EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሊ ክልል 2ኛው ዙር የጂግጂጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ጎበኙ
**************************

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ከሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት 2ኛው ዙር የጂግጂጋ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
32👍26👏7
የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ
**************************

በ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

ከትናንት ምሽት ጀምሮ የሶማሊያ፣ የቡሩንዲ፣ የኬፕቨርድ፣ የኮሞሮስ እና የካሚሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የህብረቱ የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
38👍26👎1
ሲጋራ በእንጀራ ውስጥ በመክተት ተጠርጣሪ ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ መምሪያ ይዞ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
**********************

ግለሰቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አንበሳ ጋራዥ ጀርባ ወደ ሚገኘው የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የሄደው በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ሰው ለመጠየቅ ነበር።

ስንቅ ለማቀበል በሚመስል መልኩ በያዘው ሳህን ውስጥ ወደ ተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ሲጋራ ለማስገባት ሲሞክር በፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውሏል።

በፖሊስ መምሪያው የተጠርጣሪ ማረፊያ ቤት አካባቢ የፍተሻ እና የማረጋገጥ ስራ የሚሰሩ የፖሊስ አባላት በወቅቱ ግለሰቡ ምግብ አስመስሎ የያዘውን ሳህን እንዲከፍት አድርገው ሲመለከቱ 20 ፓኬት ሲጋራ ከላይ በእንጀራ ተሸፍኖ ሊያገኙ መቻላቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ጣቢያ የተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ለሚገኙ ሰዎች ሲጋራ ማስገባት የተከለከለ ሲሆን፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው ደንብ ቁጥር 299/2006 ላይ በተደነገገው መሰረት ትምባሆን በማንኛውም ህዝብ በሚሰበሰብበት ወይም በሚገለገልበት ቦታ ማጨስ ክልክል እንደሆነ ተደንግጎ ይገኛል።
👍568👎4
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተወያዩ
*******************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ በዚሁ ወቅት፥ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን መካከል ያለው ግንኙነት ሥር የሰደደ መሆኑን አንስተው፤ ሀገሪቱ እንደ ሕብረቱ አባልነቷ እና መቀመጫነቷ ለኮሚሽኑ ስታደርገው የቆየችውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው፥ አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የደስታ መግለጫ አስተላልፈው፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ደህንነት እና መረጋጋት ያላትን ቁልፍ ሚና አውስተዋል።
👍8728👏7👎2
Live stream finished (1 day)
የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ
**********

በ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

ከትላንት ምሽት ጀምሮ የሶማሊያ፣ ቡሩንዲ፣ ኬፕቨርድ፣ ኮሞሮስ እና የካሜሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም የቱኒዚያ፣ የደቡብ ሱዳን፣ ጋና እና የአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የህብረቱ የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።
👍393👏2
ተልዕኳቸውን በጀግንነት ፈጽመው ለተመለሱ ልዩ የፀረ-ሽብር አመራርና አባላት አቀባበል ተደረገ
*************

ተልዕኳቸውን በጀግንነት ፈጽመው ለተመለሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልዩ ፀረ ሽብር መምሪያ አመራርና አባላት በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ ካምፕ ደማቅ አቀባበል ተደርጓል፡፡

አመራርና አባላቱ በተለያዩ ግዳጆች ላይ ከአራት ዓመት በላይ ቆይተው ሲመለሱ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታና የማኔጅመንታቸው አባላት በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር አባላቱ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በሚንቀሳቀስባቸው በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በተልዕኮ ላይ ቆይተው አሁንም ለሌላ ፖሊሳዊ ተልዕኮ እንደተመለሱ ተጠቁሟል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር ኃይሉ ያካበተውን ልምድና ሙያዊ ብቃት ተጠቅሞ በተሰማራባቸው አካባቢዎች ሁሉ በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድና በመቆጣጠር በርካታ ድሎችን ሲጎናፀፍ የቆየ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የልዩ ፀረ-ሽብር ኃይል አመራርና አባላት በቀጣይ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በጥሩ ፖሊሳዊ ሙያና ስነ-ምግባር ለመፈፀም የተዘጋጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
👍11633👎13👏12