ሙያዊ ውይይት ነገ ይካሄዳል
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ የወርሐዊ ገለፃና የፓናል ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
አሁንም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ መርሐግብሮች አንዱ የኾነውን የፓናል ውይይት “የዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ተሳትፎ” በተሰኘ ርእስ በዘርፉ ከፍተኛ ምሑራን አቅራቢነትና አወያይነት ያካሂዳል።
በዕለቱም ፕ/ር አሰፋ ገብረአምላክ፣ፕ/ር አስቻለው መንግስቱ ፣ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ዶ/ር ደረጀ እንግዳ መነሻ ሀሳብ አቅራቢዎች ናቸው።
መርሐግብሩ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ ነገ ሐሙስ ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ይካሄዳል ተብሏል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

Event Addis Media
Photo
የሐሙስ መረጃዎች
የሳምንቱን ኪናዊ መረጃዎችን እነሆ:
📍መረጃውን ሲጠቀሙ ምንጭ ይጠቀሱ!
1.አንጋፋዋ ድምጻዊት ሐመልማል አባተ "ራያ" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃዋን በቅርቡ ለአድማጮች እንደምታደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የሙዚቃው ግጥምና ዜማ በቢኒያም ረዳኢ (ሀ ግዕዝ ) ተሰርቷል። በሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግና ማስተሪንጉ ላይ አሌክስ ይለፍ ተሳትፏል።
2.የድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ " ሀገር እና ሰው" የተሰኘ የሙዚቃ ስራ ነገ አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ለአድማጮች ይደርሳል። የሙዚቃው ግጥምና ዜማ የአቡሽ ዘለቀ ሲሆን ሙዚቃ ቅንብሩ ደግሞ የቤካ ነው።
3. "ኦሎምፒክ ኮንሰርት" ተራዘመ። በዚህ ሳምንት ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው "ኦሎምፒክ ኮንሰርት " ለሐምሌ 13 2016 ዓ.ም እንደተራዘመ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከሌብል ዋን ኢንተርቴይመንት ያገኘው መረጀ ያመለክታል።በዚህ ኮንሰርት ላይ አንጋፋዎቹን ድምጻዊያን ንዋይ ደበበ፣ዳዊት መለስን ጨምሮ ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
4.ገጣሚ አስታወሰኝ ረጋሳ በተዋናይነት የሚሳትፈበት " ሔሎ" የተሰኘ ድራማ በቅርቡ በሀገሬ ቴሌቪዥን መተላለፍ ሊጀምር ነው። በደራሲ እና ዳይሬክተር ሙሴ አበባየሁ የተዘጋጀው ይህ ድራማ በቤባንያ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን የተዘጋጅ ነው። በድራማው ላይ ከአስታወሰኝ በተጨማሪ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ፣ ተስፋብርሃን ገ/ ጻዲቅ ፣ ሳምራዊት ከበደ እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።
5.የዳይሬክተር ቅድስት ይልማ "ጀስቲሺያ" የተሰኘ ፊልም ከነገ አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል። የ"ጀስቲሺያ" ፊልም ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ ስትሆን አዜብ ወርቁ እና ቅድስት ይልማ በፊልም ጽሑፍ ተሳትፈዋል። ህሊና ሲሳይ ፣እድለወርቅ ጣሰው ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ ፣ቢታኒያ መስፍን ፣ኤደን ግርማና ሌሎችሞ በተዋናይነት ተሳትፈዋል።"ጀስቲሺያ" የቤት ሰራተኞን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ እንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠርን ዓላማ ይዞ የተሰራ ፊልም እንደሆነ ተሰምቷል።
6. አንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ነብይ መኮንን የሚዘክረበት "ወደ ነብይ" የተሰኘ መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ካዛንቺስ በሚገኙው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተዘጋጅቷል።የፕሮግራሙ አዘጋጆች በዕለቱ አንጋፋውን ኪያኒ የሚዘክሩ መርሐግብሮች አዘጋጅተናል ብለዋል።አንጋፋው ከያኒ ነብይ መኮንን ባሳለፍነው ሳምንት እንዳረፈ ይታወሳል።
7.የኢትዮጵያ ሴት ሠዓሊያንና ቀራጺያን ማህበር ከአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ጋር በመተባባር ያዘጋጁት "በዘመናችን የሠዓሊነት ዕድልና ፈተና" የተሰኘ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በውይይቱ ርዕስጉዳይ ላይም መነሻ ሀሳብ በመምህርና ሠዓሊ በቀለ መኮንን የሚቀረብ ሲሆን ሠዓሊ ኃይሉ ክፍሌ አወያይ ነው ተብሏል።
8.በሥነጥበብ ባለሞያው አብዱላዚዝ ሙሳ የተዘጋጁ የክር ጥበብ ስራዎች የቀረቡበት " String vibration" የተሰኘ አውድርዕይ ከሰሞኑ ለእይታ በቅቷል። ይህም የሥነጥበብ አውደርዕይ ቦሌ በሚገኘው አትሞስፌር ጋለሪ ውስጥ ለሳምንታት በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።
አዘጋጅ: ናቲ ማናዬ
ቀን: ሐምሌ 4 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#Last 🙏
በድረገጻችን በተሻለ አቀራረብ ያንብቡ:
https://eventaddis.com
ቴሌግራም: @EventAddis1

