Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.13K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
"የጊዜ ሰሌዳ" መጽሐፍ በብሔራዊ ቴአትር ቤት ተመረቀ!

የገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ "የጊዜ ሰሌዳ" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ሐምሌ 1 2016 ዓ.ም በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።

በዕለቱም ጸሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕለ ፣ አርቲስት አዳነች ወ/ገብርኤል፣ ደራሲ የዝና ወርቁ፣ወ/ሮ አስቴሮ ወ/ሚካኤል(የመንቢ እናት) እና ሌሎችም በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ገጣሚያኑ ቴዎድሮስ ካሣ፣ ባንቺአየሁ አሰፋ፣ ፌቤን ፋንጮ፣ መሰረት ጌታነህ፣አስካለ ልቅና፣ ዘካሪያስ አንተነህ የግጥም ስራዎቻቸውን አቅረብዋል።

በሙዚቃው በኩል ተስፋ ፣ ቤቲ አፍሮ ፣ አብርሃም ኸይሩ እና የህብረ ዝማሬ ቡድን አባላት ነበሩ።

የውዝዋዜ ትርዒት በ"ኢትዮጵያን ባህላዊ የውዝዋዜ ቡድን" እና "የሻዳ ትርዒት " በምጣድ ፕሮዳክሽን" ቀርቧል።

"የጊዜ ሠሌዳ" መጽሐፍ በ103 ገፆች ተቀንብቡ በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

ገጣሚዋ ከዚህ ቀደም "የቃል ሠሌዳ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷ ይታወሳል።

መጽሐፉ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል።

ፎቶ: አቤል ምህረቴ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ሙዚቀኛ ሮፍናን ከክሪስ ብራውን ጋር ያቀርባል የተባለው ኮንሰርት አልተሳካም በአካልም አልተገናኙም ተብሏል።

በአሜሪካ የሙዚቃ ስራዎቹን ሊያቀርብ የሄደው ኢትዮጵያዊው ዝነኛ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ ጁላይ 6/2024 በአትላንታ ከክሪስ ብራውን ጋር የሙዚቃ ስራውን በጋራ ያቀርቡ ተብሎ ቢጠበቅም ክሪስ ብራውን የሙዚቃ ስራውን እንዳላቀረበ ሮፍናን ብቻ እንደዘፈነ ተነግሯል።

በርካታ አድናቂ ያለው ሮፍናን ጉዳዩን አስመልክቶ ከኢትዮጲካሊንክ ጋር ቆይታ አድርጓል "እኔ ዘግይቼ ነበር ቦታው ላይ የደረስኩት ከመኪና ወርጄ ቀጥታ ወደ ስቴጅ ነው የወጣውት፣ እነ ክሪስ ብራውን ዘግቶ ነበር የመጡት ከዛ ሰዓቱ በጣም ገፍቶ ስለነበር ክሪስ ብራውን ወደ መድረክ እንዳይወጣ በፖሊስ ተከለከለ እነሱም ግርግር በቦታው እንዳይፈጠር ሄዱ፣ እኔም ቀሪ የሙዚቃ ስራዬን አቅርቤ ዝግጅቱ ተጠናቀቀ፣ እኔ እና ክሪስ ብራውን አልተገናኘንም" ብሏል።

📍መረጃው የ fastmereja ነው።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ሙያዊ ውይይት ነገ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ የወርሐዊ ገለፃና የፓናል ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡

አሁንም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ መርሐግብሮች አንዱ የኾነውን የፓናል ውይይት “የዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ተሳትፎ” በተሰኘ ርእስ በዘርፉ ከፍተኛ ምሑራን አቅራቢነትና አወያይነት ያካሂዳል።

በዕለቱም ፕ/ር አሰፋ ገብረአምላክ፣ፕ/ር አስቻለው መንግስቱ ፣ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ዶ/ር ደረጀ እንግዳ መነሻ ሀሳብ አቅራቢዎች ናቸው።

መርሐግብሩ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ ነገ ሐሙስ ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ይካሄዳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
የሐሙስ መረጃዎች

የሳምንቱን ኪናዊ መረጃዎችን እነሆ:

📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ!

