Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
650 photos
9 videos
59 files
206 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
በ2018 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የአንደኛ ዓመት የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች ወደየተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ብዙ ተማሪዎችን ተቀበሉ?
🔵 ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 5,700 የፍሬሽማን ተማሪዎችን መቀበሉን አሳውቋል፡፡ 
🔵 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ5,000 በላይ የፍሬሽማን ተማሪዎችን መቀበሉን ገልጿል፡፡ 
🔵 ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3,100 በላይ የፍሬሽማን ተማሪዎችን ተቀብሏል፡፡ 

ዩኒቨርሲቲዎቹ በተጨማሪም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ያመጡ የሪሚዲያል ተማሪዎችንም ተቀብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን የ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ዛሬ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም መቀበል ጀምሯል፡፡

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወሰደው ያለፉ ተማሪዎች ቁጥር 52,279 እንደነበር አይዘነጋም፡፡ (የ2017 ዓ.ም እና የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎችን ሳይጨምር)

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
51👍3👏3
Forwarded from Campus materials
በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በጣም መጠንቀቅ ያሉባቹ ነገሮች

ከመጥፎ ጓደኛ ተጠንቀቁ

ይህ እጅጉን የማይስተዋል ነገር ግን በአንድ ተማሪ ህይወት ላይ ይሄ ነው የማይባል ተፅእኖ የሚያሳድር ወሳኝ ነገር ነው። ውድ የ Campus material ቤተሰቦቻችን በጊቢ Life ስኬታማ መሆን ከፈለጋቹ አልባሌ ነገር ከሚያስተምራቹ ከጥናት ከትጋት ከሚያስተጓጉላቹ ጓደኛ ተጠበቁ።

ሺ አመት አይኖር? ዛሬ እንዝናና

አብዛኛው ተማሪ ለነገ መልካም ነገር ለነገ ስኬቱ ዛሬ ዋጋ መክፈል እንዳለበት አይረዳም። በቃ ስኬት ከመሬት ተነስቶ Or ከሰማይ ተንጠባጥቦ የሚያገኘው ይመስለዋል። ውድ ቤተሰቦቻችን ስንዴ ዘርታቹ ጤፍ እንደማትጠብቁ ዛሬ ጥናት ትታቹ ፈታ ካላቹ እመኑኝ ጥሩ ውጤት ማምጣት ህልም ሆኖ ይቀራል ስለዚህ አስተውሉ ዛሬውኑ ሰግጡ ዛሬውኑ በአግባቡ አንብቡ መዝናናቱም ሁሉም ይደርሳል።

ጊዜን ከማባከን ተቆጠቡ

በጊቢ ህይወት የናንተን ጊዜ የሚፈልጉ እጅግ ብዙ ነገሮች አሉ። ጊዜያቹን በአግባቡ ካልተጠቀማቹ ባካኝ ሆናቹ ነው የምትቀሩት። ና እንውጣ ሲሉህ/ሽ እምቢ በል/በይ በቃ በ PlanProgram ተንቀሳቀሱ።

☑️ይህ የ Campus Material ራእይ እና አላማ ነው እናንተን ውጤታማ ማድረግ።

መልካም የፍሬሽማን ጉዞ ይሁንላችሁ🥰

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
JOIN: @Campus_materials
JOIN:
@Campus_materials
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
69👍23🆒7🥰6👏3
Forwarded from Remedial Class
የጥሪ ማስታወቂያ
#ሰላሌ_ዩንቨርስቲ

በ2018 ዓ. ም በረሜድያል ፕሮግራም በሰላሌ ዩንቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ ምዝገባ የሚካሄደው ህዳር 2 እና 3/2018 ዓ. ም  መሆኑን እናሳዉቃለን ::

ሰላሌ remedial group👇
https://news.1rj.ru/str/selale2018remedial

JOIN📱 @Remedial2018batch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
26👍6😱3
Forwarded from Remedial Class
#BoranaUniversity

በ2018 ዓ.ም ቦረና ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 03 እና 04/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

