EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ዛሬ የ2017 የኢሬቻ ፎረም አካሂደናል።

6ኛው ዙር የኢሬቻ ፎረም አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች፣ አምባሳደሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ የፌደራል፣ ክልልና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ፎሌዎች፣ ዲያስፖራዎች እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት አካሂደናል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃ ማንነቶች ባለ ፀጋ እንደመሆኗ መጠን ህዝባዊ እና ኃይማኖታዊ በዓላት አንድነትን፣ ፍቅርንና የህዝቦች ትብብርን በማፅናት ረገድ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነት፣ የአብሮነት እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት በዓል ሆኖ በመከበር ላይ ይገኛል።

ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አንዱ ምሰሶ ሲሆን የምስጋና፣ የሰላም እና የወንድማማችነት ተምሳሌት ሆኖ የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ከፈጣሪ፣ ከተፈጥሮ እና ከሰው ሁሉ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያድስበት ነው።

በኢሬቻ የተራራቀ ይቀራረባል፤ የተቀያየመም ይታረቃል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0GXf28LFH3EBC79miSMdmfUGLk2i9DyXvbiE6s3bDgvLNPQxvwBBgJ864MaHC1Spql?cft[0]=AZXvyoIz0E9QkVtDPr5lo-9BllbD9prGWUQ-7f1W-GwPfuYxGbnYl16i7_PVQwjdlfluhT0s1DzZkLWxemqLmIqJcOG27bBq2QwwmnRPnfn3TwSIfzqQFQsaWOD53XR_1pRKizkudSLx8j7SLJKa5Ep_MCrfdfxxoz9ph-WPNFPI6g&tn=%2CO%2CP-R
👍237👎5
ለኢሬቻ በዓል የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት ተደርጓል - የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
****************************

የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ለሚጓዙ የበዓሉ ተሳታፊች የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ኢሬቻን ለማክበር ወደ ከተሞቹ ለሚጓዙ የበዓሉ ተሳታፊዎች ከፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቂ የትራንስፖር ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ በአምስቱም መግቢያ በሮች ወደ በዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሚያደርሱ ከአዲስ አበባ ሲቲ ባስ 907 የከተማ አውቶቡሶች እንዲሁም 400 የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶቡሶች መዘጋጀታቸውንም ጠቁሟል፡፡

በቢሾፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም 150 ሀገር አቋራጭና መለስተኛ አውቶቡሶች መዘጋጀታቸውን አመላክቷል፡፡

በአጠቃላይ ታክሲዎችን ሳይጨምር ለበዓሉ አገልግሎት የሚሰጡ 1 ሺህ 457 ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
👍1814👎11👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
****************************

የተከበርከው የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ እንኳን አስቸጋሪውን የክረምት ወቅት አልፈህ ለብሩሁ ብራ ተሸጋገርክ!
ኢሬቻ ዕርቅ ነው፤ ፈጣሪ ደግሞ ዕርቅ ይወዳል። የተጣሉ ሰዎች ቂም ይዘው ለኢሬቻ ወደ መልካ አብረው አይወርዱም። ኢሬቻ መትረፍረፍ ነው! ኢሬቻ ምስጋና ነው! ኢሬቻ ልምላሜ ነው!
ለምለም ሣር ክብርን ፣ ፍቅርን እና መልካም ምኞትን ይወክላል። ብራ ሽግግር ነው፤ ያለፈውን ወደኋላ ትተን ወደ አዲስ ተስፋ በንጹሕ ኀሊና እንሻገራለን፡፡ ከሕዝቡ እሴት ውስጥ ጎልቶ የሚታየውም ይህ ነው። ኢሬቻ አንድነት ነው። ኢሬቻ ኅብረት ነው። ከኢሬቻው መልካ የሚቀርም ሆነ ወደ ኋላ የሚል የለም። አባቶችና እናቶቻችን አቆይተው ያወረሱን እሴት ማዳላት የለውም። ሰው ሁሉ እኩል ነው።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02bEL6g1NiBCN1i2sdmHNKdcRg5yUeGRvSCMyzbHXneu7W6NFTPUkXbubeaQojN6Wzl?cft[0]=AZWHmKRdmvlDjRcoVO8IYeLnKAhksg1svHIv4HJI1pprZErYWIzh38MsSWdgH5cqtLZ63n8IZVl48BYtLNm0q9ruGOcZQSPxsCqCslPdmG2gn81wqjMCIc8-tFZ7uWNM76GhOA6rJ6dWCLbCc8iDzhoJ&tn=%2CO%2CP-R
👍42👎1410
እንኳን ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን ፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*******

