የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
**********************
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሄደው መደበኛ ጉባኤው የአሰፈፃሚ ተቋሟት የ6ወር አፈፃፀም ሪፖርት ፤ተጨማሪ በጀት እና ሹመትን በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
በሚካኤል ገዙ

👍23❤9👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሐፊና የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ሞሊ ፊ፣ እና የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክል ሀመር ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በአህጉራዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል ።

👍49👎12❤11👏2
44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ተጀመረ
******************************
44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ዛሬ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።
ስብሰባው "ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ሥርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2024 መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።
በስብሰባው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማኅማት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶችና የኅብረቱ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።
ምክር ቤቱ በዋናነት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራ ለማፋጠን ባለፈው አንድ ዓመት የተሰራውን ሥራ በተመለከተ በሚቀርበው ሪፖርት ላይ ምክክር ያካሄዳል።
በተለይም ነጻ የንግድ ቀጣናውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የኃብት ማሰባሰብ ሥራዎች፣ ቅንጅታዊ አሰራር፣ በታሪፍና የንግድ ሰንሰለት ዙሪያ በተሰሩ ሥራዎች ዙሪያም ይመክራል።
የአፍሪካ ኅብረት ከአገራትና ከባለብዙ ወገን ተቋማት ጋር በተመለከተ ያለውን አጋርነት በተመለከተ የሚደነግገውን ረቂቅ ፖሊሲና ስትራቴጂ ዘሪያ እንደሚወያይም ይጠበቃል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/791657002988481

👍45❤8👎1
ኢትዮጵያ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጠየቀች
***************
አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኩል ጥሪ አቀረበች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ፤ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጥያቄ ያቀረቡት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ጥያቄ ከአፍሪካ የ2063 አጀንዳ ጋር የሚጣጠም መሆኑን አንስተዋል።
ያም ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን አገር በቀል ቋንቋዎች ለማጠናከር ከተያዘውን የአፍሪካ ኅብረት ግብ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑንም ነው በማብራሪያቸው ያነሱት።
የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር የተፈረመው አማርኛን ጨምሮ በአራት ቋንቋዎች መሆናቸውን ያነሱት አምባሳደር ታዬ፤ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ ማድረግ የአፍሪካ የቋንቋ ብዝኃነት መቀበል እና የጋራ ማንነትን ማጠናከር ነው ብለዋል።
ይህም አህጉሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እገዛ እንደሚያደርግ መጠቆማቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

👍150❤27👏11👎10
የኢትዮጵያ ህልም የነበረው ኅብረት ተሳክቷልን?
****************
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩት ሀገራት ነጻነት የከፈለችው ዋጋ ውድ ነው፡፡ ነጻነቷን ጠብቃ የኖረችው ኢትዮጵያ ብቻዋን የመንግሥታቱ ማኅበር አባል በነበረችበት ወቅት የአውሮፓውያንን የግፍ ወረራ አውግዛለች፤ ብቻዋንም በፍትህ አደባባይ ቆማለች፡፡
የኢትዮጵያ የፍትህ አደባባይ ጩኸት የገለጠው የአውሮፓውያን ግፍ አውዳሚው የሁለተኛ ዓለም ጦርነት እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ይሁንና ከታሪክ ያልተማረው ዓለም አሁንም ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካን እና የጭቁን ሕዝቦችን ጩኸት እየሰማ ባለመሆኑ ዓለም መከራ ውስጥ እንድትኖር አድርጓታል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ኅብረቶችን መሥራች ሆና በአባልነት የምትቀላቀለው በዓለም ላይ ፍትህ እንዲሰፍን፣ ጉልበተኞች አቅመ ቢሶችን እንዳይጨፈልቁ እና ሁሉም የዓለም ሕዝብ በእኩልነት የመኖር መብቱ እንዲከበርለት ነው፡፡
ለዚህም ነው ራሷ ነጻነቷን ስላስከበረች በቃ ብላ ያልተቀመጠችው፡፡ አፍሪካውያን ወንድሞቿ ነጻ ሳይወጡ ነጻነቷ ሙሉ ስለማይሆን አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት ነጻ እንዲሆኑ የታገለችው፡፡ የዓለምን ፍትህ የማይሻው የምዕራባውያኑ ጎራ ይህን የኢትዮጵያን ጥረት ለማሰናከል እና አፍሪካን ድምጽ አልባ ለማድረግ ዛሬም ኢ-ፍትሃዊ ጫናውን እንደቀጠለ ነው፡፡
ኢትዮጵያ አፍሪካ ነጻነቷን እንድታገኝ ካደረገቻቸው ትግሎች ጎን ለጎን አፍሪካውያን ኅብረት ፈጥረው የሚደርስባቸውን ጫና እንዲቋቋሙ እና ሕዝቦቻቸው ወደ ተሻለ ህይወት እንዲሸጋገሩ ስትሰራ ቆይታለች፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0taa67HvPawF3sNSrRCjMEQVw2szFxEWgwjPzvxoA34xN6B3dwGcgNXeC3RyVzYPFl

