"ዛሬ ከጀግኖች የማዕከላዊ ዕዝ ብሔራዊ ኃይላች አባላት ጋር ጊዜ በማሳለፌ ክብር ይሰማኛል። ብዙዎች ሀገራችንን ለማገልገልና ታላቋን #ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሲሉ መሥዋዕትነት ከፍለዋል። መሥዋዕትነት፣ ትጋት፣ ዕውቀት፣ ርኅራኄና አንድነት ሀገራችንን ልትደርስበት ወደሚገባት ከፍታ ያሻግሯታል።"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች መልዕክት‼️
የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ለትንሣኤ በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በዓሉን ስናከብር በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመርዳትና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል።
👉 የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት ላለፉት ሁለት ወራት በጾም ጸሎት ለሀገር ሰላምና በረከት በመለመን እንዲሁም የክርስትና አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት መልካም ነገሮችን በመፈጸም ለቆዩና በነገው እለት የትንሳኤ በአልን ለሚያከብሩ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ ብለዋል።
በዓሉ ሲከበር የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘው መሰረትና በተለመደው ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ ባህልና እሴታችን መሰረት በተለያየ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖችን አስበን ያለንን በማካፈል፣ ማእዳችንን በማጋራት ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች በድርቅ፣ በጦርነትና በተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡና በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም ብለዋል፡፡
በታላቁ የረመዳን የጾም ወር ላይ የእስልምና እምነት ተከታዮችም የጀመሯቸውን መልካም ተግባራት በማከናወን እንዲያሳልፉ ጠይቀዋል፡፡
👉 የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሞትን አሸንፎ ከመነሣት፣ ከመቃብርና ጨለማ ከመውጣት፣ ከሲኦልና እስራት ከመፈታት የሚበልጥ ምንም ደስታ ሊኖር አይችልም፤ ትንሳኤም በአዳም ላይ የተፈረደው ፍርድ ሁሉ ተደምስሶ፣ ፍጹም ነፃነት፣ የማይለወጥ ደስታ የተገኝበት ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት በጦርነት እና በተለያዩ ግጭቶች ምክንያት ተፈናቅለው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖች በዓሉን በአብሮነትና በደስታ እንዲያሳልፉ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይም የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም የምናደርገው ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ኅብረተሰቡ የትንሣኤ በዓልን ሲያከብር ወገኖችን በመደገፍና ማዕድ በማጋራት ወገናዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
👉 የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በመልዕክታቸው የትንሳዔ በዓል የላቀ ፍቅርን፣አክብሮትን ዝቅ በማለት የላቀ ከፍታ እንዳለ የምንረዳበት በዓል ነው፡፡ በዓሉን ስናከብር በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመርዳትና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል። በማይመች ሁኔታ ላይ ሆነው በዓልን የሚያሳልፉ ወገኖቻችንን አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል ብለዋል።
ህብረታችንን ካጠናከርን እጅግ የገዘፈ የመሰለንን ችግር በቀላሉ መሻገር እንችላለን ለዚህ ደግሞ የመላው ህዝባችንን የላቀ ድጋፍ ይጠይቃል በማለት ተናግረዋል። መንግስት የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እያካሄደ ያለው ጥረት ሊጠናከር ይገባል ያሉት ርእሰ መስተዳደሩ፤ በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚስተዋለውን ህገ ወጥነትን በመከላከል ረገድ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
👉 ሲዳማ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ እየሱስ ክርስቶስ በቀራኒዮ መሰቀል ላይ ተሰቅሎ ዘላለማዊ የሞት መጋረጃን ከማስወገዱም ባሻገር በምድር ላለን ፍቅርን፣ ትህትናን፣ መልካምነትንና ለሌሎች ስንል መስዋዕትነት መክፈልን አስተምሮናል። መላው የክርስትና እምነት ተከታይ ምንም የሌላቸውን ወገኖችን በመርዳት፤ ጠዋሪ የሌላቸውን አረጋዊያን በመደገፍ ፤ ያላው ለሌለው በማካፈል በዓሉን ማክበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