የሰላም፣ የአንድነትና የብራ ንጋት መልካም ምኞት ምልክት የሆነው ኢሬቻ፤ የኦሮሞ ህዝብ በጋራ ወጥቶ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ትልቅ በዓል ነው።

ዝናብ ሰጥቶ ያበቀለውን ፈጣሪ፣ የክረምቱን ጎርፍና በረዶ በሰላም አሳልፎት ብሩህ በሆነና በተስፋ ወደ ተሞላው ብራ ያሻገረውን ፈጣሪ፤ ለማመስገን ወደ መልካ (ወንዝ) ወጥቶ የኢሬቻን ስርዓት ይፈጽማል።

ብራ ለፍጥረት ሁሉ ልዩ ነው። ለሁሉም የሚተርፍ ነገር አለው። ብራ ምድሩ በልምላሜ ተሞልቶ፣ በአበቦች ውበት አጊጦ፣ ጋራው ሸንተረሩ ዓይንን የሚማርክበት ወቅት ነው። የአበቦች መዓዛ አካባቢን የሚያውድበት ጊዜ ነው።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0TVUdP2g4AqhPbTaGn38UGztp8CDCWZn8ZqxGhgpE1tVZscjqQ9MokyNw9EcJHbdnl
👍245👎4
ባህላዊና ትውፊታዊ ቅርሶቻችን የሀገር ግንባታ መሳሪያ ሆነው እንዲያገለግሉ አበክረን እንሰራለን፡-አቶ አደም ፋራህ
********

ሕዝባዊ በዓላት በሕዝቡ ባለቤትነት ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፉ፣ ማህበራዊ ትስስር እንዲፈጥሩ፣ የሀገር ግንባታ መሳሪያ ሆነው እንዲያገለግሉና ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን እንዲያጠናክሩ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አመታት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።

በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ያሉ የሕዝብ ሀብት የሆኑ የጋራ እሴቶችና ባህሎች የሚንፀባረቅባቸውን በዓላት ተገቢውን ክብርና ትኩረት እንዲያገኙ በማድረግ በሰራነው ስራም የሀገራችንን ህብረ ቀለማዊ ሀምራዊነት ከሀገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያሳዩ የሚችሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/955238913296955
👍248👎3
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት በመጪው ሰኞ ይካሄዳል
*****************

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

በኢፌዴሪ ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት ስራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ አስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0bp5RRrVEUN2kVSqcT1T6eSUqVYXWiPcBcwiKEwM9PZF4uTGW3F9mW3Ea38J6VvjLl
👍114👎2
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የኢሬቻ በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
********************

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የኢሬቻ በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

መላዉ የኦሮሞ ህዝብ ሆይ፤ እንኳን የምስጋና፤ የሰላምና የአንድነት በዓል ለሆነው የኢሬቻ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

የገዳ ሥርዓት አንዱ አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በኦሮሞ ህዝብ ባህል፤ እምነትና ማንነት ትልቅ ቦታ ያለው፤ በአንድነትና በፍቅር በልዩ ድምቀት የሚከበር ታላቅ የምስጋና በዓል ነው፡፡ https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0dyn3btYjBikmw5mq1eTypxVJbrJ96evz2TYL1AnEByNsY9R9xMDzhWBodnzERypfl
👍98👎3
ኢሬቻ የልምላሜና ተስፋ አመላካች መጻኢን ለስኬት ማዘጋጀት በመሆኑ ሁላችንም ከዚህ በዓል ዕሴቶች ብዙ በመማር፣ያሉንን አቅሞች አሰባስበን ተስፋን መያዝ ያሰፈልጋል፡-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
***************

ኢሬቻ የልምላሜና ተስፋ አመላካች መጻኢን ለስኬት ማዘጋጀት በመሆኑ ሁላችንም ከዚህ በዓል ዕሴቶች ብዙ በመማር፣ ያሉንን አቅሞች አሰባስበን ተስፋን መያዝ ያሰፈልጋልሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የኦሮሞ ህዝብ ባህላዊ ፣ ታሪካዊ፥ የምስጋናና የፍቅር፥ የደስታናየሰላም ፣ የእርቅናየወንድማማችነትእና እህትማማችነት ተምሳሌት የሆነዉ ኢሬቻ በዓል - ለህብረ ብሔራዊ አንድነታችን የነገ ተስፋ የብርሃን ጮራ ነው ።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0JXrbRyHUpksw7rwPK7gd9FtKpCenNgsu6gKyjNaTnwV3Nw9dS6h9ZPmejJRaNuqAl
8👍7👎4
በካሳንቺስ አካባቢ ከ400 በላይ የግል ባለይዞታ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ ተረከቡ
******************

