Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.13K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
የመጻሕፍት አውደርዕይ በኢግዚብሽን ማዕከል

የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 9ኛ ዙር የንባብ ፌስቲቫል “ንባብ ለትውልድ ግንባታ!” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 2016 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል፡፡

ቴሌግራም: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ድረገፅ:   https://eventaddis.com
"ሚውዚኮሎጂ" የቴሌቪዥን ዝግጅት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ(Addis TV) መቅረብ ሊጀምር ነው።

በሄኖክ መሓሪ (መሓሪ ብራዘርስ) እየተዘጋጅ የሚቀረበው "ሚውዚኮሎጂ" የሙዚቃ እና ሙዚቀኞች የቴሌቪዥን ዝግጅት በቅርቡ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ( Addis TV) መቅረብ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጁ ሄኖክ መሓሪ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በ ቃና እና አቦል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለዓመታት ሲቀረብ የቆየው "ሚውዚኮሎጂ" የቴሌቪዥን ዝግጅት ዘወትር እሁድ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (Addis TV) እና በዩቲዩብ አማራጮች ለተመልካቾች ይቀርባል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ሮፍናን እና ክሪስ ብራውን ተጣምሩ !

ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ እና አሜሪካዊው ድምጻዊ ክሪስ ብራውን በአንድ መድረክ ዝግጅታቸውን ሊያቀርቡ ነው።

ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ዓለምአቀፍ ድምጻዊ ክሪስ ብራውን የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ነገ ሰኔ 29 2016 ዓ.ም በአሜሪካ አትላንታ በአንድ መድረክ ሊቀርቡ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

አሜሪካዊው ክሪስ ብራውን ራፐር ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ፣ ተዋናይ እና ተወዛዋዥ ሲሆን በ "አር ኤንድ ቢ" የሙዚቃ ስልት በመላው ዓለም ዝነኛ ከሆኑ ሙዚቀኞች አንደኛው ነው።

ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በ"USA TOUR" በአሜሪካ ከትላንት ጀምሮ የሙዚቃ ስራውን ማቅረብ ጀምሯል።

ይህም የሙዚቃ ዝግጅት ጉዞው የሮፍናን ኑሪ ዘጠኛ(ኖር እና ሐራንቤ) አልበም ከተለቀቀ በኃላ የመጀመሪያው ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ደራሲ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ እና ልጁ ተመረቁ

"ጥበብ ከጲላጦስ" ተከታታይ መጻህፍትን ጨምሮ በልዩ ልዩ መጽሔቶች ጸሐፊነቱ የምናውቀው ደራሲ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ዶ/ር) ከመጀመሪያ ሴት ልጁ ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመርቀዋል።

ኃይለጊዮርጊስ ማሞ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ በፒኤችዲ ዲግሪ ካስመረቃቸው ሶስት ምሩቃን መካከል አንዱ ሆኗል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ  አጠገብ ስለሚገኘው"የይሁዳ አንበሳ" አጭር መረጃን እነሆ !

በምስሉ ላይ የሚገኘውን መረጃ ያንብቡ !

📍ምንጭ: መዲና ዲጂታል መጽሔት

ማስታወሻ: መዲና ዲጂታል መጽሔት ቅጽ አንድ ቁጥር 4 ዲጂታል መጽሔት በነፃ ለአንባቢያን ቀርባለች። የሚከተለውን ሊንክ በመጠቀም መዲና ዲጂታል መጽሔትን ማንበብ ትችላላችሁ።

https://news.1rj.ru/str/Medinamagazine

በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ልትሆኑ ትችላላችሁ።

https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL

https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj
"የጊዜ ሰሌዳ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ "የጊዜ ሰሌዳ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 1 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

በዕለቱም ጸሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮተ መዋዕለ ፣ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል፣ አርቲስት ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ አርቲስት ፈለቀ ካሣ፣ ደራሲ የዝና ወርቁ፣ ደራሲ ሮማን ተወልደብርሃን በክብር እንግድነት ይገኛሉ።

ገጣሚያኑ ቴዎድሮስ ካሣ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ ፌቤን ፋንጮ፣ መሰረት ጌታነህና ሌሎችም የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

"የጊዜ ሠሌዳ" መጽሐፍ በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" የተሰኘ ፊልም ከፊታችን አርብ ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለእይታ ይበቃል ተብሏል።

የዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" የተሰኘ ፊልም ከፊታችን አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የ"ጀስቲሺያ" ፊልም ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ስትሆን አዜብ ወርቁ እና ቅድስት ይልማ በፊልም ጽሑፍ ተሳትፈዋል።

ህሊና ሲሳይ ፣እድለወርቅ ጣሰው ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ቢታኒያ መስፍን ፣ኤደን ግርማና ሌሎችሞ በተዋናይነት ተሳትፈዋል።

"ጀስቲሺያ" የቤት ሰራተኞን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠርን ዓላማ ይዞ የተሰራ ፊልም እንደሆነ ተሰምቷል።

ለተጨማሪው: @EventAddis1
                    @EventAddis1
"የጊዜ ሰሌዳ" መጽሐፍ በብሔራዊ ቴአትር ቤት ተመረቀ!

የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ "የጊዜ ሰሌዳ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ሐምሌ 1 2016 ዓ.ም በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

በዕለቱም ጸሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕለ ፣ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል፣ ደራሲ የዝና ወርቁ፣ወ/ሮ አስቴሮ ወ/ሚካኤል(የመንቢ እናት) እና ሌሎችም በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ገጣሚያኑ ቴዎድሮስ ካሣ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ ፌቤን ፋንጮ፣ መሰረት ጌታነህ፣አስካለ ልቅና፣ ዘካሪያስ አንተነህ የግጥም ስራዎቻቸውን አቅረብዋል።

በሙዚቃው በኩል ተስፋ ፣ ቤቲ አፍሮ ፣ አብርሃም ኸይሩ እና የህብረ ዝማሬ ቡድን አባላት ነበሩ።

የውዝዋዜ ትርዒት በ"ኢትዮጵያን ባህላዊ የውዝዋዜ ቡድን" እና "የሻዳ ትርዒት " በምጣድ ፕሮዳክሽን" ቀርቧል።

"የጊዜ ሠሌዳ" መጽሐፍ በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።

መጽሐፉ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል።

ፎቶ: አቤል ምህረቴ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ሙዚቀኛ ሮፍናን ከክሪስ ብራውን ጋር ያቀርባል የተባለው ኮንሰርት አልተሳካም በአካልም አልተገናኙም ተብሏል።

በአሜሪካ የሙዚቃ ስራዎቹን ሊያቀርብ የሄደው ኢትዮጵያዊው ዝነኛ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ጁላይ 6/2024 በአትላንታ ከክሪስ ብራውን ጋር የሙዚቃ ስራውን በጋራ ያቀርቡ ተብሎ ቢጠበቅም ክሪስ ብራውን የሙዚቃ ስራውን እንዳላቀረበ ሮፍናን ብቻ እንደዘፈነ ተነግሯል።

በርካታ አድናቂ ያለው ሮፍናን ጉዳዩን አስመልክቶ ከኢትዮጲካሊንክ ጋር ቆይታ አድርጓል "እኔ ዘግይቼ ነበር ቦታው ላይ የደረስኩት ከመኪና ወርጄ ቀጥታ ወደ ስቴጅ ነው የወጣውት፣ እነ ክሪስ ብራውን ዘግቶ ነበር የመጡት ከዛ ሰዓቱ በጣም ገፍቶ ስለነበር ክሪስ ብራውን ወደ መድረክ እንዳይወጣ በፖሊስ ተከለከለ እነሱም ግርግር በቦታው እንዳይፈጠር ሄዱ፣ እኔም ቀሪ የሙዚቃ ስራዬን አቅርቤ ዝግጅቱ ተጠናቀቀ፣ እኔ እና ክሪስ ብራውን አልተገናኘንም" ብሏል።

📍መረጃው የ fastmereja ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ሙያዊ ውይይት ነገ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ የወርሐዊ ገለፃና የፓናል ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡

አሁንም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ መርሐግብሮች አንዱ የኾነውን የፓናል ውይይት “የዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ተሳትፎ” በተሰኘ ርእስ በዘርፉ ከፍተኛ ምሑራን አቅራቢነትና አወያይነት ያካሂዳል።

በዕለቱም ፕ/ር አሰፋ ገብረአምላክ፣ፕ/ር አስቻለው መንግስቱ ፣ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ዶ/ር ደረጀ እንግዳ መነሻ ሀሳብ አቅራቢዎች ናቸው።

መርሐግብሩ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ ነገ ሐሙስ ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ይካሄዳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
የሐሙስ መረጃዎች

የሳምንቱን ኪናዊ መረጃዎችን እነሆ:

📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ!