JOIN: @Remedial2018batch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
21🥰3
Forwarded from Remedial Class
#JinkaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 10 እና 11/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል።

ትምህርት ህዳር 15/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።

ቻናላችንን Join ማድረግ እንዳትረሱ
JOIN: @Remedial2018batch ⚡️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
18👌2😇2
Forwarded from Campus ተማሪ
Patrick_J_Hurley_A_concise_introduction_to_logicBookZZ_org.pdf
6.4 MB
🧠 Hurley  - A concise introduction To logic

💎 11th edition

🔶 እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ኖቶች እና ጥያቄዎች ያሉት የ Logic and Critical Thinking አጋዥ መፅሀፍ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውጤት እንዲሰቅሉ የሚረዳ መፅሀፍ ነው😘

እዚህ ላይ ያሉትን የሁሉንም ጥያቄዎች መልስ የያዘ PDF እናጋራቿለን::

ቻናላችንን ለሌሎች share ያድርጉ😀

✈️ @CAMPUS_TEMARI
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
29👍4🥰2😱2
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል። #Fortune

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭8225👎17😱4🤗2🔥1😇1
ዛሬ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች ቅሬታቻዉን በትምህርት ሚኒስቴር ላይ ሲያሰሙ ዉለዋል👋

ይህም ተቃዉም ትላንት ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች 3ኛ ዓመት ካጠናቀቁ ቦኃላ ለአንድ ዓመት ማስተማር አለባቸው በሚለው ሃሳብ ጋር በተያያዘ መሆኑን ለመረዳት ችለናል::

የተማሪዎቹ መፈክር"Down Down Birhanu'

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
👏225🫡2820👍9👎7🔥7
Forwarded from Remedial Class
የ Remedial Special Class ዝግጅታችን ተጀመሯል።

ትምህርቱ እና ሌሎች ሚጠቅሟቹ materials የሚሰጠው በቴሌግራም Private Group ሲሆን: ለመረዳት በጣም ግልፅ የሆኑ ኖቶች,Video, Voice, PDF እና Diagram ይሆናል::

በተጨማሪም:-
📝በቂ Note እና አጋዥ መፅሐፍት፣
🔗በአማርኛ ፅሁፍ, diagram ማብራሪያ፣
📹እርስ በርስ ምትረዳዱበት group
Review questions ፣ ግልፅ እና በቀላሉ እንድትረዱ በማድረግ ትምህርቱ ይሰጣል።

✔️ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች
ይህን
➡️@Remedialtutor_bot ቦት ተጠቀሙ::

ለበለጠ መረጃ :@Remedial_supportbot


🙀 መልካም የRemedial ጉዞ ይሁንላችሁ🥰

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
JOIN:
@Remedial2018batch
JOIN:
@Remedial2018batch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
17🙏3👍1
አዲሱ መመሪያ‼️
ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ኦልድ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ፣ ቶማቶ ዴይ፣ ከለር ዴይ፣ ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡

በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ ከባት በታች የሆነ ቁመት ያለው ለብሶ መገኘት አለባቸው ተብሏል፡፡ 

ከደንብ ልብስ ውጪ ቢሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን አለባበስ መልበስ ይጠበቅባቸዋል ይላል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ትምህርት ቤት ውስጥ መፈፀም የተከለከሉ ድርጊቶች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል ደግሞ የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ የትምህርት አመራር፣ ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ማህበረሰብ አካላትን መዝለፍ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽና አካላዊ ጥቃት መፈጸም ቅጣት የሚያስከትል ተግባር ነው ተብሏል፡፡

ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ሞባይል እና የሙዚቃ ማዳመጫ መሣሪያዎችን ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል፡፡

በቃል፣ በምልክትም ሆነ በጽሑፍ ፀያፍ ነገሮችን መግለፅ፤ ጨዋነት የጎደላቸውን እንዲሁም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ምስሎችና ጽሑፎች በትምህርት ቤት ውስጥ ይዞ መገኘትና ማሰራጨት አይፈቀድም፡፡