👍65❤12👏4
የኢትዮጵያ ሬድዮ ለመላው አፍሪካውያን ድምጽ ሆኖ ያገለገለ ነው፡- ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሀፊ ጥበቡ በለጠ
******************
"ሬድዮ ለፀረ ቅኝ ግዛት" ትግል በሚል ሀሳብ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉት ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሀፊው ጥበቡ በለጠ፤ የኢትዮጵያ ሬድዮ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያንም በተለያዩ ቋንቋዎች ድምጽ ሆኖ ያገለገለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሬድዮ ለአፍሪካ ነጻነት ትልቅ ሚና መጫወቱን ያወሱት አቶ ጥበቡ፤ የኢትዮጵያ ሬድዮ ወደ ስራ ሲገባ መላው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ስር የወደቀበት እና ነጻነት የሚናፈቅበት ወቅት መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያ ሬድዮ አማካኝነት የነጻነት ድምጽ ማሰማት መቻሏን የገለጹት አቶ ጥበቡ፤ የኢትዮጵያ ሬድዮ ለነጻነት ብስራት መታገያ እና ማታገያ ሆኖ መቆየቱንም አቶ አክለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የሬድዮ ቴክኖሎጂን ያመጣችበት እና ያሳደገችበት ጊዜ በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው የሚሉት ባለሙያው፤ ከ1928 በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ የጣሊያን ወረራ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ከወረራው ማግስት ጀምሮም ጣሊያኖች ኢትዮጵያ ያቋቋመችውን ሬድዮ በመዝጋት የራሳቸውን የፕሮፓጋንዳ ማሽን መፍጠራቸውን አውስተው፤ ኢትዮጵያውያ ግን ለዚህ እጅ ባለመስጠት በሌሎች የህትመት ውጤቶች ለፀረ ቅኝ ግዛት ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ይሄንን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከጦርነቱ በኋላ፤ በኮሚዮኒኬሽንም ሆነ በጦርነት በዲፕሎማሲው ድል ያደረገችበት እንደነበር ገልፀዋል፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid032td8LeRRyVsa8gLgPyWfpqb6jSkGCuwU6tsDFYnmpfjUzsaHwDmZg5hj66xihb4Xl

👍37👎5❤3👏1
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ከፖርቱጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
*********************
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲልቪ ባይፖ-ተሞን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በተመሳሳይ ሚኒስትሩ ከፖርቱጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ ከፖርቱጋል ጋር በቱሪዝም፣ በትምህርት፣ በንግድ እና በኢንቬስትመንት ዘርፎች ተባብራ መስራት ትፈልጋለች ብለዋል።
የፖርቱጋሉ ሚኒስትር በበኩላቸው አገራቸው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራን እንደምትደግፍ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

👍48👏8❤7