EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ዛሬ የበሰቃን ሐይቅ ድብቅ ውበት ገልጠናል፤ የተገለጠው ምሥጢርም 'ቤኑና መንደር' ይሰኛል
**

ከመተሃራ ከተማ አቅራቢያ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቤኑና መንደር' ከእሳተ ገሞራ ቅሪት መልክዓ ምድር ገጽታው ወደ ሰላምን የሚያጎናፅፍ የመዝናኛ መዳረሻ እና አረንጓዴ የእርሻ ምድርነት በአስደናቂ አኳኋን ተለውጧል ሲል የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

#PMOEthiopia
👍43👏1110
"ለማየት እንደሚናፈቅ ሩቅ ምድር ግን ደግሞ በይቻላል መንፈስ ዕውን መሆን የቻለ፤
ምስራቃዊቷ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ከፍታ ማሳያ፤ የተፈጥሮ ውበት ምስጢር፣ ሩቅ የሚያስቡ ብሩህ አዕምሮዎች ትሩፋት እና የሚሰሩ እጆች ድምር ውጤት፤ የመቻል ልክ፡፡
በሰቃ!"

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
26👍15👏4
ጎግል ፕሌይ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል ጀመረ
*************

የጎግል ፕሌይ (Google Play) አልሚዎች ምዝገባ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል ጀምሯል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጉዳዩን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት፤ የጎግል ፕሌይ የአልሚዎች ምዝገባ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል መጀመሩ ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ ተጽእኖ የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ይህ ምዕራፍ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ባለቤቶች መተግበሪያዎቻቸውን በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ ዲጂታል መድረኮች ላይ እንዲያትሙ አዲስ እድሎችን እንደሚከፍትም ገልፀዋል።

መንግስት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት በርካታ ተነሳሽነቶችን በመተግበር እየሰራ መሆኑን ገልጸው ይህ አዲስ ጅማሮ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ነው ብለዋል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0gsDZmRkvic1LCDhw1sF8pWdG84jyF4GK7VesH511NbRnMmkTnsUQ5YXZnrdroMrFl
👍1715
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ትልቁ ተራራ መገኛ ወደ ሆነው ኪሊማንጃሮ መብረር ሊጀምር ነው
**************

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ትልቁ ተራራ መገኛ ወደ ሆነው ኪሊማንጃሮ በኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን መብረር ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ፤ የአፍሪካ ትልቁ ተራራ መገኛ ወደሆነው ኪሊማንጃሮ በዛሬው ዕለት የአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ከፍ ብለን ለመብረር ዝግጅታችንን አጠናቅቀናል ብሏል።
👍38👏53
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ቤኑና መንደር የ'ይቻላል' እምነት ቋሚ ምስክር ነው"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍164
በሁሉም ውድድሮች ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን አንድ ነገር ለማግኘት ጥረታችንን እንቀጥላለን፦ የሊቨርፑል አሰልጣኝ
****

ትላንት ምሽት በተካሄደ 11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ሊቨርፑል አስቶን ቪላን 2 ለ 0 አሸንፎ መሪነቱን በ5 ነጥብ አስፍቷል።

በምሽቱ ጨዋታ ዳርዊን ኑኔዝ በ20ኛው ደቂቃ የመጀመሪያዋን ግብ ሲያስቆጥር ሞሀመድ ሳላህ በ84ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሮ ሊቨርፑል በድምሩ 2ለ0 አሸንፏል።

የክለቡ አሰልጣኝ አርን ስሎት በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ብቻ ሳይሆን በእንግሊዝ የውስጥ ሊግም በውጤት መንገድ ላይ ናቸው።

"ሊቨርፑል በምሽቱ ከአስቶን ቪላ ጋር ያሳየውን ድንቅ ብቃት ባለፉት ሳምንታት አላሰየም ነበር። አስቶንቪላ ግብ እንዳይስቆጠርብን ማድረግ ችለናል" ብለዋል አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት።
https://web.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid0Cs3YhMLg1NVu7mjaajZBbz7zn1f8ysPWqSw9Boj7fdfubSeLwJ5X8S82fBbmpRGhl
👍146