1.አንጋፋዋ ድምጻዊት ሐመልማል አባተ "ራያ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃዋን በቅርቡ ለአድማጮች እንደምታደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የሙዚቃው ግጥምና ዜማ  በቢኒያም ረዳኢ (ሀ ግዕዝ ) ተሰርቷል። በሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግና ማስተሪንጉ ላይ አሌክስ ይለፍ ተሳትፏል።

2.የድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ " ሀገር እና ሰው" የተሰኘ የሙዚቃ ስራ ነገ አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ለአድማጮች ይደርሳል። የሙዚቃው ግጥምና ዜማ የአቡሽ ዘለቀ ሲሆን ሙዚቃ ቅንብሩ ደግሞ የቤካ ነው።

3. "ኦሎምፒክ ኮንሰርት" ተራዘመ። በዚህ ሳምንት ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው "ኦሎምፒክ ኮንሰርት " ለሐምሌ 13 2016 ዓ.ም እንደተራዘመ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከሌብል ዋን ኢንተርቴይመንት ያገኘው መረጀ ያመለክታል።በዚህ ኮንሰርት ላይ አንጋፋዎቹን ድምጻዊያን ንዋይ ደበበ፣ዳዊት መለስን ጨምሮ ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

4.ገጣሚ አስታወሰኝ ረጋሳ በተዋናይነት የሚሳትፈበት " ሔሎ" የተሰኘ ድራማ በቅርቡ በሀገሬ ቴሌቪዥን መተላለፍ ሊጀምር ነው።  በደራሲ እና ዳይሬክተር ሙሴ አበባየሁ የተዘጋጀው ይህ ድራማ በቤባንያ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን የተዘጋጅ ነው። በድራማው ላይ ከአስታወሰኝ በተጨማሪ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ፣ ተስፋብርሃን ገ/ ጻዲቅ ፣ ሳምራዊት ከበደ እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

5.የዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" የተሰኘ ፊልም ከነገ አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የ"ጀስቲሺያ" ፊልም ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ስትሆን አዜብ ወርቁ እና ቅድስት ይልማ በፊልም ጽሑፍ ተሳትፈዋል። ህሊና ሲሳይ ፣እድለወርቅ ጣሰው ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ቢታኒያ መስፍን ፣ኤደን ግርማና ሌሎችሞ በተዋናይነት ተሳትፈዋል።"ጀስቲሺያ" የቤት ሰራተኞን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠርን ዓላማ ይዞ የተሰራ ፊልም እንደሆነ ተሰምቷል።

6. አንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ነብይ መኮንን የሚዘክረበት "ወደ ነብይ" የተሰኘ መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ካዛንቺስ በሚገኙው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተዘጋጅቷል።የፕሮግራሙ አዘጋጆች በዕለቱ አንጋፋውን ኪያኒ የሚዘክሩ መርሐግብሮች አዘጋጅተናል ብለዋል።አንጋፋው ከያኒ ነብይ መኮንን ባሳለፍነው ሳምንት እንዳረፈ ይታወሳል።

7.የኢትዮጵያ ሴት ሠዓሊያንና ቀራጺያን ማህበር ከአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ጋር በመተባባር ያዘጋጁት "በዘመናችን የሠዓሊነት ዕድልና ፈተና" የተሰኘ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በውይይቱ ርዕስጉዳይ ላይም መነሻ ሀሳብ በመምህርና ሠዓሊ በቀለ መኮንን የሚቀረብ ሲሆን ሠዓሊ ኃይሉ ክፍሌ አወያይ ነው ተብሏል።

8.በሥነጥበብ ባለሞያው አብዱላዚዝ ሙሳ የተዘጋጁ የክር ጥበብ  ስራዎች የቀረቡበት " String vibration" የተሰኘ አውድርዕይ ከሰሞኑ ለእይታ በቅቷል። ይህም የሥነጥበብ አውደርዕይ ቦሌ በሚገኘው አትሞስፌር ጋለሪ ውስጥ ለሳምንታት በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ

ቀን: ሐምሌ 4 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

#Last 🙏

በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:

https://eventaddis.com

ቴሌግራም: @EventAddis1