ማህበረሰቡ ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ከሚሸጡ ህገወጦች እንዲጠነቀቅ ፖሊስ አሳሰበ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በዓላት ተከትሎ የምግብ ምርቶችን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ከሚሸጡ ህገወጦች ማኀበረሰቡ ሊጠነቀቅ እንደሚገባው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ።
ከስቅለትና ፋሲካ በዓላት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎችና የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከል በቂ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መጪው የስቅለትና የፋሲካ በዓልን ተንተርሶ በርከት ያለው የማኀበረሰብ ክፍል የተለያዩ የምግብ ምርቶችንና ቁሳቁሶች ሲገበያይ ከሕገወጦች መጠንቀቅ አለበት።
በሕገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖች አጋጣሚዎችን በመጠቀም የተለያዩ የማታለል ተግባራቶችን ሊፈጽሙ ይችላሉ ያሉት ኮማንደሩ፤ በምግብ ውስጥ በተለይም በዘይት፣ ቅቤ፣ በርበሬና ሌሎች ምርቶች ውስጥ ባዕድ ነገሮችን ቀላቅሎ የሚሸጥ አጭበርባሪ ይኖራል ብለዋል።
እንዲህ ያሉ ወንጀሎች ከመፈጠራቸው በፊት ፖሊስ አስፈላጊውን የቅድመ መከላከል...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71391
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ህዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን በመደገፍ ሊሆን ይገባል-ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
******
(ኢ ፕ ድ)
ህዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከበር የተቸገሩትን በመርዳትና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል አሳሰቡ።
የጋምቤላ ፣የቤንሻንጉል፣ የምዕራብ ወለጋ፣የቄለም ወለጋና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል የትንሳኤን በዓል በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝበ ክርስቲያኑ አብሮነቱንና አንድነቱን በማጠናከር እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመረዳዳት በዓለ ትንሳኤውን ሊያከበር ይገባል።
በዓለ ትንሳኤ ክርስቶስ የአዳም ዘርን ነፃ ያወጣበት ክብረ በዓል በመሆኑ ህዝበ ክርስቲያኑ የዘረኝነትና የጎሰኝነት አስተሳሰቦችን በማስወገድ በዓለ ትንሳኤውን በአንድነትና በመደጋገፍ እንዲያሳልፈው አሳስበዋል።
እንደ ኢዜ ዘገባ በጋምቤላና በቤሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ህዝበ ክርስቲያን በዓሉን በፍቅርና እርስ በእርስ በመረዳዳት እንዲያከብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም በሀገሪቱ ለተጀመረው የሰላም ግንባታና የለውጥ ጉዞ ስኬታማነት ምዕመኑ የበኩሉን እንዲያበረክት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ጥሪ አቅርበዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ213 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ስድስት ስምምነቶችን ተፈራረመ
****
(ኢ ፕ ድ)
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ213 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሰድስት ስምምነቶችን ተፈራረመ፡፡
ከ41 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው በጦርነቱ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን እያስተናገዱ ላሉትና በዚህ ሳቢያ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ላይ ተግዳሮት ለገጠማቸው 4 ከተሞች ጎንደር ፣ባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃናና ሰመራ- ሎጊያ የሚውል ነው፡፡
ከስድስቱ ሁለቱ ስምምነቶች ለአራቱ ከተሞቹ 11 የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ መሳቢያ ፓምፖችና 9 ጀኔረተሮች ለማቅረብ ነው።
ቀሪ አራት ስምምነቶች፤ ሦስቱ ለ22 ከተሞች 44 ሞተር ሳይክሎችን፣ ማጓጓዝን ጨምሮ 10 ሰርፌስ ፖምፖቹን፣ ለ22 ከተሞች ቧንቧዎችና የባንቧ መገጣጠሚያዎችን ለማቅረብ የተደረጉ ናቸው፡፡
ቀሪው አንድ ስምምነት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የመጠጥ ውሃ ችግር ባለባቸው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጠምባሮና ዛላ ወረዳዎች የውሃ ምንጭ ፍለጋ፣ የአዋጭነት ጥናት ፣ ዝርዝር ዲዛይን ሥራና በጉድጓድ ቁፋሮ ወቅት የፕሮጀክት አስተዳደርና ቁጥጥር ሥራን ለማከናወን የተደረገ ነው፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ለአራቱ ከተሞች የሚቀርቡት ጠላቂ ፓምፖች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ለተፈናቀሉ ዜጎች ውሃ በማቅረብ ረገድ በየከተሞቹ ያለውን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ይቀርባሉ።
