EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.3K photos
462 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የተራራው ላይ የዓጋመ መስቀል እና ደመራ
***********************

ኢትዮጵያ ውስጥ የመስቀል በአል በተለያዩ ቦታዎች በድምቀት ይከበራል።

በመስቀል በዓል ከቤተስብ እርቆ ያለ እረጅም መንገድ ተጉዞም ቢሆን ቤተሰቡን ይጠይቃል ናፍቆቱን ይወጣል ያለውን ስጦታም በዚሁ በዓል ያበረክታል።

ታዲያ ይህ ትልቅ ሀይማኖታዊ መሰረት ያለው ከቦታ ቦታ ደግሞ የማህበረሰቡ አንድነት ተጠብቆበት የቆየ ባህላዊ አንድምታን የተላበሰ በአል ሲነሳ የዓጋመ መስቀል አይረሳም።

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በትግራይ ክልል በአዲግራት ከተማ የሚከበረው የዓጋመ መስቀል እጅግ በድምቀት ከሚከበሩ እና የተለየ አከባበር ካላቸው የመስቀል በአላት አንዱ ነው። እርግጥ የበዓሉ አከባበር ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቱ እንዳለ ቢሆንም ባሕላዊ ይዘትንም የተላበሰ ነው።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0QX92xsJgojge6sCpx9L3t3tZGUsx5StuNzhQVnGyY2BK71dD54AJDsC91xYt11Vyl
11👍10
ዓለም የእኔም ነው ብሎ የመስቀል በዓልን በቅርስነት ከመዘገበው 11 ዓመታት ተቆጠሩ
*****************

የመስቀል በዓል አከባበር ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ቅርሶች መካከል የመጀመሪያው በዩኒስኮ የተመዘገበ የማይዳሰስ ቅርስ ነው።

ልክ የዛሬ 11 ዓመት ህዳር 2006 ዓ.ም ኢትዮጵያ ተንከባክባ እና ጠብቃ ይዛው የነበረው በዓል የዓለምም በዓል ይሆን ዘንድ ነው የተመዘገበው።

የመስቀል በዓል አከባበር በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ (Intangible) ሆኖ የተመዘገበው በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ በተደረገ ስምንተኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጉባዔ ላይ ነበረ።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid04hV4BPDBrmgdSNmR7RH8tcs8qfsicSzoh6zNABUeywDE6CX8h4ZQJCD4eLnEHu7cl
👍1310👎2
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከግሪክና ሴራሊዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
*******************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ኢትዮጵያ ከግሪክ እና ሴራሊዮን ጋር ያላትን ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ ከግሪኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊኦርጎስ ጀርፐትራይተስ ጋር ባደረጉት ውይይት ግሪክ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

አምባሳደር ታዬ በወቅታዊው የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ለሚኒስትሩ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ፀረ-ሽብር ዘመቻ አጠናክራ ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

በተያያዘ አምባሳደር ታዬ ከሴራሊዮን ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጢሞቲ ካባ ጋር በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኀንነት ዙሪያ መክረዋል።

በውይይቱ ላይም አምባሳደር ታዬ፤ በሶማሊያ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ሥምሪት ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
👍1211
የመስቀል ደመራ በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው

በዓሉ የሀይማኖት አባቶች እና በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በሀዋሳ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በአስረሳው ወገሼ
👍12👏54