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የማንኛውንም ዓይነት የኃይማኖት አምልኮ ሥርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ ይከለክላል፡፡

ማንኛውም ተማሪ አገራዊ እሴት ያልሆኑና መጤ የሆኑ ነገሮችን በሰውነት ላይ ምልክት ማድረግ፤ ከአገራዊ እሴት ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ መጤ ምልክቶችን በሰውነት ላይ መነቀስ፣ ማሳየት፣ ማድረግ፣ መጠቀም ፍፁም የተከለከለ ነው ብሏል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አንድ ተማሪ በሥነ-ምግባር ጉድለት እጅ ከፍንጅ ከተያዘና የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ሆኖ ከተገኘ ውሳኔ እስኪሰጠው ከትምህርት ቤት ሊታገድ እንደሚችልም በመመሪያው ሰፍሯል፡፡

ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ በተለይም ከ7 እስከ 12ተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እስከ 1 ዓመት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከትምህርት ሊታገዱ ይችላልም ሲል ረቂቅ መመርያው አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ደንብ ተሰናድቷል፡፡

በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምባሆ(ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶች እና ሱስ አስያዥ ዕፆች ትምህርት ቤት አካባቢ መሸጥም ሆነ ይዞ መገኘትን ይከለክላል።

የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሻጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፤ ቁማር ቤቶች፤ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ ወይም ማሳጅ ቤቶች በትምህርት ቤቶች በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ መክፈት አይቻልም፡፡

ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ፣ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም በትምህርት ቤት አቅራቢያ መክፈትን ከልክሏል።

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁7655👏25👍15😭6🫡4👎3🙏2
ትናንት ህዳር 11/2018 ዓ.ም ጠዋት ላይ በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ተማሪዎች "የምግብ እጥረት አለ ይስተካካከል" ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡበት  የግቢው ዘበኞች ተኩስ ከፍተው የ2 ተማሪዎች ህይወት እንዳለፈ እና ሌሎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ :- (አዩዘሀበሻ)

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭260💔33😢129😱9
Advanced Freshman
ትናንት ህዳር 11/2018 ዓ.ም ጠዋት ላይ በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ተማሪዎች "የምግብ እጥረት አለ ይስተካካከል" ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡበት  የግቢው ዘበኞች ተኩስ ከፍተው የ2 ተማሪዎች ህይወት እንዳለፈ እና ሌሎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የደረሰን መረጃ ያመላክታል። ምንጭ :- (አዩዘሀበሻ) 🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
" በምግብ በአቅርቦቱ ላነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ ሊሰጥ፣ እነርሱም ጥያቄዎቻቸውን በነጻነት አንስተው መግባባት ተደርሷል " - ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡና ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ የጠየቃቸው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ተበጀ፣ ተማሪዎች ቅሬታ የማቅረብ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አምነዋል።

" ጥያቄዎች አንስተው ነበር ችግሩን ለመፍታት በተፈጠረ መድረክ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተማሪዎችም በተገኙበት ተወያይተው መግባባት ላይ ተደርሷል " ሲሉ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ፣ " የምግብ ችግር አለብን " በማለት ጭምር ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፤ መግባባት ላይ የተደረሰው በምን መልኩ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፣ " ከዚህ ጋር በተገናኘ በአቅርቦቱ ላነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥ፣ እነርሱም ጥያቄዎቻቸውን በነጻነት አንስተው ይሄ መግባባት ተደርሷል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በደፈናው መግባባት ላይ ተደርሷል ሳይሆን ላነሱት ቅሬታ ምን ማስተካከያ ልታደርጉ ነው መግባባት ላይ የተደረሰው ? ሲል በድጋሚ የጠየቃቸው አቶ አምሳሉ፣ መስተካከል ያለባቸው የጠየቋቸው የቀን ሽፍት ማድረግና መሰል ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል።