ቀሪዎቹም ኮንትራቶች በስምምነቶቹ መሠረት ተግባራዊ እንዲደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ለተዋዋዮቹ ወገኖች አስፈላጊው ድጋፍና ትብብር እንደሚደርግ አመልክተዋል፡፡
ስምምነቶቹ ከሁለት እስከ 9 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ የኢሙ ጠቅላላ አስመጪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የድዛሚል ጀነራል ትሬዲንግ፣ ፀሜክስ ግሎባል ኢንተርፕራይዝና መታፈሪያ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ተወካዮችም በስምምነታቸው መሠረት በጊዜ ግዴታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡
በስምምነቶቹ የተመለከተው ክፍያ ለሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራምና ለሁለተኛው የአንድ ቋት መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ከተያዘውን በብድር ከተገኘው ገንዘብ የሚሸፈን ነው፡፡

በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች‼️
👉 በለውጥ ጎዳና ላይ በመጓዝ ዴሞክራሲን የሚገነቡ ሀገራት በሁለት ጫፍ መካከል የሚቆም ፈተና ይገጥማቸዋል፤
👉 በአንዱ ዴሞክራሲያዊ ባህልን መገንባት ሲሆን ሌላ የሀገርንና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በጥብቅ ርምጃዎች ማስከበር ነው፣
👉 ዴሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት ስንነሣ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስከብሩ ጥብቅ ዕርምጃዎች በነጻነትና በመብት ስም እንዳይላሉ በሚዛን መንቀሳቀስ ይገባል፣
👉 ሁለቱን በሚዛን ለማከናወን ደግሞ የእያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ ፓርቲ፣ ቡድን፣ ወገን፣ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት፤ የህግና የጸጥታ ተቋማትም ሕገ መንግሥታዊና ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፣
👉 ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሠራጨት ሕዝብና ሀገርን ሰላም የሚነሡ አካላትን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሕዝብን ሰላም የሚነሡና በተላላኪነት የሚያገለግሉ ቡድኖችን በጥናትና በመረጃ በመለየት አስፈላጊው ሁሉ ሕግ የማስከበር ርምጃ እንዲወሰድ የደኅንነት ምክር ቤቱ ወስኗል፣
👉 የምግብና ልዩ ልዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በሕገ ወጥመንገድ ምርት የሚያከማቹ፣ በኮንትሮባንድ መልክ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚያሾልኩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል፣
👉 ወላጆች ልጆቻችሁን፣ ሽማግሌዎች ወጣቶቻችሁን፣ የሃይማኖት አባቶች ምእመኖቻችሁን፣ የፓርቲ መሪዎች አባሎቻችሁን፣ የጎሳ መሪዎች ወገኖቻችሁን በመምከር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከግጭትና ከሽብር ራሱን አርቆ፣ ለሰላምና ለሀገር ደኅንነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ተጠይቋል፣

በወላይታ ሶዶ ከተማ በሀሰተኛ የብር ኖቶች ሊገበያይ የሞከረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በሚገኘው መርካቶ ገበያ 15 ሺህ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ሊገበያይ የሞከረው ግለሰብ ዛሬ እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
የከተማዋ ፖሊስ ዋና አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ ዘውዴ እንዳሉት፤ ግለሰቡ ከአንድ ሱቅ ዘይትና ስኳር እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ ምርቶች ከገዛ በኋላ ክፍያ ሊፈጽም ሲል ባለቤቱ ጥርጣሬ አድሮበት ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት 75 ባለ 200 ሐሰተኛ የብር ኖቶች እጁ ላይ መገኘቱን ገልጸዋል።
ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አስታውቀዋል።
ህብረተሰቡ በተለይ የበዓል ወቅት መሆኑን ተከትሎ መሠል ማጭበርበርና ህገወጥ ተግባራት የሚፈጠር መሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የኢዜአ ዘግቧል።
ሐሰተኛ የብር ኖቶችና መሰል ጥርጣሬ የሚፈጥሩ የወንጀል ድርጊቶች እንቅስቃሴ ሲመለከትም ለፀጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲጠቁምም መልዕክት አስተላልፈዋል።