የደራሲ ሌሊሳ ግርማ አዲስ መጽሐፍ "ደማቆቹ"
ደራሲ ሌሊሳ ግርማ "ደማቆቹ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የትርጉም መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚያደርስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
ደራሲ ሌሊሳ ግርማ ከዚህ ቀደም "አፍሮጋዳ" ፣ "እስቲ ሙዚቃ" ፣ "ይመስላል ዘላለም " እና ሌሎችንም መጻሕፍት ለአንባቢያን አድርሷል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ደራሲ ሌሊሳ ግርማ "ደማቆቹ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የትርጉም መጽሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን እንደሚያደርስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
ደራሲ ሌሊሳ ግርማ ከዚህ ቀደም "አፍሮጋዳ" ፣ "እስቲ ሙዚቃ" ፣ "ይመስላል ዘላለም " እና ሌሎችንም መጻሕፍት ለአንባቢያን አድርሷል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
አንጋፋው ከያኒ ነብይ መኮንን የሚዘከርበት ሁለት መሰናዶዎች ከሰሞኑ ይካሄዳሉ
አንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ነብይ መኮንን የሚዘክረበት "ወደ ነብይ" የተሰኘ መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ካዛንቺስ በሚገኙው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተዘጋጅቷል።የፕሮግራሙ አዘጋጆች በዕለቱ አንጋፋውን ኪያኒ የሚዘክሩ መርሐግብሮች አዘጋጅተናል ብለዋል።
በሌላ በኩል "ዝክረ ነብይ" የተሰኘ የመታሰቢያ ፕሮግራም ሰኞ ሐምሌ 8 ቀን በዋቢ ሸበሌ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል:: ፕሮግራሙ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ከቀኑ 11:00 ጀምሮ ይካሄዳል::በዚህ ፕሮግራም ላይ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ፣በቀለ መኮንን፣ዘነበ ወላ፣ጥበቡ በለጠ፣ ተስፋዬ ማሞና ሌሎችም በመድረኩ ላይ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ምሑራዊ ክርክርና የውይይት መድረክ (Dialogue) የፊታችን ሐሙስ ይካሄዳል
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካባቢ በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት ያለመ ገለጻና የውይይት መድረክ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል::
“ኢትዮጵያ ለምን በምግብ ራሷን ሳትችል ቆየች?” በሚል ርእስ ምሁራዊ ክርክር በዘርፉ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ተመራማሪዎች፣ የመንግሥት አካላትና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተወጣጡ አካላት መካከል ይካሄዳል።
መርሐግብሩ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ ሐሙስ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ይካሄዳል።

