Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ213 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ስድስት ስምምነቶችን ተፈራረመ
****
(ኢ ፕ ድ)

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ213 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሰድስት ስምምነቶችን ተፈራረመ፡፡

ከ41 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው በጦርነቱ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን እያስተናገዱ ላሉትና በዚህ ሳቢያ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ላይ ተግዳሮት ለገጠማቸው 4 ከተሞች ጎንደር ፣ባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃናና ሰመራ- ሎጊያ የሚውል ነው፡፡

ከስድስቱ ሁለቱ ስምምነቶች ለአራቱ ከተሞቹ 11 የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ መሳቢያ ፓምፖችና 9 ጀኔረተሮች ለማቅረብ ነው።

ቀሪ አራት ስምምነቶች፤ ሦስቱ ለ22 ከተሞች 44 ሞተር ሳይክሎችን፣ ማጓጓዝን ጨምሮ 10 ሰርፌስ ፖምፖቹን፣ ለ22 ከተሞች ቧንቧዎችና የባንቧ መገጣጠሚያዎችን ለማቅረብ የተደረጉ ናቸው፡፡

ቀሪው አንድ ስምምነት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የመጠጥ ውሃ ችግር ባለባቸው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጠምባሮና ዛላ ወረዳዎች የውሃ ምንጭ ፍለጋ፣ የአዋጭነት ጥናት ፣ ዝርዝር ዲዛይን ሥራና በጉድጓድ ቁፋሮ ወቅት የፕሮጀክት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥራን ለማከናወን የተደረገ ነው፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ለአራቱ ከተሞች የሚቀርቡት ጠላቂ ፓምፖች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ለተፈናቀሉ ዜጎች ውሃ በማቅረብ ረገድ በየከተሞቹ ያለውን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ይቀርባሉ።

ቀሪዎቹም ኮንትራቶች በስምምነቶቹ መሠረት ተግባራዊ እንዲደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ለተዋዋዮቹ ወገኖች አስፈላጊው ድጋፍና ትብብር እንደሚደርግ አመልክተዋል፡፡

ስምምነቶቹ ከሁለት እስከ 9 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ የኢሙ ጠቅላላ አስመጪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የድዛሚል ጀነራል ትሬዲንግ፣ ፀሜክስ ግሎባል ኢንተርፕራይዝና መታፈሪያ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ተወካዮችም በስምምነታቸው መሠረት በጊዜ ግዴታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

በስምምነቶቹ የተመለከተው ክፍያ ለሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራምና ለሁለተኛው የአንድ ቋት መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ከተያዘውን በብድር ከተገኘው ገንዘብ የሚሸፈን ነው፡፡
በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች‼️

👉 በለውጥ ጎዳና ላይ በመጓዝ ዴሞክራሲን የሚገነቡ ሀገራት በሁለት ጫፍ መካከል የሚቆም ፈተና ይገጥማቸዋል፤

👉 በአንዱ ዴሞክራሲያዊ ባህልን መገንባት ሲሆን ሌላ የሀገርንና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በጥብቅ ርምጃዎች ማስከበር ነው፣

👉 ዴሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት ስንነሣ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስከብሩ ጥብቅ ዕርምጃዎች በነጻነትና በመብት ስም እንዳይላሉ በሚዛን መንቀሳቀስ ይገባል፣

👉 ሁለቱን በሚዛን ለማከናወን ደግሞ የእያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ ፓርቲ፣ ቡድን፣ ወገን፣ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት፤ የህግና የጸጥታ ተቋማትም ሕገ መንግሥታዊና ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፣

👉 ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት ሕዝብና ሀገርን ሰላም የሚነሡ አካላትን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሕዝብን ሰላም የሚነሡና በተላላኪነት የሚያገለግሉ ቡድኖችን በጥናትና በመረጃ በመለየት አስፈላጊው ሁሉ ሕግ የማስከበር ርምጃ እንዲወሰድ የደኅንነት ምክር ቤቱ ወስኗል፣

👉 የምግብና ልዩ ልዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በሕገ ወጥመንገድ ምርት የሚያከማቹ፣ በኮንትሮባንድ መልክ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚያሾልኩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል፣

👉 ወላጆች ልጆቻችሁን፣ ሽማግሌዎች ወጣቶቻችሁን፣ የሃይማኖት አባቶች ምእመኖቻችሁን፣ የፓርቲ መሪዎች አባሎቻችሁን፣ የጎሳ መሪዎች ወገኖቻችሁን በመምከር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከግጭትና ከሽብር ራሱን አርቆ፣ ለሰላምና ለሀገር ደኅንነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ተጠይቋል፣
በወላይታ ሶዶ ከተማ በሀሰተኛ የብር ኖቶች ሊገበያይ የሞከረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በሚገኘው መርካቶ ገበያ 15 ሺህ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ሊገበያይ የሞከረው ግለሰብ ዛሬ እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማዋ ፖሊስ ዋና አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ ዘውዴ እንዳሉት፤ ግለሰቡ ከአንድ ሱቅ ዘይትና ስኳር እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ ምርቶች ከገዛ በኋላ ክፍያ ሊፈጽም ሲል ባለቤቱ ጥርጣሬ አድሮበት ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት 75 ባለ 200 ሐሰተኛ የብር ኖቶች እጁ ላይ መገኘቱን ገልጸዋል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡ በተለይ የበዓል ወቅት መሆኑን ተከትሎ መሠል ማጭበርበርና ህገወጥ ተግባራት የሚፈጠር መሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የኢዜአ ዘግቧል።

ሐሰተኛ የብር ኖቶችና መሰል ጥርጣሬ የሚፈጥሩ የወንጀል ድርጊቶች እንቅስቃሴ ሲመለከትም ለፀጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲጠቁምም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
አንድ ሺህ 149 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል
******
(ኢ ፕ ድ)

በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ አንድ ሺህ 149 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከተመላሾቹ ውስጥ 14 ህጻናትና አንድ ሺህ 135 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ12 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እና የቱርኩ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ
**********************
(ኢ ፕ ድ)

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከቱርክ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን ጋር በጋራ በትምህርት፣ በምርምር፣ በባህልና በቋንቋ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የትብብር ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሀመድ ኡስማን እና በኢትዮጵያ የቱርክ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን ተወካይ ሌቬንት ሳሂን ፈርመዋል።

በስምምነቱ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ሰራተኞች በቱርክ የድህረ ምረቃ ትምህርቶችን የመከታተል እድሉ ይኖራቸዋል ተብሏል።

ማዐሪፍ ፋውንዴሽን የተቋቋመው በሰው ልጆች የጋራ እውቀትና እሴቶች ላይ የተመሰረተ መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ አገልግሎቶችን ለመስጠት መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