኖቻችሁን፣ የፓርቲ መሪዎች አባሎቻችሁን፣ የጎሳ መሪዎች ወገኖቻችሁን በመምከር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከግጭትና ከሽብር ራሱን አርቆ፣ ለሰላምና ለሀገር ደኅንነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ተጠይቋል፣
በወላይታ ሶዶ ከተማ በሀሰተኛ የብር ኖቶች ሊገበያይ የሞከረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በሚገኘው መርካቶ ገበያ 15 ሺህ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ሊገበያይ የሞከረው ግለሰብ ዛሬ እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማዋ ፖሊስ ዋና አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ ዘውዴ እንዳሉት፤ ግለሰቡ ከአንድ ሱቅ ዘይትና ስኳር እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ ምርቶች ከገዛ በኋላ ክፍያ ሊፈጽም ሲል ባለቤቱ ጥርጣሬ አድሮበት ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት 75 ባለ 200 ሐሰተኛ የብር ኖቶች እጁ ላይ መገኘቱን ገልጸዋል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡ በተለይ የበዓል ወቅት መሆኑን ተከትሎ መሠል ማጭበርበርና ህገወጥ ተግባራት የሚፈጠር መሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የኢዜአ ዘግቧል።

ሐሰተኛ የብር ኖቶችና መሰል ጥርጣሬ የሚፈጥሩ የወንጀል ድርጊቶች እንቅስቃሴ ሲመለከትም ለፀጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲጠቁምም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
አንድ ሺህ 149 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል
******
(ኢ ፕ ድ)

በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ አንድ ሺህ 149 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከተመላሾቹ ውስጥ 14 ህጻናትና አንድ ሺህ 135 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ12 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እና የቱርኩ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ
**********************
(ኢ ፕ ድ)

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከቱርክ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን ጋር በጋራ በትምህርት፣ በምርምር፣ በባህልና በቋንቋ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የትብብር ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሀመድ ኡስማን እና በኢትዮጵያ የቱርክ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን ተወካይ ሌቬንት ሳሂን ፈርመዋል።

በስምምነቱ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ሰራተኞች በቱርክ የድህረ ምረቃ ትምህርቶችን የመከታተል እድሉ ይኖራቸዋል ተብሏል።

ማዐሪፍ ፋውንዴሽን የተቋቋመው በሰው ልጆች የጋራ እውቀትና እሴቶች ላይ የተመሰረተ መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ አገልግሎቶችን ለመስጠት መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ልዑክ ከብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ ፕ ድ)

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ልዑክ በብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር የሁለትዮሽና የኢኮኖሚ ትብብር ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያየ።

በውይይቱም ለኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ጠቃሚ በሆኑ የሁለትዮሽና የኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

የሰብዓዊ አቅርቦት እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ሁሉ መደረግ ስላለበት ድጋፍ መወያየታቸውም ተገልጸዋል።

በተመሳሳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋርም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በባንኩ ፖርትፎሊዮ አፈጻጸም፣በአለም ባንክና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ በቅርቡ ዓለም ባንክ በግጭት ለተጎዱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን፣ በበኩላቸው መንግስት ቅድሚያ ለሰጣቸው የልማት ፕሮጀክቶችለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ የተመራው ልዑክ በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዋሺንግተን ዲሲ መግባቱ ይታወሳል።
በወላይታ ሶዶ ከተማ በሀሰተኛ የብር ኖቶች ሊገበያይ የሞከረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በሚገኘው መርካቶ ገበያ 15 ሺህ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ሊገበያይ የሞከረው ግለሰብ ዛሬ እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማዋ ፖሊስ ዋና አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ ዘውዴ እንዳሉት፤ ግለሰቡ ከአንድ ሱቅ ዘይትና ስኳር እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ ምርቶች ከገዛ በኋላ ክፍያ ሊፈጽም ሲል ባለቤቱ ጥርጣሬ አድሮበት ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት 75 ባለ 200 ሐሰተኛ የብር ኖቶች እጁ ላይ መገኘቱን ገልጸዋል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡ በተለይ የበዓል ወቅት መሆኑን ተከትሎ መሠል ማጭበርበርና ህገወጥ ተግባራት የሚፈጠር መሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የኢዜአ ዘግቧል።

ሐሰተኛ የብር ኖቶችና መሰል ጥርጣሬ የሚፈጥሩ የወንጀል ድርጊቶች እንቅስቃሴ ሲመለከትም ለፀጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲጠቁምም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio