ሩድ ቫኔስትሮይ ማንቺስተር ዩናይትድን መልቀቁ ተነገረ
**************
የማንቺስተር ዩናይትድ ረዳት አሰልጣኝ የነበረው ሩድ ቫኔስትሮይ ከክለቡ መልቀቁ ተነግሯል።
ሩድ ቫኔስትሮይ በክለቡ በረዳት አሰልጣኝነት ሲያገለግል የነበረ ሲሆን አሰልጣኝ ቴን ሃግ ከለቀቁ በኋላ ደግሞ በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ያለፉትን አራት ጨዋታዎች መርቷል።
አዲሱ የማንቺስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ክለቡን በይፋ መቀላቀሉ የተገለፀ ሲሆን፤ ሩድ ቫኔስትሮይ የአሰልጣኞች ስታፍ አባል ሆኖ እንደማይቀጥልም ክለቡ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል፡፡

👍29❤5👏3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የሁለተኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ገመገመ
*************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባው የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ በጥልቀት ገምግሟል።
በግምገማው በዋናነት የልማት ተነሺዎች የተስተናገዱበትን አግባብ፤ በመንግስት የሚኖሩ የነበሩ የተነሱበት አግባብ፤ መሰረተ ልማት የተሟሉላቸው መሆኑን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የግል ተነሺዎች ደግሞ የካሳ የ3 አመት የቤት ኪራይ እና ምትክ መሬት መውሰዳቸውን፤ የትራንስፖርት አቅርቦት እና የሞራል ካሳ በህጉ መሰረት የተከፈለ መሆኑን የተተነተነ ሪፖርት በየኮሪደሩ አስተባባሪዎች ቀርቦ መገምገሙ ተጠቅሷል።
በግምገማውም ሁሉም ህጋዊ ውል ወይም ሰነድ ኑሯቸው እንዲሁም በመጠለያ በተገኙበት ተጠልለው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ሁሉ የቤት መስተንግዶ እና የቤት መሰረተ ልማቶች በተሟላላቸው እጅግ የተሻለ፣ ንፁህ፣ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉላቸው ቤቶች የተስተናገድ ሲሆን፤ ለመኖር ምቹ አካባቢ ያገኙ ስለመሆኑ እና አንዳንድ ሳይቶች ላይ የመንገድ ደረጃውን ለማሻሻል ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦ ካቢኔው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።
ሌሎች ሳይት ላይ አስፈላጊው መሰረተ ልማት ተጠናቆ ነዋሪዎች የየእለት ኑሯቸውን፤ የማህበራዊ ኑሯቸው ሳይበታተን እንደ እድር እና ማህበር ያሉ ማህበራዊ መስተጋብራቸው እንደተጠበቀ መስተናገዳቸው ተጠቁሟል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid025RZAdrmAGL6etrFvwj2NDyiGSgFbvg8mxRUs5uzpQfUz58egVBa6NYPSCp3mVVgjl

👍39❤13👎5
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው
******************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ እቅዳችንን የከወንበትን መንገድ በመገምገም ጥንካሬዎቻችንን እያስቀጠልን በድክመት የተለዩ ስራዎችን ደግሞ በትኩረት መገምገም ተገቢ ነው ብለዋል።
አያይዘውም በስራዎቻችን ላይ የሚታዩ ድክመቶችን ሳንሸፋፍን መገምገማችን አንዱ የጥንካሬያችን ምንጭ ነው ብለዋል።
በዚህም ብልሹ አሰራር፣ ሌብነት፣ ጉቦኝነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ክፍተት በመፍታት ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት ሁሉም አመራር እንዴት አቅደን ሰራን እንዲሁም ሀላፊነቴን እንዴት ተወጣሁ ብሎ መገምገም ይገባዋል ሲሉ መናገራቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

👍32❤6👏1
ማስታወቂያ
********
ምቹና ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነውን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶቻችንን ይጠቀሙ!
Tajaajila Baankii Dijiitaalaa Baankii keenyaa mijataa fi amansiisaa ta'etti fayyadamaa.
#Siinqee_Bank #Baankii_Siinqee #ሲንቄ_ባንክ
#EMPOWERED_TOGETHER

👍10
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያን የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የሚያሳይ መካነ-ርዕይ ከፈቱ
*********************
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያን የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የሚያሳይ መካነ-ርዕይ በአዘርባጃን ባኩ መርቀው ከፍተዋል፡፡
መካነ-ርዕዩ ሀገሪቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በአረንጓዴ አሻራ እና በሌሎች የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች እያከናወነችው ያለውን ተግባር ያሳያል፡፡
29ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በአዘርባጃን ባኩ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ዓለም ለአየር ንብረት ለውጥ ተቢውን ትኩረት መስጠት እና ለታዳጊ ሀገራት ተጨባጭ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው “ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ በምግብ ዋስትና እና በቱሪዝም መዳረሻ ሥራዎቿ ሁሉ የችግኝ ተከላ እና የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎችን እያስቀደመች ትገኛለች” ብለዋል፡፡
ሀገሪቱ የተራቆቱ አካባቢዎችን አረንጓዴ ለማልበስ በያዘችው ውጥን እስካሁን ከ40 ቢሊየን ዶላር በላይ ፈሰስ ማድረጓንም አንስተዋል፡፡
በ29ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን እና በረሃማነትን ለመከላከል እየሰሯቸው ያሉ ሥራዎችን ያቀርባሉ፡፡
ተመስገን ሽፈራው

👍21👏2❤1