በካሳንቺስ አካባቢ 444 የግል ባለይዞታ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ ተረክበዋል።

በቀበሌ ቤት የሚኖሩ የልማት ተነሺዎች ደግሞ ግልፅና ይፋዊ በሆነ መልኩ እጣ በማውጣት የኮንዶሚኒየምና የመንግስት መኖሪያ ቤቶችን እየተረከቡ መሆኑ ተገልጿል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0tMhv8hLt4GVWSV6T4J8NxrNMiAnSrGri6Dx3yuL7prFoEd3HArmwXjRLa4dZcH1al
👍7👎1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክ አስተላለፉ
***************

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክ አስተላልፈዋል።

የከንቲባዋ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የኢሬቻ በዓል የክረምቱ ጭጋግ አልፎ ብራ ሲሆን፣ ወንዞች ጎድለው ምድር አረንጓዴ ለብሳ በአበቦች ስትዋብ፣ ቡቃያው ደረስኩ ደረስኩ ሲል፣ ክረምቱ ወደ ጸደይ ሲሸጋገር ተለያይቶ የቆየው ሁሉ የሚገናኝበት የአንድነት እና የወንድማማችነት መገለጫ በዓል ነዉ።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02zm8RakJE1azr2ugdMyYzAkcPBqrJY4zTCoFDXR6JEZ5t9kaCYC5oeLKSqiTVESExl
14👎9
የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት ወጥቶ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበትና አብሮነትን የሚያጠናክርበት እሴት ነው፡- ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
*********

የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት ወጥቶ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበትና አብሮነትን የሚያጠናክርበት እሴት ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ አሻድሊ በመልዕክታቸውም፣ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት ወጥቶ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበትና አብሮነትን የሚያጠናክርበት እሴት መሆኑን ገልጸዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0n6N5YRLhNTeuPKwGZVo2Yupzp73Vr9FdzhaTV2o1uvrYjzBtxsJVaDHoG1hGu8t3l
👍137👎2
“ካለፈው መልካም ነገር እንወስዳለን፤ ያለፈው የሚወቀስበትን እያስተካከልን እንዳንወቀስ አድርገን እንሠራለን። የሰውን ልጆችን በእኩል ማየትን ከገዳ እንማራለን”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍33👎87
የሐረሪ ክልላዊ መንግስት ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
*******************

የሐረሪ ክልላዊ መንግስት ያስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

የሐረሪ ክልላዊ መንግስት የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅ፣ የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነት እና የአንድነት ማሳያ ለሆነው የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቱን ያስተላልፋል።

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በታላቅ በድምቀት የሚከበረው የኢሬቻ በዓል በመስከረም ወር ከክረምት ወደ በጋ ፣ ከጭለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን በማሰብ ለፈጣሪ ምስጋናን ለማቅረብ የሚከበር የአደባባይ በዓል ነው።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0ckgWqBrYf3i6ue1tBGyrzS51kkH7X1echSD6Seubu1dRrzNcvP9FSzvE9y28xFEFl
👍143👎3
ኢሬቻ ከልዩነት ይልቅ አንድነት የሚንፀባረቅበት፣የምስጋና፣ የእርቅና ሠላም በዓል ነው፡- ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
*************

ኢሬቻ ከልዩነት ይልቅ አንድነት የሚንፀባረቅበት፣የምስጋና፣ የእርቅና ሠላም በዓል ነው ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሯ የሰላም፣የፍቅር፣የእርቅ እና የአንድነት ማሳያ ለሆነው የኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ኢሬቻ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር አንድነትን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል እንደሆነ ገልፀዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02gGFMUW9BsKawYNSE5GzKbcuJ8ve1ynfpum2bAcdE6ThFKzzGmpVhst5EELgiDeael
👍164👎4👏1
ፍቅር እና መተሳሰብ የሚነግስበት በዓል
📷 በአሰግድ ሲሳይ
#etv #EBC #ኢሬቻ
24👍17👎15