" ለምሳሌ 'ረቡዕ የሆነው የሩዝ ምግብ ቅዳሜ ይሁንልን' " እንዳሉ ተናግረው፣ " ከዚህ በፊት ይቅር ብለው የነበረውን ፓስታ ይዘጋጅልን ብለዋል፤ በመጠንም ያነሱት ጥያቄ አለ " ሲሉ ያከሉ ሲሆን፣ የተግባቡት ይህን ሊያስተካክሉ መሆኑን ገልጸዋል።

" የሞቱና የቆሰሉ ተማሪዎች አሉ " ስለመባሉ ስንጠይቃቸው ደግሞ፣ " መረጃው የለኝም " ያሉ ሲሆን፣ ስለጉዳዩ እያብራሩልን አይደል እንዴ እንዴት መረጃው የለኝም ይላሉ ? ስንላቸው፣ " ያለኝን መረጃ ነው የምናገረው፤ ስለዛኛው (ግድያው) መረጃ የለኝም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ቢጠይቅም ጉዳይ እንደማይመለከተው በመግለጽ፣ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። የተማሪዎች ኀብረት መረጃው በፕሬዚዳንት ደረጃ ይሰጥ ተብሏል ቢልም፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ግን ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

" በጥይት ቆሰሉና ተገደሉ " ስለተባሉ ተማሪዎች መረጃው ደርሶት እንደሆን የጠየቅነው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ግን፣ " የሞተም ሆነ የቆሰለ የት፣ በማን? " የሚለውን መረጃ እያጠናቀረ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ውይይት በተደረገበት ወቅት አንድ ተማሪ ምን አለ?

" ዩኒቨርሲቲው ጊዜ ስጡኝ ብሎን ነበር። ግን አመት ከርመን ስንመጣ ያቆየን ረሃብ ነው። ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መስከረም 5 ነው የገቡት። እኛ የሁለተኛ አመት ተማሪዎች ጥቅምት 17 ነው የገባነው። ግን መስከረም 5 ከገባ ተማሪ ጋር ነገ የመውጫ ፈተና የምንፈተነው። ለምን ?

እናንተ ናችሁ ፓለቲካን የምንትሰብኩብን እንጅ እኛ ለመማር ነው የመጣነው። እኛ ጥያቄያችን ርቦናል የሚል ነው። ከተለያዬ ቦታ ነው የመጣነው፤ ስልካችንን እየተዘረፍን፤  በሬ እያሸጥን ነው ለመማር የመጣነው።

በዓለማችን ትልቁ መሳሪያ ትምህርት ነው። ስለዚህ አስተምሩን፤ መግቡን ኢትዮጵያን እናሳድጋት ነው ያልነው። ሌላ የፓለቲካ አጀንዳ የለንም። ሞትማ በነበርንበት ቦታ ሞልቷል። ምግባችንን አስተካክሉልን፣ እንማር " ብሏል።

Via:- TIKVAH

🌟JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
40😢35👍16👏5💔2
Forwarded from Remedial Class
እስካሁን ለ2018 ሪሚድያል ተማሪዎቻቸው ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር!

1. ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 2 እና 3
2. ቦረና ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 8 እና 9
3. ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 4 - 7
4. ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 5-8
5. ባህርዳር ዩንቨርስቲ:- ህዳር 11 እና 12
6. ጋምቤላ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 15 እና 16
7. ራያ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 22 እና 23
8. ጅንካ ዩንቨርስቲ:- ተራዝሟል
9. ደባርቅ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
10.ኦዳ ቡልቱም ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
11.ድሬ ደዋ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 20 እና 21
12.አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
13. መቱ ዩንቨርስቲ :- ታህሳስ 1 እና 2
14. መቅደላ አምባ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
15. አምቦ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
16. ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
17. ወሎ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
18. አሶሳ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
19.ደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ :- ህዳር 25 እና 26
20. ወልድያ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 6 እና 7
21. ሰመራ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
22. ጎንደር ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
23. ወራቤ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
24. ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
.

#️⃣ቻናላችንን ዘንድሮ Remedial ለሆኑ ተማሪዎች share ያድርጉ🤔

JOIN: @Remedial2018batch
JOIN: @Remedial2018batch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
39🙏7👍3🆒2