በደራሲ አዳም ረታ መጻሕፍት ላይ ያተኮር ሥነጽሐፋዊ ውይይት በሚቀጥለው ሳምንት ሊካሄድ ነው
በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) የሚዘጋጅው " የወር ወንበር" መሰናዶ ላይ በዚህ ወር በደራሲ አዳም ረታ መጻሕፍት ላይ ያተኮር "አዳም ከአለፍ አገደም" የአዳም ረታ ሥራዎች ጥቂት ምልከታ" በሚል ርዕስ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ሐምሌ 13 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 በወመዘክር አዳራሽ ሥነጽሑፋዊ ውይይት እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከወመዘክር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ ሥነጽሐፋዊ ውይይት ላይ አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ መነሻ ሀሳብ ያቀርባሉ ተብሏል።
በዝግጅቱ ላይ የሚገኙ ከሆነ ይህንን ቅፅ https://bit.ly/3S45QS2 ይሙሉ ተብለዋል።

"ወደ ነቢይ" የዝክረ ፕሮግራም ዛሬ ይካሄዳል
አንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን የሚዘክረበት "ወደ ነቢይ" የተሰኘ መርሐግብር ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ተዘጋጅቷል።
የፕሮግራሙ አዘጋጆች በዕለቱ አንጋፋውን ኪያኒ ነቢይ መኮንን የሚዘክሩ መርሐግብሮች አዘጋጅተናል ብለዋል።

አንጋፋው ጊታሪስት ሰላም ስዩም የተሳተፈበት "አፍሮ ናይል" የተሰኘ አልበም ተለቀቀ
አንጋፋው ጊታሪስት ሰላም ስዩም የተሳተፈበት "አፍሮ ናይል" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም አርብ ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም "AfroNile" በተሰኘ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች እንደደረሰ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
ሙዚቀኛ ዳዊት ብርሃነ እና ጊታሪስት ሰላም ስዩም የተጣምሩበት ይህ አልበም በርካታ ድምጻዊያንን አሳትፏል።
በዚህ "አፍሮ ናይል" በተሰኘው የሙዚቃ አልበም ላይ ድምጻዊኑ ዲባኩሉ ታፈሰ ፣ ሚኪ ሀሴት፣ ሊያ ግርማ፤ጌጥሽ ተስፋዬ በፊውቸርንግ ተሳትፈዋል።
ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እንደተመለከተው ከሆነ በዚህ አልበም ላይ አፍሪካ ዩኒቲ፣ ናፍቆት፣የደስታ እንባ፣አይ ፍቅር ፣ዜም ቲዩን ሪይስ የተሰኙ አምስት ሙዚቃዎች ተካተውበታል።
የሮሀ እና የአይቤክስ ባንድ መስራች የሆነው ጊታሪስት ሰላም ስዩም ከረጅም በኃላ በሙዚቃ አልበም ላይ ተሳትፏል።