1.አንጋፋዋ ድምጻዊት ሐመልማል አባተ "ራያ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃዋን በቅርቡ ለአድማጮች እንደምታደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የሙዚቃው ግጥምና ዜማ  በቢኒያም ረዳኢ (ሀ ግዕዝ ) ተሰርቷል። በሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግና ማስተሪንጉ ላይ አሌክስ ይለፍ ተሳትፏል።

2.የድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ " ሀገር እና ሰው" የተሰኘ የሙዚቃ ስራ ነገ አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ለአድማጮች ይደርሳል። የሙዚቃው ግጥምና ዜማ የአቡሽ ዘለቀ ሲሆን ሙዚቃ ቅንብሩ ደግሞ የቤካ ነው።

3. "ኦሎምፒክ ኮንሰርት" ተራዘመ። በዚህ ሳምንት ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው "ኦሎምፒክ ኮንሰርት " ለሐምሌ 13 2016 ዓ.ም እንደተራዘመ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከሌብል ዋን ኢንተርቴይመንት ያገኘው መረጀ ያመለክታል።በዚህ ኮንሰርት ላይ አንጋፋዎቹን ድምጻዊያን ንዋይ ደበበ፣ዳዊት መለስን ጨምሮ ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

4.ገጣሚ አስታወሰኝ ረጋሳ በተዋናይነት የሚሳትፈበት " ሔሎ" የተሰኘ ድራማ በቅርቡ በሀገሬ ቴሌቪዥን መተላለፍ ሊጀምር ነው።  በደራሲ እና ዳይሬክተር ሙሴ አበባየሁ የተዘጋጀው ይህ ድራማ በቤባንያ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን የተዘጋጅ ነው። በድራማው ላይ ከአስታወሰኝ በተጨማሪ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ፣ ተስፋብርሃን ገ/ ጻዲቅ ፣ ሳምራዊት ከበደ እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

5.የዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" የተሰኘ ፊልም ከነገ አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የ"ጀስቲሺያ" ፊልም ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ስትሆን አዜብ ወርቁ እና ቅድስት ይልማ በፊልም ጽሑፍ ተሳትፈዋል። ህሊና ሲሳይ ፣እድለወርቅ ጣሰው ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ቢታኒያ መስፍን ፣ኤደን ግርማና ሌሎችሞ በተዋናይነት ተሳትፈዋል።"ጀስቲሺያ" የቤት ሰራተኞን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠርን ዓላማ ይዞ የተሰራ ፊልም እንደሆነ ተሰምቷል።

6. አንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ነብይ መኮንን የሚዘክረበት "ወደ ነብይ" የተሰኘ መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ካዛንቺስ በሚገኙው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተዘጋጅቷል።የፕሮግራሙ አዘጋጆች በዕለቱ አንጋፋውን ኪያኒ የሚዘክሩ መርሐግብሮች አዘጋጅተናል ብለዋል።አንጋፋው ከያኒ ነብይ መኮንን ባሳለፍነው ሳምንት እንዳረፈ ይታወሳል።

7.የኢትዮጵያ ሴት ሠዓሊያንና ቀራጺያን ማህበር ከአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ጋር በመተባባር ያዘጋጁት "በዘመናችን የሠዓሊነት ዕድልና ፈተና" የተሰኘ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በውይይቱ ርዕስጉዳይ ላይም መነሻ ሀሳብ በመምህርና ሠዓሊ በቀለ መኮንን የሚቀረብ ሲሆን ሠዓሊ ኃይሉ ክፍሌ አወያይ ነው ተብሏል።

