Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌አላቲኖስ የፊልም ውይይት ነገ ይካሄዳል

አላቲኖስ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪዎች ማሕበር ፒያሳ በሚገኘው የሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ ውስጥ በሚያዘጋጀው የፊልም ውይይት መርሐግብር ነገ ሐሙስ ነሐሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ" የፌርናንዶ ሶላኖስ አርጀንቲናዊ ሲኒማቶግራፊ"  በሚል ርዕስ እይታ እና ውይይት ያካሄዳል።በዕለቱም መነሻ ሀሳብ በምኒሊክ መርዕድ ይቀርባል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መቅረዝ ሥነኪን የኪነጥበብ ዝግጅት ነገ ይካሄዳል

አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ የክብር እንግዳ የሆነበት "መቅረዝ ሥነኪን" የኪነጥበብ ዝግጅት ሀሙስ ይካሄዳል።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችን እያጣመር የዘለቀው መቅረዝ ሥነኪን ወርሀዊ የኪነጥበብ  ዝግጅት ነገ ሐሙስ ነሐሴ 2 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ  ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር )አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የዓመቱ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ  አንጋፋው ደራሲ አበራ ለማ የክብር እንግዳ በመሆን የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች የግጥም ፣የሙዚቃ እና  የዳንስ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

የዚህ ዝግጅት መግቢያ በነፃ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ዓለምአቀፍ ፕሮፌሽናል የቦክስ ውድድር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌደሬሽን ዋና ቢሮውን በአዲስ አበባ የከፈተ ሲሆን ቅዳሜ ነሐሴ 11 2016 ዓ.ም በደማቅ ዝግጅት በይፋ ያስመርቃል፡፡

ከቢሮ ምርቃቱ በተጨማሪም በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ ቦክስ ውድድርም ይካሄዳል፡፡

ይህ ዓለምአቀፍ የቦክስ ውድድርን የዓለምአቀፉ የቦክስ ማህበር ከአፍሪካ የቦክስ ኮንፌደሬሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ የቦክስ ፌደሬሽን ጋር በመተበበር በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚዘጋጅ ሲሆን፣ 20 ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች ከራሺያ፣ ከሜክሲኮ፣ ከእንግሊዝ፣ ከካዛኪስታን፣ ከሞሮኮ፣ ከናይጄሪያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በአፍሪካ ታይቶ ለማይታወቅ ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት በ10 የቦክስ ውድድሮች ይፋለማሉ፡፡

ይህን ዓለምአቀፍ የቦክስ ውድድርን ለመዘገብ በርካታ ሚዲያዎች ከተለያዩ ሀገራት እንደሚመጡ ተገልጿል። መሰል ፕሮፌሸናል ውድድር ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለችም ተብሏል።

ስመጥርና ፕሮፌሽናል ቦክሰኞችን ውድድር ማንኛውም ስፖርት ወዳድ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት መታደም ይችላልም ተብሏል።

ቅድሚያ የመግቢያ ትኬት ለሚገዙና ለጥንዶች ልዩ ቅናሽ መኖሩ የተገለጸ ሲኾንን፣ ትኬቱንም ለመግዛት በ https://chapa.link/event/view/EV-6xynuuPvIkUK መጠቀም እንደሚቻል አዘጋጆቹ ለትርታ በላኩት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ገጣሚ ሠዓሊና ቀራፂ ከበደች ተክለአብ የሥነጥበብ ጉዞዋን ያካፈለችበት ዝግጅት ተካሄደ

አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን "ALONG WALK TO CREATIVITY  THE JOURNEY OF RESILIENT ARTIST "  በሚል ርዕስ  ሠዓሊ ቀራጺና ገጣሚ  ከበደች ተክለአብ  ያዘጋጁት ፕሮግራም ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም  በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ  ተካሄደ::

ሠዓሊ ቀራጺና ገጣሚ  ከበደች ተክለአብ ከረጅም ዓመታት የአሜሪካን ቆይታ በኃላ ወደ ሐገሯ በመምጣት በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት አዳራሽ  ተገኝታ ከረጅሙ የማስተማር  የስነጥበብ ጉዟዋ ሰዓት የፈቀደውን ሁሉ አካፍላለች::

