Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በሶማሌ ክልል ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጠ
******
(ኢ ፕ ድ )

በሶማሌ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ9 ቢሊየን ብር የሚበልጥ ካፒታል ላስመዘገቡ 381 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ዘይነባ ሀጂ አድን እንደገለጹት የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የተሰጠው ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ነው።

ባለሃብቶቹ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ትራስፖርት፣ አገልግሎትና ሌሎችም የልማት ዘርፎች በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ለመሰማራት የሚያስችል እቅድ አቅርበው እንደፀደቀላቸው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም የፕሮጀክቶቻቸው ግንባታና ሂደት በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ወይዘሮ ዘይነባ፣ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ ከ14 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት በከተሞች የመንገድ መሰረተ ልማት ማስፋፋቱ በተለይ ጅግጅጋ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድ መገንባቱ፣ ከምን ጊዜም በላይ ሰላምና መረጋጋት በክልሉ መኖሩ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስረድተዋል።

ባለሃብቶቹ በገቡት ውል መሰረት እቅዶቻቸውን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነውም ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ባለሃብቶች ራሳቸውን እና ማህበረሰቡን እንዲጠቅሙ የኢንቨስትመንት ስራዎች ፈቃድ ከመስጠት ጀምሮ የተለያዩ ማበረታቻዎች እንዲያገኙ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"በዓሉን በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍና በመንከባከብ ማሳለፍ ይገባል" - የሃይማኖት አባቶች
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ፣ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ፣ ከስደት የተመለሱና ህመምተኞችን በማገዝ፣ በማጽናናትና ችግራቸውንም በመካፈል ሊሆን እንደሚገባም የሃይማኖት አባቶች አሳስበዋል፡፡

የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት የሃይማኖት አባቶቹ የእንኳን አደረሳችሁ መከልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን ይገባል፡፡ ጥላቻን በፍቅር፣ ቂም በቀልን በይቅርታ፣ ሐዘንን በደስታ፣ ቅራኔን በሰላም፣ ተስፋ መቁረጥን በጽናትና በክርስቲያዊ ተስፋ ማሸነፍ ይገባል፤ ለኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ እንዲሆን መጸለይ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ለታመሙ ምህረትን፣ ተፈናቅለው በስደት ላይ ለሚገኙትም ወደ ቄያቸው መመለስ እንዲሆን፣ በጦርነትና በግጭት ቀጠናዎች ለሚገኙ ወገኖችም ሰላም እንዲሰፍን ተመኝተዋል፡፡ የትንሳኤ በዓል የደስታ፣ የፍቅር፣ የፍስሃ፣ የይቅርታና የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

አብዛኛው ሰው በአንደበታቸው የሰላም መልዕክት እየተናገረ በድርጊቱ ለሰላም መናጋት ምክንያት ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ ልዩነቶችን በመታገስ መቻቻልና የሰላም ተምሳሌት መሆን እንደሚገባቸውም መክረዋል፡፡

በዘላለም ግዛው
74 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ መቀሌ ከተማ እየተጓዙ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ የገባውን ቃል በማክበር ምቹ የሰብአዊ ርዳታ ማጓጓዣ ሁኔታን ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል።

በዚህም መሠረት በሶስተኛው ዙር በዛሬው እለት 74 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እየተጓዙ ነው።

ከእነዚህ ውስጥ 6 ተሽከርካሪዎች ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ናቸው።

መንግስት ከአለም የምግብ ፕሮግራም እና ሌሎችም አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፍ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸጋሪ ሁኔታ ወስጥ የሚገኙት የክልሉ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ወራሪው ሃይል አሁንም ከያዛቸው የአፋርና አማራ ክልል አካባቢዎች እንዲወጣና ምቹ የእርዳታ ማስተላለፊያ መስመርን መዘርጋት እንዲቻል እንዲሁም ከሚነዘቸው የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎች እንዲቆጠብ እና እስከአሁን ድረስ ያልተመለሱ 1025 ተሽከርካሪዎች በፍጥነት እንዲመለሱ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ከተማ አስተዳደሩ በሕገ ወጥ ዕርድ ምክንያት በየዓመቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ብር ያጣል

👉 ከ90 በመቶ በላይ በግና ፍየሎች በሕገወጥ መንገድ ታርደው ሥጋቸው ለገበያ ይቀርባል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በሕገ ወጥ ዕርድ ሥጋን ለገበያ የማቅረብ ተግባር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየዓመቱ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር እንደሚያጣ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ገለጸ።

ከ25 እስከ 35 በመቶ የሚሆኑ የዳልጋ ከብቶች እና ከ90 እስከ 94 በመቶ የሚሆኑት በግና ፍየሎች በሕገ ወጥ መንገድ ታርደው ለገበያ ይቀርባሉም ተብሏል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰኢድ እንድሪስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሕገ ወጥ ዕርድ ምክንያት መንግሥት ከግብር፣ ከተረፈ ምርት እና ከቆዳና ሌጦ ማግኘት የሚገባውን 1 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር በየዓመቱ ያጣል።

በመዲናዋ 246 የተለያዩ ቦታዎች የሕገ ወጥ ዕርድ እንደሚከናወንባቸው በዳሰሳ ጥናት መረጋገጡንና በእነዚህና በሌሎች ቦታዎች እየተካሄዱ ያሉ ሕገወጥ ዕርዶች ኀብረተሰቡ ላይ ከሚያስከትሉት የጤና ችግር ባለፈ ከተማ አስተዳደሩን ገቢ እያሳጡት ይገኛሉ ተብሏል።

ሕገ ወጥ ዕርድ ከቄራ ውጪ ታርዶ ለገበያ የሚቀርብ ማንኛውም የእንስሳት ዕርድ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71529

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
“እውነተኛ እርካታና ደስታ የሚገኘው በዓሉን ከችግረኞች ጋር ስናሳልፍ ነው” – መምህር አባ ዳዊት አማረ
*******
(ኢ ፕ ድ)

እውነተኛ የበዓል እርካታና ደስታ የምናገኘው የፋሲካውን በዓል ከችግረኞች ጋር ማሳለፍ ስንችል ነው ሲሉ የወልቃይት ጠገዴ የሰላም አምባሳደርና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ሰላም መድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን የቁጥጥር ኃላፊ መምህር አባ ዳዊት አማረ ገለጹ።

መምህር አባ ዳዊት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት፤ የዛሬውን የፋሲካ በዓል ከተቸገሩ ሰዎች፣ ከተፈናቀሉ ዜጎችና ከስደት ተመላሾች ጋር በመሆን ብናከብረው ትልቅ ደስታ እናገኛለን።

በልተን ያልጠገብነው፤ ተኝተን ያላረፍነው ያለንን ማካፈል ባለመቻላችን ነው ያሉት መምህሩ፤ በልተን የምንጠግበው፤ ተኝተንም የምናርፈው ደግሞ ያለንን ማካፈል ስንችል በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ከተቸገሩ ሰዎች፣ ከተፈናቀሉ ዜጎች እና ከስደት ተመላሾች ጋር በመሆን ማክበር እንደሚገባው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዛሬ የምናከብረው የፋሲካ በዓል በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት አባ ዳዊት፤ ፋሲካ ማለት መሻገር በመሆኑ ከመገዳደል፣ ከዘረኝነት፣ ከምቀኝነትና ወንድሞቻችንን ከማሳደድ በመሻገር...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71527

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