8.በሥነጥበብ ባለሞያው አብዱላዚዝ ሙሳ የተዘጋጁ የክር ጥበብ  ስራዎች የቀረቡበት " String vibration" የተሰኘ አውድርዕይ ከሰሞኑ ለእይታ በቅቷል። ይህም የሥነጥበብ አውደርዕይ ቦሌ በሚገኘው አትሞስፌር ጋለሪ ውስጥ ለሳምንታት በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ

ቀን: ሐምሌ 4 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

#Last 🙏

በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:

https://eventaddis.com

ቴሌግራም: @EventAddis1
የፎቶግራፍ አውደርዕይ

ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 23

📍በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የደራሲ ሌሊሳ ግርማ አዲስ መጽሐፍ "ደማቆቹ"

ደራሲ ሌሊሳ ግርማ "ደማቆቹ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የትርጉም መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚያደርስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ደራሲ ሌሊሳ ግርማ ከዚህ ቀደም "አፍሮጋዳ" ፣ "እስቲ ሙዚቃ" ፣ "ይመስላል ዘላለም " እና ሌሎችንም መጻሕፍት ለአንባቢያን አድርሷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አንጋፋው ከያኒ ነብይ መኮንን የሚዘከርበት ሁለት መሰናዶዎች ከሰሞኑ ይካሄዳሉ

አንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ነብይ መኮንን የሚዘክረበት "ወደ ነብይ" የተሰኘ መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ካዛንቺስ በሚገኙው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተዘጋጅቷል።የፕሮግራሙ አዘጋጆች በዕለቱ አንጋፋውን ኪያኒ የሚዘክሩ መርሐግብሮች አዘጋጅተናል ብለዋል።

በሌላ በኩል "ዝክረ ነብይ" የተሰኘ የመታሰቢያ ፕሮግራም ሰኞ ሐምሌ 8 ቀን በዋቢ ሸበሌ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል:: ፕሮግራሙ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በዋቢ ሸበሌ  ሆቴል ከቀኑ 11:00 ጀምሮ ይካሄዳል::በዚህ ፕሮግራም ላይ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ፣በቀለ መኮንን፣ዘነበ ወላ፣ጥበቡ በለጠ፣ ተስፋዬ ማሞና ሌሎችም በመድረኩ ላይ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ምሑራዊ ክርክርና የውይይት መድረክ (Dialogue) የፊታችን ሐሙስ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካባቢ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ ገለጻና የውይይት መድረክ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል::

“ኢትዮጵያ ለምን በምግብ ራሷን ሳትችል ቆየች?” በሚል ርእስ ምሁራዊ ክርክር በዘርፉ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ተመራማሪዎች፣ የመንግሥት አካላትና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተወጣጡ አካላት መካከል ይካሄዳል።

መርሐግብሩ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ ሐሙስ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በደራሲ አዳም ረታ መጻሕፍት ላይ ያተኮር ሥነጽሐፋዊ  ውይይት በሚቀጥለው ሳምንት ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) የሚዘጋጅው " የወር ወንበር" መሰናዶ ላይ በዚህ ወር በደራሲ አዳም ረታ መጻሕፍት ላይ ያተኮር "አዳም ከአለፍ አገደም" የአዳም ረታ ሥራዎች ጥቂት ምልከታ" በሚል ርዕስ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ሐምሌ 13 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 በወመዘክር አዳራሽ ሥነጽሑፋዊ ውይይት እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከወመዘክር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ሥነጽሐፋዊ ውይይት ላይ አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ መነሻ ሀሳብ ያቀርባሉ ተብሏል።

በዝግጅቱ ላይ የሚገኙ ከሆነ ይህንን ቅፅ https://bit.ly/3S45QS2 ይሙሉ ተብለዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"ወደ ነቢይ" የዝክረ ፕሮግራም ዛሬ ይካሄዳል

አንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን የሚዘክረበት "ወደ ነቢይ" የተሰኘ መርሐግብር ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተዘጋጅቷል።

