Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
74 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ መቀሌ ከተማ እየተጓዙ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ የገባውን ቃል በማክበር ምቹ የሰብአዊ ርዳታ ማጓጓዣ ሁኔታን ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል።

በዚህም መሠረት በሶስተኛው ዙር በዛሬው እለት 74 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ እየተጓዙ ነው።

ከእነዚህ ውስጥ 6 ተሽከርካሪዎች ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ናቸው።

መንግስት ከአለም የምግብ ፕሮግራም እና ሌሎችም አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፍ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸጋሪ ሁኔታ ወስጥ የሚገኙት የክልሉ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ወራሪው ሃይል አሁንም ከያዛቸው የአፋርና አማራ ክልል አካባቢዎች እንዲወጣና ምቹ የእርዳታ ማስተላለፊያ መስመርን መዘርጋት እንዲቻል እንዲሁም ከሚነዘቸው የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎች እንዲቆጠብ እና እስከአሁን ድረስ ያልተመለሱ 1025 ተሽከርካሪዎች በፍጥነት እንዲመለሱ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ከተማ አስተዳደሩ በሕገ ወጥ ዕርድ ምክንያት በየዓመቱ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ብር ያጣል

👉 ከ90 በመቶ በላይ በግና ፍየሎች በሕገወጥ መንገድ ታርደው ሥጋቸው ለገበያ ይቀርባል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በሕገ ወጥ ዕርድ ሥጋን ለገበያ የማቅረብ ተግባር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየዓመቱ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር እንደሚያጣ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ገለጸ።

ከ25 እስከ 35 በመቶ የሚሆኑ የዳልጋ ከብቶች እና ከ90 እስከ 94 በመቶ የሚሆኑት በግና ፍየሎች በሕገ ወጥ መንገድ ታርደው ለገበያ ይቀርባሉም ተብሏል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰኢድ እንድሪስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሕገ ወጥ ዕርድ ምክንያት መንግሥት ከግብር፣ ከተረፈ ምርት እና ከቆዳና ሌጦ ማግኘት የሚገባውን 1 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር በየዓመቱ ያጣል።

በመዲናዋ 246 የተለያዩ ቦታዎች የሕገ ወጥ ዕርድ እንደሚከናወንባቸው በዳሰሳ ጥናት መረጋገጡንና በእነዚህና በሌሎች ቦታዎች እየተካሄዱ ያሉ ሕገወጥ ዕርዶች ኀብረተሰቡ ላይ ከሚያስከትሉት የጤና ችግር ባለፈ ከተማ አስተዳደሩን ገቢ እያሳጡት ይገኛሉ ተብሏል።

ሕገ ወጥ ዕርድ ከቄራ ውጪ ታርዶ ለገበያ የሚቀርብ ማንኛውም የእንስሳት ዕርድ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71529

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
“እውነተኛ እርካታና ደስታ የሚገኘው በዓሉን ከችግረኞች ጋር ስናሳልፍ ነው” – መምህር አባ ዳዊት አማረ
*******
(ኢ ፕ ድ)

እውነተኛ የበዓል እርካታና ደስታ የምናገኘው የፋሲካውን በዓል ከችግረኞች ጋር ማሳለፍ ስንችል ነው ሲሉ የወልቃይት ጠገዴ የሰላም አምባሳደርና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ሰላም መድሐኒያለም ቤተ ክርስትያን የቁጥጥር ኃላፊ መምህር አባ ዳዊት አማረ ገለጹ።

መምህር አባ ዳዊት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት፤ የዛሬውን የፋሲካ በዓል ከተቸገሩ ሰዎች፣ ከተፈናቀሉ ዜጎችና ከስደት ተመላሾች ጋር በመሆን ብናከብረው ትልቅ ደስታ እናገኛለን።

