EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የመስቃንና ማረቆ ወንድማማች ሕዝቦች የእርቅ ማጽኛ ፕሮግራም እየተካሔደ ነው
***********************

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስቃን እና ማረቆ ወንድማማች ህዝቦች የእርቅ ማጽኛ ፕሮግራም በኢንሴኖ ከተማ እየተካሔደ ነው።

በመስቃን እና ማረቆ ወንድማማች ሕዝቦች የእርቅ ማጽኛ ፕሮግራም ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የብሔረሰቦች ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የመስቃን ቤተ ጉራጌ እና የማረቆ ብሔረሰብ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የመስቃን እና የማረቆ ወንድማማች ሕዝቦች ለዘመናት ያቆዩትን የጋራ እሴት በጽኑ መሰረት ላይ ለመገንባት ያለመ የእርቅ ማጽኛ ፕሮግራም ዛሬ በመካሔድ ላይ መሆኑን ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍354
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን የግንባታ ሂደት ተዘዋውረው ተመለከቱ
************************

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የፌዴራል መንግሥት ልዑክ ከትናንት ጀምሮ በክልሉ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ከክልሉ መንግሥት አመራሮች ጋር እየመከረ ነው።

ከጠዋት ጀምሮ ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ የሚገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የአዲሱን የዓባይ ድልድይ የግንባታ ሂደት የተመለከቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው ብሔራዊ ባንክ የሚያስገነባውን ሕንጻም በቦታው ተገኝተው አስጀምረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎቹ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታን መመልከታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
👍3214👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሊ ክልል 2ኛው ዙር የጂግጂጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ጎበኙ
**************************

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ከሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት 2ኛው ዙር የጂግጂጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
32👍26👏7
የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ
**************************

በ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

ከትናንት ምሽት ጀምሮ የሶማሊያ፣ የቡሩንዲ፣ የኬፕቨርድ፣ የኮሞሮስ እና የካሚሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የህብረቱ የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
38👍26👎1
ሲጋራ በእንጀራ ውስጥ በመክተት ተጠርጣሪ ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ መምሪያ ይዞ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
**********************

ግለሰቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አንበሳ ጋራዥ ጀርባ ወደ ሚገኘው የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የሄደው በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ሰው ለመጠየቅ ነበር።

ስንቅ ለማቀበል በሚመስል መልኩ በያዘው ሳህን ውስጥ ወደ ተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ሲጋራ ለማስገባት ሲሞክር በፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውሏል።

በፖሊስ መምሪያው የተጠርጣሪ ማረፊያ ቤት አካባቢ የፍተሻ እና የማረጋገጥ ስራ የሚሰሩ የፖሊስ አባላት በወቅቱ ግለሰቡ ምግብ አስመስሎ የያዘውን ሳህን እንዲከፍት አድርገው ሲመለከቱ 20 ፓኬት ሲጋራ ከላይ በእንጀራ ተሸፍኖ ሊያገኙ መቻላቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ጣቢያ የተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ለሚገኙ ሰዎች ሲጋራ ማስገባት የተከለከለ ሲሆን፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው ደንብ ቁጥር 299/2006 ላይ በተደነገገው መሰረት ትምባሆን በማንኛውም ህዝብ በሚሰበሰብበት ወይም በሚገለገልበት ቦታ ማጨስ ክልክል እንደሆነ ተደንግጎ ይገኛል።
👍568👎4
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተወያዩ
*******************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ በዚሁ ወቅት፥ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን መካከል ያለው ግንኙነት ሥር የሰደደ መሆኑን አንስተው፤ ሀገሪቱ እንደ ሕብረቱ አባልነቷ እና መቀመጫነቷ ለኮሚሽኑ ስታደርገው የቆየችውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው፥ አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የደስታ መግለጫ አስተላልፈው፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ደህንነት እና መረጋጋት ያላትን ቁልፍ ሚና አውስተዋል።
👍8728👏7👎2