"በዓሉ ግርማ: ቤርሙዳ" ተውኔት ተቋረጠ
በውድነህ ክፍሌ ተደርሶ በተሻለ አሰፍ የተዘጋጀውና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ የመጣው "በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ" ተውኔት ከሐሙስ ሰኔ 20 2016 ዓ.ም ጀምሮ "በአንድ ተዋናይ መቅረት" ምክንያት እንደተቋረጠ ኤቨንት ድረገፅ ሰምቷል።
በተውኔቱ ላይ ተሳታፊ የሆነ ባለሞያዎች ተደጋጋሚ መቅረት እና በሁለቱ ቴአትር ቤቶች ማለትም በሀገርፍቅር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤቶች መካከል ያለው የተግባቦት እና አሰራር ችግር ምክንያት "በዓሉ ግርማ: ቤርሙዳ" ተውኔት ሙሉበሙሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መቋረጡን ድረገጻችን ሰምቷል።
የተውኔቱ አዘጋጅ ወድነህ ክፍሌ በማህበራዊ ትስስር ገፁ"በዓሉ ግርማ - ቤርሙዳ" ቴአትር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አይታይም ቆሟል።" ማለቱን ኤቨንት ድረገፅ ተመልክቷል።
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ አሜሪካ ገባ
ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጪ በመሔድ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካን እንደገባ ከፊልም ባለሞያው ያሬድ ሹመት ማህበራዊ ትስስር ገፁ ተመልክተናል።
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ “አሸባሪ መረጃዎችን በማጋራት የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት የሚያውክ ተግባር ፈጽመዋል” በሚል ለወራት ታስሮ እንደነበርና ከሳምንታት በፊት በ50ሺ ብር ዋስ ከእስር እንደተፈታ ይታወሳል።

ዛሬ በኢትዮጵያ ቡክ ፎረም "በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" መጽሐፍ ላይ ውይይት ይካሄዳል
በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ወንድማማቾቹ አንቷንና ሚሼል ዳባዲን የጉዞ ማስታወሻ በሆነው"በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" መጽሐፍ ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች ዛሬ ሐምሌ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 እስከ 4:00 ውይይት ያደርጋሉ።
https://www.clubhouse.com/invite/XXycJVX7rAdj98OD3qAZ84pN8QeoT2J3jgL:yv5cdmqgNlhRRw54x1RomHaxaiexQBx-WOguphY4hFE
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ወንድማማቾቹ አንቷንና ሚሼል ዳባዲን የጉዞ ማስታወሻ በሆነው"በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራሮች ቆይታዬ" መጽሐፍ ዙሪያ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞችና ተሳታፊዎች ዛሬ ሐምሌ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 እስከ 4:00 ውይይት ያደርጋሉ።
https://www.clubhouse.com/invite/XXycJVX7rAdj98OD3qAZ84pN8QeoT2J3jgL:yv5cdmqgNlhRRw54x1RomHaxaiexQBx-WOguphY4hFE
ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
ራኬብ አለማየሁ አዲስ የቲቪ ዝግጅት ልትጀምር ነው
የቀድሞዋ "የእሁድን በኢቢኤስ" ፕሮግራም አቅራቢ ራኬብ አለማየሁ "ራኪ በዚህ ሳምንት" የተሰኘ የቴሌቪዥን ፕርግራም በአባይ ቴሌቪዥን ከቅዳሜ ሐምሌ 13 2016 ዓ.ም ጀምሮ ማቅረብ ልትጀምር እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
"ራኪ በዚህ ሳምንት" በሳይኮሎጂ ፣ በፍቅርና በማሕበራዊ ሕይወት አንደምታ አልፎም በጤና፣ በስነምግብ፣ በፋሽን፣ በውበት ነክ እና በተለያዩ የህይወት ዘይቤዎች እንግዶችን በመጋበዝ የሚቀረብ ፕርግራም ነው ተብሏል።

አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ
ተዋናይ፣ ደራሲ፣ ዳይሬክተር እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢው ነፃነት ወርቅነህ ለህክምና ወደ ሀገረ ህንድ መሄዱን የሚገልጽ ማስታወሻ በግል የፌስቡክ ገፁ ማጋራቱ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎች ለአርቲስቱ መልካም ምኞታቸውን ሲገልፁ ነበር።
ገሚሶቹ ደግሞ አርቲስቱ ላይ ያጋጠመው የጤና እክል የከፋ ይሆናል የሚል ስጋታቸውን ጭምር ሲገልፁ እንደነበር ይታወሳል።
ያም ሆኖ ግን አርቲስቱ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መልዕክቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በተጨማሪም መልካም ምኞታቸውን ለተመኙለት ምስጋናውን በማቅረብ በጥቂት ቀናት ውስጥ የህክምና ክትትሉን አገባዶ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለስ ተናግሯል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኀበር
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ሐምሌ 6 2016 ዓ.ም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ በሦስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በጉባኤውም ያለፈው ሁለት ዓመት የሥራ ክንውን እና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ግምገማ ተደርጎበታል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ማኅበሩን በፕሬዝዳንትነት ያገለገለው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ባለበት የሥራ መደራረብ ምክንያት ማኅበሩን ተተኪዎች እንዲመሩት በመጠየቁ በጠቅላላ ጉባኤው በክብር ተሸኝቷል።
በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በሥራ ላይ ያሉት የሥራ አስፈጻሚ አባላት የቆይታ ጊዜያቸው ስለተጠናቀቀ የተጓደሉትን ጨምሮ እንደ አዲስ የዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ተካሂዷል። በዚህም መሰረት ሶስት ነባር ሥራ አስፈጻሚዎችና ስምንት አዳዲስ አባላት በእጩነት ቀርበው ምርጫ ተደርጓል። በጉባኤው ለምርጫ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ዘጠኝ ሥራ አስፈጻሚዎች በጠቅላላ ጉባዔው በድምፅ ምርጫ ተመርጠዋል።
በጠቅላላ ጉባዔው ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተመጡት እታገኘሁ መኮነን፣ ትብለፅ ተስፋዬ፣ ሲሳይ ሳህሉ፣ሳሙኤል አባተ፣ ዳግማዊት ግርማ፣ዳዊት ታደሰ፣መርሻ ጥሩነህ፣ማናዬ እውነቱ፣ዳዊት አስታጥቄ ናቸው።
ከተመረጡት ዘጠኝ ሥራ አስፈጻሚዎች መካከል በተደገው የፕሬዝዳንት የምርጫ ውድድር ጋዜጠኛ እታገኘሁ መኮነን አብላጫ ድምጽ በማግኘት የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሆና ተመርጣለች፡፡
አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ የማኅበሩን ጠንካራጰ ጎኖች በማስቀጠልና ከአባላት ጋር በመተባበር ለጋዜጠኞች መብት መከበር እና ለኢትዮጵያ ሚዲያ አጠቃላይ ዕድገትና ነፃነት እንደሚሰራ ቃል ገብቷል።

9ኛው የኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ባለሞያዎች ዓመታዊ ጉባኤ ተካሄደ።
9ኛው የኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ባለሞያዎች ዓመታዊ ጉባኤ ከሐምሌ 6 እስከ 7 ቀን በኃይሌ ግራንድ ሆቴል አዲስ አበባ ተካሄደ።
ለተከታታይ ሁለት ቀናት በተካሄደው በዚህ ጉባኤ የልብ ሕክምና አገልግሎትን በሀገሪቱ ለማስፋት የተሰሩ ልዩ ልዩ ሥራዎች ለማኅበሩ አባላት እና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች ገለጻ ተደርጓል። ከዚህም ባሻገር በመስኩ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሃገር ተቋማት ምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን ለተሳታፊዎች ለ ዕይታ አቅርበዋል። በልብ ሕክምና ዘርፍ የተሰሩ ልዩ ልዩ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከፈለኝ ደጀኔ የልብ ሕክምና ባለሞያተኞች ማኅበር ባለፉት ጊዜያት ማኅበሩ እና የልብ ሕክምና አገልግሎቶች እንዲጠናከሩ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፤ የልብ ሕክምና አገልግሎት ተደራሽነት እና ጥራት እየጨመረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ማኅበሩ የልብ ሕክምና አገልግሎት እንዲጠናከር ከልብ ሕሙማን ማኅብር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ባለሞያተኞች ማኅበር በመስኩ የተሰማሩ ከ300 በላይ አባላት በመላው ሀገራችን ክፍል ያሉት ሲሆን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የልብ ሕክምና አገልግሎት አስጣጥን ለማሻሻል በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል።