EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) – Telegram
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.4K photos
462 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከእስያ በማገናኘት የጎላ አበርክቶ እንዳለው ተገለፀ
***************

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከእስያ በማገናኘት የጎላ አበርክቶ እንዳለው የሲንጋፖር የጉዞና ጭነት አገልግሎት ወኪሎች ገለፁ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሲንጋፖር ለሀገሪቱ ለተጓዦች፣ የጉዞና የጭነት አገልግሎት ወኪሎች የማበረታቻ ሽልማት መስጠቱ ይታወቃል፡፡

ኢነርጂያ፣ ሲንጋፖር ፖስት ኃ/የተ/የግ/ ማህበር፣ ኤርሰርቭ ግሩፕ፣ ሲቲስቴት ትራቭል፣ እና ኤር ፍራይት ሲንጋፖር እውቅና የተሰጣቸው ተቋማት ናቸው።

የሲቲስቴት ተራቭል ዋና ዳይሬክተር አልበርቶ ሆ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሲንጋፖር ያዘጋጀው ሁነት አየር መንገዱ ምን ያህል ታላቅና እንዴት ውጤታማ እንደሆነ ለመረዳት አስችሎኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከሲንጋፖር ለማስተሳሰር የሚያደርገው አስደናቂ እንቅስቃሴ አድናቆት የሚቸረው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0UW31kyh9nzYLdKWTNyJGx9JXWPxYxGH51vjHrty2U58RGvbAAft5SXgfecRNewQFl
👍265
የጌዴኦ ዞን የቡና ምርት በፎቶ፡-
👍427👏5
ሩድ ቫኔስትሮይ ማንቺስተር ዩናይትድን መልቀቁ ተነገረ
**************

የማንቺስተር ዩናይትድ ረዳት አሰልጣኝ የነበረው ሩድ ቫኔስትሮይ ከክለቡ መልቀቁ ተነግሯል።

ሩድ ቫኔስትሮይ በክለቡ በረዳት አሰልጣኝነት ሲያገለግል የነበረ ሲሆን አሰልጣኝ ቴን ሃግ ከለቀቁ በኋላ ደግሞ በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ያለፉትን አራት ጨዋታዎች መርቷል።

አዲሱ የማንቺስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ክለቡን በይፋ መቀላቀሉ የተገለፀ ሲሆን፤ ሩድ ቫኔስትሮይ የአሰልጣኞች ስታፍ አባል ሆኖ እንደማይቀጥልም ክለቡ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል፡፡
👍295👏3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ገመገመ
*************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባው የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ በጥልቀት ገምግሟል።

በግምገማው በዋናነት የልማት ተነሺዎች የተስተናገዱበትን አግባብ፤ በመንግስት የሚኖሩ የነበሩ የተነሱበት አግባብ፤ መሰረተ ልማት የተሟሉላቸው መሆኑን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የግል ተነሺዎች ደግሞ የካሳ የ3 አመት የቤት ኪራይ እና ምትክ መሬት መውሰዳቸውን፤ የትራንስፖርት አቅርቦት እና የሞራል ካሳ በህጉ መሰረት የተከፈለ መሆኑን የተተነተነ ሪፖርት በየኮሪደሩ አስተባባሪዎች ቀርቦ መገምገሙ ተጠቅሷል።

በግምገማውም ሁሉም ህጋዊ ውል ወይም ሰነድ ኑሯቸው እንዲሁም በመጠለያ በተገኙበት ተጠልለው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ሁሉ የቤት መስተንግዶ እና የቤት መሰረተ ልማቶች በተሟላላቸው እጅግ የተሻለ፣ ንፁህ፣ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉላቸው ቤቶች የተስተናገድ ሲሆን፤ ለመኖር ምቹ አካባቢ ያገኙ ስለመሆኑ እና አንዳንድ ሳይቶች ላይ የመንገድ ደረጃውን ለማሻሻል ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦ ካቢኔው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

ሌሎች ሳይት ላይ አስፈላጊው መሰረተ ልማት ተጠናቆ ነዋሪዎች የየእለት ኑሯቸውን፤ የማህበራዊ ኑሯቸው ሳይበታተን እንደ እድር እና ማህበር ያሉ ማህበራዊ መስተጋብራቸው እንደተጠበቀ መስተናገዳቸው ተጠቁሟል፡፡

https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid025RZAdrmAGL6etrFvwj2NDyiGSgFbvg8mxRUs5uzpQfUz58egVBa6NYPSCp3mVVgjl
👍3913👎5
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው
******************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ እቅዳችንን የከወንበትን መንገድ በመገምገም ጥንካሬዎቻችንን እያስቀጠልን በድክመት የተለዩ ስራዎችን ደግሞ በትኩረት መገምገም ተገቢ ነው ብለዋል።

አያይዘውም በስራዎቻችን ላይ የሚታዩ ድክመቶችን ሳንሸፋፍን መገምገማችን አንዱ የጥንካሬያችን ምንጭ ነው ብለዋል።

በዚህም ብልሹ አሰራር፣ ሌብነት፣ ጉቦኝነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ክፍተት በመፍታት ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት ሁሉም አመራር እንዴት አቅደን ሰራን እንዲሁም ሀላፊነቴን እንዴት ተወጣሁ ብሎ መገምገም ይገባዋል ሲሉ መናገራቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
👍326👏1