የፕሮግራሙ አዘጋጆች በዕለቱ አንጋፋውን ኪያኒ ነቢይ መኮንን የሚዘክሩ መርሐግብሮች አዘጋጅተናል ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አንጋፋው ጊታሪስት ሰላም ስዩም የተሳተፈበት "አፍሮ ናይል" የተሰኘ አልበም ተለቀቀ

አንጋፋው ጊታሪስት ሰላም ስዩም የተሳተፈበት "አፍሮ ናይል" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም "AfroNile" በተሰኘ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች እንደደረሰ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።

ሙዚቀኛ ዳዊት ብርሃነ እና ጊታሪስት ሰላም ስዩም የተጣምሩበት ይህ አልበም በርካታ ድምጻዊያንን አሳትፏል።

በዚህ "አፍሮ ናይል" በተሰኘው የሙዚቃ አልበም ላይ ድምጻዊኑ ዲባኩሉ ታፈሰ ፣ ሚኪ ሀሴት፣ ሊያ ግርማ፤ጌጥሽ ተስፋዬ በፊውቸርንግ ተሳትፈዋል።

ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እንደተመለከተው ከሆነ በዚህ አልበም ላይ አፍሪካ ዩኒቲ፣ ናፍቆት፣የደስታ እንባ፣አይ ፍቅር ፣ዜም ቲዩን ሪይስ የተሰኙ አምስት ሙዚቃዎች ተካተውበታል።

የሮሀ እና የአይቤክስ ባንድ መስራች የሆነው ጊታሪስት ሰላም ስዩም ከረጅም በኃላ በሙዚቃ አልበም ላይ ተሳትፏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
"በዓሉ ግርማ: ቤርሙዳ" ተውኔት ተቋረጠ

በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፍ የተዘጋጀውና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የመጣው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ከሐሙስ ሰኔ 20 2016 ዓ.ም ጀምሮ "በአንድ ተዋናይ መቅረት" ምክንያት እንደተቋረጠ ኤቨንት ድረገፅ ሰምቷል።

በተውኔቱ ላይ ተሳታፊ የሆነ ባለሞያዎች ተደጋጋሚ መቅረት እና በሁለቱ ቴአትር ቤቶች ማለትም በሀገርፍቅር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤቶች መካከል ያለው የተግባቦት እና አሰራር ችግር ምክንያት "በዓሉ ግርማ: ቤርሙዳ" ተውኔት ሙሉበሙሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መቋረጡን ድረገጻችን ሰምቷል።

የተውኔቱ አዘጋጅ ወድነህ ክፍሌ በማህበራዊ ትስስር ገፁ"በዓሉ ግርማ - ቤርሙዳ" ቴአትር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አይታይም ቆሟል።" ማለቱን ኤቨንት ድረገፅ ተመልክቷል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ አሜሪካ ገባ

ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጪ በመሔድ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካን እንደገባ ከፊልም ባለሞያው ያሬድ ሹመት ማህበራዊ ትስስር ገፁ ተመልክተናል።

አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ “አሸባሪ መረጃዎችን በማጋራት የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት የሚያውክ ተግባር ፈጽመዋል” በሚል ለወራት ታስሮ እንደነበርና ከሳምንታት በፊት በ50ሺ ብር ዋስ ከእስር እንደተፈታ ይታወሳል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ዛሬ በኢትዮጵያ ቡክ ፎረም "በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" መጽሐፍ ላይ ውይይት ይካሄዳል

በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ወንድማማቾቹ አንቷንና ሚሼል ዳባዲን የጉዞ ማስታወሻ በሆነው"በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" መጽሐፍ ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች ዛሬ ሐምሌ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 እስከ 4:00 ውይይት ያደርጋሉ።

https://www.clubhouse.com/invite/XXycJVX7rAdj98OD3qAZ84pN8QeoT2J3jgL:yv5cdmqgNlhRRw54x1RomHaxaiexQBx-WOguphY4hFE

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1