EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
38.2K photos
458 videos
80 files
13.1K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የጎዴ ሼክ ኢብራሂም አብደላ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀው ከፈቱ
****************

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በ300 ሚልዮን ብር ወጪ ማስፋፊያ የተደረገለት የጎዴ ከተማ ሼክ ኢብራሂም አብደላ አጠቃላይ ሆስፒታል እና አዲስ የተገነባውን የኦክስጂን ማዕከል መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ሆስፒታሉና የኦክሲጂን ማምረቻ ማዕከሉ ከሚሰጡት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ባሻገር መንግሥት ለክልሉ የጤና ዘርፍ መሻሻል እያደረገ ያለውን ጥረት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ሆስፒታሉና የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከሉ በጎዴ ከተማ ሥር የሚገኙ የጤና ማዕከላትን ጨምሮ በሸቤሌና አጎራባች ዞኖች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የጎላ ጠቀሜታን ያበረክታል ያሉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሳ አህመድ ናቸው።

የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከሉ በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከል ቀጥሎ በክልሉ ሁለተኛው እንደሆነና በቀን 150 ሲሊንደሮችን የማምረት አቅም እንዳለውም ዶ/ር ሙሳ አክለው ገልፀዋል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0gA3Z1nant8HNcACtfvhXhzArzDghwQmN7aK3ZgaGNMtzhNsHciyEvXYmYm3Va6Frl
👍3515
ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር።

ሃሳብ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ባደረገው ነጋድራስ የስራ ፈጠራ ውድድር ከምዕራፍ ሶስት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የታይትል ስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ኢቢሲ ወደ ይዘት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ ከይዘት ስራዎች አንዱ የሆነው ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር ከህዳር 1 ጀምሮ ይቀርባል፡፡

አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሃሳቦች ወደ ፊት እንዲመጡና በሀገር ኢኮኖሚ ላይም ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ኢቢሲ ሁልጊዜም ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡

ከሀገር ልማት ጀርባ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዚህ ፕሮግራም የታይትል ስፖንሰርሽፕ ስምምነትን ከኢትዮጰያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ከማድረግ ባለፈ ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ ቁርጠኝነቱን በተግባር አሳይቷል።

በስምምነቱ መሠረት የውድድሩ ሽልማት ወደ ላቀ ደረጃ የተሸጋገረ ሲሆን አሸናፊዎች ከሚያገኙት የገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ማስጀመሪያ የገንዘብ ብድር ያለማስያዣ የሚያገኙ ይሆናል፡፡

ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር ከእሁድ ህዳር 1 ቀን 2017 ጀምሮ ከቀኑ 8 ሰዓት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና ቻናል በየሳምንቱ ይቀርባል፡፡

#etv #EBC #cbe #የኢትዮጵያንግድባንክ #ነጋድራስ #CBE #Ethiopian #Commercial_bank_of_Ethiopia #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ስራፈጠራ #ነጋድራስ_የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ_የሥራ_ፈጠራ_ውድድር #negadras
👍252👏1
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩሲያ አቻቸው ጋር ተወያዩ
********************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስሮቹ ውይይቱን ያካሄዱት ከመጀመሪያው የሩሲያ አፍሪካ የሚኒስትሮች አጋርነት ፎረም ጎን ለጎን ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
👍236
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ እና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወልወል ድህረ-ምረቃ እና የ25ኛ ሰላም ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው
**********************

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ እና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወልወል ድህረ-ምረቃ እና የ25ኛ ሰላም ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ይገኛል።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ ጄኔራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ተመራቂ ዕጩ መኮንኖች በማሠልጠኛ ማዕከሉ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩና የሚጠበቅባቸውን ሥልጠና ወስደው ያለፉ መሆናቸው ተገልጿል።

ይመር አደም
👍1912👏3👎2
ኢትዮጵያ ዕድገት ተኮር የኢኮኖሚ ሪፎርም እያካሄደች ትገኛለች - ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
**************************

ኢትዮጵያ ዕድገት ተኮር የኢኮኖሚ ሪፎርም እያካሄደች እንደምትገኝ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ሪፎርሙ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እና የግል ዘርፉን ተሳትፎ እንደሚያበረታታም ጠቁመዋል፡፡

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና የንግድ ሚኒስትሮች 15ኛ ጉባኤ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጉባኤው የጋራ ግቦችን ውጤታማ የሚያደርጉ አቅጣጫዎችን ለማመላከት፣ ችግሮችን ለመፍታት እና ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እንደሚያግዝም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና በአባል ሃገራት መካክል ንግድን በማሳለጥ ኢንዱስትሪያላይዜሽንን በመገንባት ሂደት ውስጥ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
👍186
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን ለኮሚሽኑ አስረከቡ
*********************

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክበዋል፡፡

ኮሚሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሲያካሂድ የቆየውን የአጀንዳ ልየታ መርሐ-ግብር አጠናቋል፡፡

የክልሉ ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ እንዲሁም ለኮሚሽነር ዘገየ አስፋው እና ሙሉጌታ አጎ አስረክበዋል።

ላለፉት 7 ቀናት በክልሉ በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የማኀበረሰብ ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አካላት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና የሲቪል ማኀበራት ሲሳተፉ ቆይተዋል።

ሰለሞን ከበደ
👍13👏21
መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በላቀ ደረጃ የማስጠበቅ አስተማማኝ ብቃት ላይ ይገኛል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
*************************

መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም በላቀ ደረጃ የማስጠበቅ አስተማማኝ ብቃት ላይ እንደሚገኝ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡

ሠራዊቱ የኢትዮጵያን የዕድገት ጉዞ በበጎ የማይመለከቱ ታሪካዊ ጠላቶችን እና የውስጥ ተላላኪ ኃይሎችን አፍራሽ ተግባር በታላቅ ብቃት እያከሸፈ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊት የጠላቶችን እና የቅጥረኞችን ሴራ በማሸነፍ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዕድገት ጉዞ ከግብ እንድታደርስ በሚያስችለው ብቃት ላይ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ እና የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የወልወል ድህረ-ምረቃ እና የ25ኛ ሰላም ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ ጄኔራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
👍2210👏2