የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተከናወነ
******************************
የኤጲስ ቆጶሳቱ ሹመት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መሪነት በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባደረገው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ መሠረት ለዘጠኙ ቆሞሳት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መሪነት በሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ ዕድ ተፈጽሟል።
በዚህ መሰረት
1. ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል ተ/ማርያም አባ ገሪማ ተብለው የጌዲኦ፣ አማሮና ቡርጅ ሀገረ ስብከት፣
2. ቆሞስ አባ ሳህለ ማርያም ቶላ አባ ገብርኤል ተብለው የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣
3. ቆሞስ አባ ስብአት ለአብ ሀይለማርያም አባ ጢሞቲዎስ ተብለው የዳወሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት፣
4. ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ አባ ኤልሳዕ ተብለው የምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት፣
5. ቆሞስ አባ ሀይለማርያም ጌታቸው አባ በርቶሎሜዎስ ተብለው የድሬደዋ ሀገረ ስብከት፣
6. ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ አባ ኤፍሬም ተብለው የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት፣
7. ቆሞስ አባ ዘተ/ሀይማኖት ገብሬ አባ ኤጲፋንዮስ ተብለው የሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት፣
8. ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ አባ ዳንኤል ተብለው የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት እና
9. ቆሞስ አባ ወ/ገብርኤል አበበ አባ ኒቆዲሞስ የምስራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ሆነው መሾማቸውን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

👍76❤13👎13👏4
በኢትዮጵያ አይዶል የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ ያደረጉት ንግግር https://www.youtube.com/watch?v=iCkkYOlgLKI
YouTube
በኢትዮጵያ አይዶል የመክፈቻ ሥነ ስርዓት-የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ
በኢትዮጵያ አይዶል የመክፈቻ ሥነ ስርዓት-
የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ
t #EbcEntertainment #Ethiopian #Ebc #meznagna #

👍23👎11❤2
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ማታ ጀምሮ መመልከት ይችላሉ፡- የትምህርት ሚኒስቴር
**************************************
የትምህርት ሚኒስቴር ከሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በማጠናቀቅ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ማታ ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ አስታውቋል።
በዚህም ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ እሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ በ https://result .ethernet.edu.et በመግባት ማወቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በመውጫ ፈተናው የሚፈለገውን የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ፈተናውን በየስድስት ወሩ ደጋግመው መውሰድ እንደሚችሉም ነው የተገለፀው።
የመውጫ ፈተናው ከመሰጠቱ አስቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ከፈተና ስርዓቱ ጋር እንዲለማመዱ የሙከራ እና የሞዴል ፈተና እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከተጀመሩ ሪፎርሞች አንዱ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

👍62👎22❤20👏3
ተጀመረ
ነገን ዛሬ እንትከል!!!
**********
ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉበት እለት ነው!!
መላው ኢትዮጵያውያንም በያሉበት ስፍራ ጀንበር ወጥታ እስከምትገባ የአረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ነገን ዛሬ ይተክላሉ።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid026uZPSxKbRsRW4tXw5gcg6rZFkodYpZUCTGhfqWLhBmLk7wtbFfbpRpizhUh3xukkl

👍54👎30❤10👏8
ችግኝ መትከላችንን በጠዋት ጀምረናል፤ እስከምሽት ይቀጥላል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
********************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ ማለዳ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
በማለዳ በዝናብ ወጥታችሁ አረንጓዴ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ ለምትገኙ ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ምስጋናችን ይድረስ ብለዋል።
ዛሬ ኢትዮጵያውያን በህብረት ታሪክ የምንሰራበት ቀን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ዛሬ ለኛ ቀላል የሚመስለው ጉዳይ ብዙዎች የከበዳቸው እና የማይችሉት ነው ብለዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid08HimLAqS82RNYbUFa3PsVxCt3AYWZyDw1ZZp2qJiQUuYLqgKQ1YT935AVdztfNb4l

❤34👍33👎27
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የ500 ሚልዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ከጽ/ቤቱ ሰራተኞች እና በከተማው ከሚኖሩ አካል ጉዳተኞች ጋር ዛሬ ማለዳ የአፕል ችግኞችን በመትከል አስጀመሩ።
👍45❤24👎22👏1
ከማለዳው 12 ሰዓት እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ 147 ሚሊዮን 965 ሺህ ችግኞች ተተክለዋል፡- የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
****************
ከ9 ሺህ በላይ የችግኝ ጣቢያዎች አሁንም መረጃዎችን ወደ ማዕከሉ እየላኩ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ገልጸዋል።
ከሁነቶች መከታተያ ክፍል (situation room) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ፤ ዜጎች በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል በንቃት እየተሳተፉ ነው ብለዋል።

👍47👎16❤11👏1
የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተሳትፎ በዛሬው የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ
👍76👎17❤16👏4