ለጠላቶቻችን እኩይ ሴራ ሳንበረከክና ሳንበገር የሐገራችንን ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ ከምን ጊዜውም በላይ አንድነታችንን አጠናክረን ክርስቶስ ባስተማረን ፍቅር ከዘር ጥላቻና ፅንፈኝነት ተላቀን የሐገራችንን ሰላም በጋራ አናስጠብቅ ሲሉም ገልፀዋል።
👉 የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በመልዕክታቸው በዓሉ ስለሰው ልጆች ፍቅር በመስቀል ላይ በተከፈለ ዋጋ የተገኘ መሆኑን በማስታወስ ያለንን ማህበራዊ አንድነታችንን በማጠናከር፣ በመዋደድና በመከባበር ማክበር ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡
ያለንን ማካፈል የባህላችን አንድ አካል ሆኖ የዘለቀ ዕሴት ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ለአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ፍቅርና ክብርን በማሳየት በዓሉን እንደ አንድ ቤተሰብ በመሆን በጋራ ማክበር ይገባልም ብለዋል ፡፡
ክልሉ በቅርቡ የተመሠረተ ክልል ስለሆነ ሁሉ አቀፍ ዕድገት ለማስመዝገብ ከመቼውም በላቀ መትጋት ስለሚጠበቅንን በመተባበርና በጋራ መንቀሳቀስ ያስፈልገናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
👉 የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ ህዝበ ክርስቲያኑ በፆም ወቅት ያሳየውን መልካም ተግባራትን በበዓሉም ወቅት በማጎልበት ህሙማንን በመጠየቅ ወገናዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ይባል ብለዋል በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው፡፡
በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማስከበርና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ህዝቡ የበኩሉን አስተዋጾኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል፡፡ በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል።
👉 የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጆሀር ባስተላለፉት ትንሳኤ ለሰው ልጆች ሁሉ ከመከራ የመነሳት የተስፋ ምልክት ተደርጎ የሚወሰድ በመሆኑ እኛም አሁን የገጠሙንን የውስጥና የውጭ ችግሮች ተቋቁመን ፈተናዎችን በፅናት ለመሻገር መነሳት ይኖርብናል። አሁን ላይ የገጠሙንን ፈተናዎች አልፈን የምንሻገር እንድንሆን ተስፋን የምንሰንቀበት በዓል ነው፡፡ ፍቅርንና አንድነትን በመስበክ ማክበር ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።

በሶማሌ ክልል ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጠ
******
(ኢ ፕ ድ )
በሶማሌ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ9 ቢሊየን ብር የሚበልጥ ካፒታል ላስመዘገቡ 381 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ዘይነባ ሀጂ አድን እንደገለጹት የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የተሰጠው ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ነው።
ባለሃብቶቹ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ትራስፖርት፣ አገልግሎትና ሌሎችም የልማት ዘርፎች በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ለመሰማራት የሚያስችል እቅድ አቅርበው እንደፀደቀላቸው ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅትም የፕሮጀክቶቻቸው ግንባታና ሂደት በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ወይዘሮ ዘይነባ፣ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ ከ14 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
የክልሉ መንግስት በከተሞች የመንገድ መሰረተ ልማት ማስፋፋቱ በተለይ ጅግጅጋ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድ መገንባቱ፣ ከምን ጊዜም በላይ ሰላምና መረጋጋት በክልሉ መኖሩ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስረድተዋል።
ባለሃብቶቹ በገቡት ውል መሰረት እቅዶቻቸውን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነውም ብለዋል።
የክልሉ መንግስት ባለሃብቶች ራሳቸውን እና ማህበረሰቡን እንዲጠቅሙ የኢንቨስትመንት ስራዎች ፈቃድ ከመስጠት ጀምሮ የተለያዩ ማበረታቻዎች እንዲያገኙ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

