EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም በቢሾፍቱ የ5ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት አስጀመረ
***************

ኢትዮ ቴሌኮም በቢሾፍቱ ከተማ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጨረሻው ፈጣን የሆነውን የአምስተኛ ትውልድ (5ጂ) ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት አስጀምሯል።

በቢሾፍቱ ከተማ የቱሪዝም ዘርፉን ወደላቀ ደረጃ ለማሻገር ያስችላል የተባለው የ5ጂ አገልግሎቱን የቢሾፍቱ ከተማና የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራሮች በይፋ አስጀምረዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህወት ታምሩ የ5ጂ አገልግሎት በቢሾፍቱ ከተማ መጀመሩ ከተማዋ በቱሪዝም፣ በንግድና በሌሎችም ዘርፎች ከፍተኛ ዕድገት ለማምጣት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማዋ የ5ጂ አገልግሎት መጀመር ስማርት ቢሾፍቱን ለመገንባት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጨረሻው ፈጣን የሆነው የ5ጂ አገልግሎት በከተማዋ መጀመር የቢሮ ስራዎችን ለማቀላጠፍ፣ ለተገልጋዩ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት፣ ስማርት ሲቲን ለመገንባት፣ የቢሾፍቱን የቱሪስት መስህብነት አቅም ለማሳደግና በርካታ አገልግሎቶችን ለማከናወን የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።

130 ዓመታት ለህዝቡ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ኢትዮ ቴሌኮም ዓለማችን የደረሰችበትን የ5ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለማስጀመር እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በሐምራዊት ብርሃኑ
👍324👏4
አቶ እንዳሻው ጣሰው በዱባይ ለሀላባ ስታዲየም ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አስጀመሩ
**************

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ዱባይ በመገኘት ለሀላባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አስጀምረዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በተባበሩት አረብ ኢምሬት የሀላባ ማህበረሰብ አባላት፣ የልማት አጋሮች እንዲሁም የክልሉና የሀላባ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
👍274
በትግራይ ክልል የትምህርት ዘርፉ ዳግም እንዲያንሰራራ በሚደረገው ጥረት የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፦ አቶ ጌታቸው ረዳ
**********

መቐለ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማጠናከር በሚያደርገው ጥረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ አስታወቁ።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ-ግብር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸው 2729 ዕጩ ተማሪዎች ለ30ኛ ጊዜ አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ቀን ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 1950 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 22 በሦስተኛ ዲግሪ እና 664 በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ (93) የሕክምና ዶክተሮች ናቸው።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02SkU5yZyHTkH5eRKCRcBptWKL9FGyEy4LaBmPnswH8gdxuJfoENjcqPtZ9GSorssul
👍311
ሻምፒዮኑ ማንቸስተር ሲቲ በብራይተን አልቢዮን 2ለ1 ተሸነፈ
****

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከሜዳው ውጭ ብራይተን አልቢዮንን የገጠመው ማንቸስተር ሲቲ 2ለ1 ተሸንፏል።

ማንቸስተር ሲቲ ኮቫቲች በግሩም ሁኔታ ያቀበለውን ኳስ በመቀበል ሃላንድ በ23ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ እስከ 78ኛው ደቂቃ ድረስ 1ለ0 መምራት ችሎ ነበር።

ሆኖም ለብራይተን አልቢዮን በ2ኛው መደበኛ የጨዋታ ክፍ ጊዜ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ፔድሮ በ78ኛው ደቂቃ የአቻነቷን ግብ አስቆጠረ።

ከ5 ደቂቃ በኋላ በ83ኛው ደቂቃ ደግሞ ኦሪሌ 2ኛዋን ግብ በማስቆጠር ብራይተኖች ሲቲን በሜዳቸው 2ለ1 ማሸነፍ ችለዋል።

ብራይተን በ11 ጨዋታ አሁን በሊጉ ያለውን ደረጃ ከፍ ማድረግ ችሏል።

ሲቲ የዛሬ ምሽቱን ጨዋታ ማሸነፍ ባለመቻሉ የሊጉ መሪ መሆን የሚችልበትን ዕድል አምክኗል።

ሊጉን በ25 ነጥብ እየመራ ያለው ሊቨር ፑል ዛሬ ማታ 5 ሰዓት በሜዳው አስቶን ቪላን ይገጥማል።

በላሉ ኢታላ
👍37👏65
ዛሬ የበሰቃን ሐይቅ ድብቅ ውበት ገልጠናል፤ የተገለጠው ምሥጢርም 'ቤኑና መንደር' ይሰኛል
**

ከመተሃራ ከተማ አቅራቢያ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቤኑና መንደር' ከእሳተ ገሞራ ቅሪት መልክዓ ምድር ገጽታው ወደ ሰላምን የሚያጎናፅፍ የመዝናኛ መዳረሻ እና አረንጓዴ የእርሻ ምድርነት በአስደናቂ አኳኋን ተለውጧል ሲል የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

#PMOEthiopia
👍43👏1110