EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
"ዛሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በቤተክርስቲያኒቱ የሚገነባ ህንፃ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠናል።

ቤተ ክህነት የከተማውን ልማት ሥራ በላቀ ሁኔታ በመደገፍ እና ለኮሪደር ልማት ስራዎች መጀመር፤ በማፍረስ ሂደትም ሆነ መልሶ በመገንባት ሂደት እንዲሁም ህንፃዎችን በማደስ ላደረገችው ተሳትፎ እና ተግባራዊ የሆነ ምላሽ ከልቤ ለማመስገን እወዳለሁ።

በዚህ አጋጣሚ ከቤተክርስቲያንቱ ለቀረበልኝ ምስጋናም እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ ።"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
25👍23👎5
አክሱም አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
*******************

የአክሱም አፄ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ በይፋ ተመርቆ ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ጋር በመሆን ነው የአክሱም አፄ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የአክሱም አፄ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ዳግም አገልግሎቱን በይፋ መጀመሩ የሰላሙ ውጤት መሆኑን ገልጸው፤ አክሱም ሁሉን አቀፍ የቱሪስት መስህብ ያለው ከተማ ነው ብለዋል።

በቀጣይም ለአክሱም ህዝብና ቅርስ የሚመጥን የልማት ስራዎች እንደሚከናወን ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid035CgxcdD4k1oM1UnsPWeVpZTuMW6xocAGLPPp3LH6PA5Nw4HXpxofRvGkvXaMRnhcl
👍274
በኦሮሚያ ክልል በተያዘው ዓመት ምርት የሚሰጥ የቡና ሽፋንን ወደ 1.45 ሚሊዮን ሄክታር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ነው
*****************

በግብርናው ዘርፍ ለማሳካት ከተያዙ አራት ግቦች መካከል አንዱ የሆነውን ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ብዛት፣ ዓይነት እና ጥራት የማሳደግ አፈፃፀም በስኬት ጎዳና ላይ ይገኛል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

በተለይም የቡና ልማት ኢኒሼቲቭ በ2011 ዓ.ም፣ በ“ነቀምቴ አዋጅ” ይፋ ከተደረገ ጀምሮ ለአገሪቱ ብሎም ለክልሉ እያስገኘ ካለው ውጤት በተጓዳኝ አርሶ አደሩንም ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት።

እንደ አቶ ሽመልስ ገለጻ፥ ኢኒሼቲቩ በ2011 ዓ.ም 997 ሚሊዮን የቡና ችግኝ በመትከል የተጀመረ ሲሆን፤ በ2015 ዓ.ም 1.33 ቢሊዮን የቡና ችግኝ ለመትከል ተችሏል።

በአጠቃላይ፣ በአምስቱ ዓመታት ሂደት ከ866 ሚሊዮን ሄክታር በሚልቅ አዲስ መሬት ላይ ከ5.4 ቢሊዮን በላይ ቡና የተተከለ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ ወደ ግማሽ የሚጠጋው በአራቱ የወለጋ ዞኖች የተከናወነ ነው።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02q1uB8VPvZnmtT73u3fgWLSDnyM96Y1RNQZxVaFWLa8tcJ98McG8s5XtSPCaMdGwbl
👍529👏7
Live stream finished (2 days)
Live stream finished (3 minutes)
Live stream finished (2 minutes)
Live stream finished (5 minutes)
የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር ስራ በተያዘው የሦስት ወር መርሐ-ግብር ማጠናቀቃችንን ስገልፅ ደስታ ይሰማኛል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************

የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር ስራ በተያዘው የሦስት ወር መርሐ-ግብር ማጠናቀቃችንን ስገልፅ ደስታ ይሰማኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ የቀደሙትን የኮሪደር ልማት ስራዎች ግምገማ ስናጠናቅቅ ቀጣዩን ግምገማችንን በስራው ስፍራ ተገኝተን እንደምናካሂድ ቃል ገብተን ነበር ብለዋል።

በቀጣይ ስራ ሀብት ቁጠባ ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ በቀሪ ኮሪደሮች ስራዎቻችን ፈጣን እና ፈጠራ መር ልንሆን ይገባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ጥራትን ማስጠበቅ እና ለዜጎቻችን ሁሉ የተመቸ ከባቢን መፍጠር ቅድሚያ የምንሰጣቸው ተግባራት ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

ይህ ፕሮጀክት የሚራመደው በብዙሃን ትብብር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከጅማሮው በስራችን ባገኘነው በጎፈቃድ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

ይህም በዕቅድ እና አፈፃፀም ላይ የታየውን ጥረታችንን እና መልካም ፈቃዳችንን የመጠነ ሆኖ ታይቷል ነው ያሉት።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02EHJTy7SUmhzsNMBG8Gpup8NBdRm9M3EssvzcY2snzntCVyEtriVWvVqnodiXJwASl
👍6635👎5👏1