"በዓሉን በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍና በመንከባከብ ማሳለፍ ይገባል" - የሃይማኖት አባቶች
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ፣ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ፣ ከስደት የተመለሱና ህመምተኞችን በማገዝ፣ በማጽናናትና ችግራቸውንም በመካፈል ሊሆን እንደሚገባም የሃይማኖት አባቶች አሳስበዋል፡፡
የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት የሃይማኖት አባቶቹ የእንኳን አደረሳችሁ መከልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን ይገባል፡፡ ጥላቻን በፍቅር፣ ቂም በቀልን በይቅርታ፣ ሐዘንን በደስታ፣ ቅራኔን በሰላም፣ ተስፋ መቁረጥን በጽናትና በክርስቲያዊ ተስፋ ማሸነፍ ይገባል፤ ለኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ እንዲሆን መጸለይ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ለታመሙ ምህረትን፣ ተፈናቅለው በስደት ላይ ለሚገኙትም ወደ ቄያቸው መመለስ እንዲሆን፣ በጦርነትና በግጭት ቀጠናዎች ለሚገኙ ወገኖችም ሰላም እንዲሰፍን ተመኝተዋል፡፡ የትንሳኤ በዓል የደስታ፣ የፍቅር፣ የፍስሃ፣ የይቅርታና የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
አብዛኛው ሰው በአንደበታቸው የሰላም መልዕክት እየተናገረ በድርጊቱ ለሰላም መናጋት ምክንያት ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ ልዩነቶችን በመታገስ መቻቻልና የሰላም ተምሳሌት መሆን እንደሚገባቸውም መክረዋል፡፡
በዘላለም ግዛው

74 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ መቀሌ ከተማ እየተጓዙ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ የገባውን ቃል በማክበር ምቹ የሰብአዊ ርዳታ ማጓጓዣ ሁኔታን ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል።
በዚህም መሠረት በሶስተኛው ዙር በዛሬው እለት 74 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እየተጓዙ ነው።
ከእነዚህ ውስጥ 6 ተሽከርካሪዎች ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ናቸው።
መንግስት ከአለም የምግብ ፕሮግራም እና ሌሎችም አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፍ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።
የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸጋሪ ሁኔታ ወስጥ የሚገኙት የክልሉ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ወራሪው ሃይል አሁንም ከያዛቸው የአፋርና አማራ ክልል አካባቢዎች እንዲወጣና ምቹ የእርዳታ ማስተላለፊያ መስመርን መዘርጋት እንዲቻል እንዲሁም ከሚነዘቸው የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎች እንዲቆጠብ እና እስከአሁን ድረስ ያልተመለሱ 1025 ተሽከርካሪዎች በፍጥነት እንዲመለሱ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ከተማ አስተዳደሩ በሕገ ወጥ ዕርድ ምክንያት በየዓመቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ብር ያጣል
👉 ከ90 በመቶ በላይ በግና ፍየሎች በሕገወጥ መንገድ ታርደው ሥጋቸው ለገበያ ይቀርባል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በሕገ ወጥ ዕርድ ሥጋን ለገበያ የማቅረብ ተግባር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየዓመቱ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር እንደሚያጣ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ገለጸ።
ከ25 እስከ 35 በመቶ የሚሆኑ የዳልጋ ከብቶች እና ከ90 እስከ 94 በመቶ የሚሆኑት በግና ፍየሎች በሕገ ወጥ መንገድ ታርደው ለገበያ ይቀርባሉም ተብሏል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰኢድ እንድሪስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሕገ ወጥ ዕርድ ምክንያት መንግሥት ከግብር፣ ከተረፈ ምርት እና ከቆዳና ሌጦ ማግኘት የሚገባውን 1 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር በየዓመቱ ያጣል።
በመዲናዋ 246 የተለያዩ ቦታዎች የሕገ ወጥ ዕርድ እንደሚከናወንባቸው በዳሰሳ ጥናት መረጋገጡንና በእነዚህና በሌሎች ቦታዎች እየተካሄዱ ያሉ ሕገወጥ ዕርዶች ኀብረተሰቡ ላይ ከሚያስከትሉት የጤና ችግር ባለፈ ከተማ አስተዳደሩን ገቢ እያሳጡት ይገኛሉ ተብሏል።
ሕገ ወጥ ዕርድ ከቄራ ውጪ ታርዶ ለገበያ የሚቀርብ ማንኛውም የእንስሳት ዕርድ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71529