EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
**********

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ሪፐብሊክ በኢስታና ቤተመንግሥት በነበራቸው ቆይታ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት የሁለትዮሽ ምክክር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ብሎም በኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሲንጋፖር የትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል የፍላጎት ስምምነት መፈረሙን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
34👍22👏2
የተፈጥሮም ሆነ የሰው ሰራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም መስራት ያስፈልጋል፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*****************

ከተረጅነት በመላቀቅ የሚያጋጥሙ የተፈጥሮም ሆነ የሰው ሰራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

አደጋ በየትኛውም ወቅትና ጊዜ አይቀሬ ስለመሆኑ የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር በሚያደርጉት የተዛባ ግንኙነት ቁጥሩ እየጨመረ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

በመሆኑም አደጋን የማስተዳደርና በራስ አቅም የመቋቋም ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ነው የተናገሩት፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0EeVFxiCWx24VwdVNhM6UEr3cEaLhwQUpgyyaLsE6zMn89CnurKRB336dqAf1oA2Fl
👍451
የምክክሩ ባለድርሻዎች የትኞቹን አካላት ወክለው ተሳተፉ?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ባከናወነው የምክክር ምዕራፍ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ለመሆኑ እነዚህ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች የትኞቹን አካላት ወክለው ተሳተፉ?

1. የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች
• ከየወረዳው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወክሉ የተመረጡ ተወካዮች

2. የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች
• በአዲስ አበባ ከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች

3. የተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ)
• የሃይማኖት ተቋማት
• ሲቪል ማህበራት
• የአሰሪዎች ማህበራት
• የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን
• የመምህራን ማህበር
• የአካል ጉዳተኞች ማህበራት
• የሙያ ማህበራት
• የቀድሞው ሠራዊት ማህበር (ተቀናሽ ሠራዊት ማህበር)
• የጋዜጠኞች ማህበር
• የዩኒቨርሲቲ መምህራን (የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት)
• የንግድ ማህበራት ምክር ቤት
• የሴቶች እና ወጣቶች ማህበራት

4. የመንግሥት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ)
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች
• የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች
• የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን

5. የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች
• በተለያዩ ዘርፎች በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው፣ አንቱታን ያተረፉ እና ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ግለሰቦች

ምንጭ፦ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!
👍305
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ተጠናቀቀ
***************

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የምልዓተ-ጉባኤውን መጠናቀቅ በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሚተላለፉ አንዳንድ መልዕክቶች ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉና ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸው እንዲሁም በጥብቅ የሚያወግዛቸው መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተክርስቲያንና ለሀገራችን ህዝቦች ጠቃሚ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል በመግለጫቸው፡፡

በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን አንስተው፤ ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሚተላለፉ አንዳንድ መልዕክቶች ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉና ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸው እንዲሁም በጥብቅ የሚያወግዛቸው ናቸው ብለዋል፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/868771235277057
👍335👎3👏2
ምን እንጠይቅልዎ??
👍26👎5
ከተረጂነት እንውጣ የሚል አብዮት መቀስቀስ አለብን ፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
********************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከተረጂነት እንውጣ የሚል አብዮት መቀስቀስ አለብን ሲሉ ገለጹ፡፡

በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ ተፈጥሯዊም ይሁን ሰው ሰራሽ አደጋ አይቀሬ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህ ደግሞ አደጋን በራስ አቅም የማስተዳደር እና የመሸከም አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡

ዛሬ ባካሄዱት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባም፤ በአዲስ መልክ የፀደቀውን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲ ማስፈንጠሪያዎችና የትግበራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የ2016 በጀት ዓመት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ዕቅድ አፈጻጸምን መገምገማቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአደጋ ስጋት ስራዎች በሙሉ አቅም ለመፈፀም የባህል ለውጥ ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን የባህል ለውጥ ለማምጣት ደግሞ ልመናን የሚፀየፍ ትውልድን መፍጠር፣ የቆየውን የመደጋገፍና የመረዳዳት ማህበራዊ ዕሴት በማጠናከር እና በማጎልበት ራስን መቻል ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዓድዋ ጊዜ የነበረንን የአርበኝነት ወኔ እና ተነሳሽነት ድህነትን ለማሸነፍ መጠቀም ይኖርብናል፤ ለዚህ ደግሞ እንደ ሀገር የጀመርናቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማቶች ማፋጠን ወሳኝ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02uAhxUS2aG7JKaHXXjvDgQbEbqMPQRqbHU8FsVUvjYdWNUuoy4RbbDQqC3ntPfXF3l
👍4311👏5👎4