EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሲንጋፖር ፕሬዚዳንት ታርማን ሽሙጋርተናም ጋር ተወያዩ
************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሲንጋፖር ፕሬዚዳንት ታርማን ሽሙጋርተናም ጋር ተወያይተዋል፡፡

መሪዎቹ በፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት በኢስታና ተገናኝተው በፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኀበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ከፕሬዚዳንት ታርማን ሽሙጋርተናም ጋር “የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለማጠናከር ተስማምተናል” ብለዋል፡፡
👍5233👎6
ምርጫ ትክክለኛ የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን የሚያሳይ የህዝብ መሻት መገለጫ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*********

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ "ወዳጄ ናሬንድራ ሞዲ፣ ሰላማዊ የሆነ እና የህዝብን መሻት ያከበረ ምርጫ በማካሄድዎ እንኳን ደስ አለዎት" ብለዋል።

"ይህ በራሱ በሀገሪቱ ዴሞክራሲ እያበበ ስለመሄዱ ግልጽ ማሳያ እና ታላቅ ስኬት ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት።

አክለውም፥ ምርጫ ትክክለኛ የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን የሚያሳይ፣ የህዝብ መሻት መገለጫ ነው ብለዋል።
👍4114👎3👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው ምርጫ የዴሞክራሲ መርሆዎችን ያከበረ መሆኑን ገለጹ
************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው ምርጫ የዴሞክራሲ መርሆዎችን ያከበረ መሆኑን በመጥቀስ፤ ለፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ያላቸውን የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ ፍትሐዊ፣ ግልፅ እና ሰላማዊ እንዲሆን ለሰጡት አመራር ራማፎሳን አድንቀዋል።

ይህም ፕሬዚዳንቱ ለህዝብ ፍላጎት እና ሁሉንም ለሚያስተሳስሩት የዴሞክራሲ እሴቶች መከበር ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
38👍20👎7
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲንጋፖር የኦርኪድ አበባ በስማቸው ተሰየመላቸው
***********

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲንጋፖር የመጀመሪያ ቀን ጉብኝታቸው፥ በብሔራዊው የእፅዋት ማዕከል ባህላዊውን እፅዋት የመሰየም ሥነሥርዓት ተካፍለዋል።

በሥነሥርዓቱም በኢትዮዽያ እና በሲንጋፖር መካከል ያለውን መልካም ወዳጅነት እና የጋራ መንፈስ ለማመላከት ‘አራንዳ ዐቢይ አሕመድ፣ ዝናሽ ታያቸው' የተሰኘ የኦርኪድ አበባ በስማቸው እንደተሰየመላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
👍249👎5
ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
**********

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ሪፐብሊክ በኢስታና ቤተመንግሥት በነበራቸው ቆይታ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት የሁለትዮሽ ምክክር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ብሎም በኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሲንጋፖር የትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል የፍላጎት ስምምነት መፈረሙን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
34👍22👏2