በልተን ያልጠገብነው፤ ተኝተን ያላረፍነው ያለንን ማካፈል ባለመቻላችን ነው ያሉት መምህሩ፤ በልተን የምንጠግበው፤ ተኝተንም የምናርፈው ደግሞ ያለንን ማካፈል ስንችል በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን ከተቸገሩ ሰዎች፣ ከተፈናቀሉ ዜጎች እና ከስደት ተመላሾች ጋር በመሆን ማክበር እንደሚገባው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዛሬ የምናከብረው የፋሲካ በዓል በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት አባ ዳዊት፤ ፋሲካ ማለት መሻገር በመሆኑ ከመገዳደል፣ ከዘረኝነት፣ ከምቀኝነትና ወንድሞቻችንን ከማሳደድ በመሻገር...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71527

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለ230 አቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣ አደረጉ
****
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለጎዳና ተዳዳሪዎች፣ ጧሪ ለሌላቸው አቅመ ደካማ አዛውንቶችና ቤተሰብ ለሌላቸው ህጻናት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የምሳ ግብዣ አድርገዋል፡፡

በምሳ ግብዣው የተሰተፉ 230 ዜጎች መሆናቸው ታውቋል።

እነዚሁ የህብረተሰብ ክፍሎች በትንሳኤ በዓል ምክንያት ተጠርተው የምሳ ግብዥ የተደረጋላቸው መሆኑን ያልጠበቁት መሆኑን በመግለጸ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አመስግነዋል፡፡

በጌትነት ምህረቴ
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በማራቶን ውድድር ‼️

👉 በሀምቡርግ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በ2:17:23 የቦታውን የማራቶን ክብረወሰን በማሻሻል አሽነፈች፤

👉 በማድሪድ ማራቶን ሥራነሽ ይርጋ የቦታውን ሰዓት በማሻሻል፣ መሰረት አበባየሁ ደግሞ 2ኛ ሆና ውድድሯን ጨርሳለች፤

👉 በኢንሼዴ ማራቶን አለምፀሀይ አሰፋ 2ኛ ሲትወጣ አበራሽ ፈይሳ 4ኛ ሆኖ ጨርሳለች። በወንዶች ታዱ አባተ 3ኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል፤

👉 በቬና ማራቶን በሴቶች 4ኛ ኡርጌ ሰቦቃ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን ማጠናቀቋን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለዋግኽምራ ብሔረሰብ ተፈናቃዮች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ማዕድ ያጋሩ አካላትን አቡነ በርናባስ አመሰገኑ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና የካናዳ አሕጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ በርናባስ ለዋግኽምራ ተፈናቃዮች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ በትንሣኤ በዓል ማዕድ ያጋሩ አካላትን አመስግነዋል።

በማዕድ ማጋራቱ በርካታ አካላት 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ በማድረግ መሳተፋቸውን የገለፁት አቡነ በርናባስ ኮሜዲያን እሹቱ መለሰ እና ጋዜጠኛ መታሰብያ ቀጸላ ጉልህ አስተዋጽኦ አድርገዋል ብለዋል።

አቡነ በርናባስ ተፈናቃዮች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ በትኩረት እንዲሠራ ጠይቀዋል።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ ከፍያለው ደባሽ ሰው ሁሉ ወደ ዋግ ፊቱን እንደመለሰ ተገንዝበናል፣ ሰው በሰው ተደጋግፎ ችግርን ማለፍ እንደ ሚቻል ከዚህ ጊዜ በላይ የምንረዳበት ጊዜ አይኖርም ብለው ተፈናቃዮች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከአበርገሌ ወረዳ፣ ጻግብጅ ወረዳ፣ ዛታ ወረዳ፣ ወፍላ (ኮረም) ወረዳ፣ ዝቋላ 6 ቀበሌና ሰቆጣ ወረዳ 1 ቀበሌ ተፈናቅለው በአራት (4) መጠለያ ጣብያዎች እንደሚገኙ አቶ ከፍያለው ተናግረዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