በዚህ ፕሮግራም ላይ ከበደች ተክለአብ 
የሥነጥበብ ጉዞዋ ምን እንደሚመስል በፕሮጀክተር በተደገፉ ምስሎች ስለ ግጥም ስራዎቿ በአሜሪካና በተለያዩ ሐገሮች ስላካሄደቻቸው የስዕል አውደርዕዮቿ  በዝርዝር ነግራናለች:: በተለይ የስዕል ስራዎቿና ውጣ ውረድ የሞላበትን የስነጥበብ ጉዞዋን እውቀቷንና የልምዷን አካፍላለች:: ከታዳሚው  ለተነሳላት  በርካታ  ጥያቄዎችም መልስና ማብራሪያ ሰጥታለች::

ከበደች ተክለአብ "የት ነው?" የተሰኘው የግጥም መፅሐፏ በወቅቱ በሳንሱር ምክንያት እንዳይታተሙ የተደረጉትን ግጥሞች ጨምራና የመፅሐፉን መግቢያ አስተካክላ በድጋሚ እንደታተመ ተናግራለች::  አዲሱንም መፅሐፍ አሳይታናለች:: በተጨማሪም " ሱታፌ " የተሰኘው  አዲሱ መፅሐፏም ታትሞ ለንባብ እንደበቃ በዚሁ ፕሮግራም ላይ ተናግራለች::

በአሁኑ ወቅት በኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው ዘ ሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኒውዮርክ ኩዊንስቦሮ ውስጥ  አሲስታንት ፕሮፌሰር በመሆን ታስተምራለች::

📍መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጎዶን ጥበቃ" የተሰኘ አዲስ ተውኔት ዛሬ ሐሙስ ከምሽቱ 11:00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለእይታ ይበቃል።

ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት

ትርጉም:ሀይከል ሙባረክ

አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ

ተወዳጁ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል

ተወዳጁ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ሲከታተል የቆየውን ህክምና ጨርሶ በጥሩ ጤንነት በዛሬው ዕለት ወደ ቤቱ ገብቷል።

አርቲስት ልመንህ ታደሰ ላለፉት ጥቂት ወራት በአቢቹ መታሰቢያ የአእምሮ ክሊኒክ ሲደረግለት የነበረው ክትትልን ጨርሶ በሙሉ ጤንነት ወደ ቤቱ መግባቱን ድጋፍ እና ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ወዳጆቹ ገልፀዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ነገረ መጻሕፍት (ዛሬ ከሰዓት)

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ስብሐቲዝም (ነገ ከሰዓት )

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የአእምሮ እድገት ውስንነት ቀንን (CP-day) አስመልክቶ የፊታችን መስከረም 26 የእግር ጉዞ መርሐ-ግብር መዘጋጀቱ ተገለፀ

ስለ ሲፒ ጉዳት ይመለከተኛል በሚል በዛሬው እለት በእዝነት አካል ጉዳተኛ ህጻናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት ውስጥ የግንዛቤ ማስጨበጥ መርሐ-ግብር የተካሄደ ሲሆን  ይህን አስመልክቶ የፊታችን መስከረም 26 የእግር ጉዞ መርሐ-ግብርም መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ይህንንም የእግር ጉዞ ይፋ ለማድረግ እና የቲሸርት ምረቃ መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን 10000 የሚሆኑ ቲሸርቶች መዘጋጀታቸው ተገልጿል

ቲሸርቱ ከዛሬ ጀምሮ ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን የአንዱ ቲሸርት ዋጋ 400 ብር ነው ትብሏል
የCP ጉዳተኛ ህፃናት ራሳቸውን ችለው መቀመጥ፥ መቆም፥ መመገብ፥ ንፅህናቸውን መጠበቅ፥ መናገር አንዳንዱም ማየት የማይችሉ፥ እዲሁም በየቀኑ በተደጋጋሚ seizure የሚከሰትባቸው ህፃናት ናቸው።

እዝነት እነዚህ ህፃናት እንደማንኛውም ዜጋ ማግኘት ያለባቸውን እንከብካቤ እያገኙ ጤንነታቸው እና ምቾታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚጥር ማእከል እንደመሆኑ መጠን የCP ጉዳት ምንነትን አስመልክቶ የማሕበረሰቡ ግንዛቤ ከፍ እንዲል ለማድረግ የአይምሮ ውስንነት ቀንን (CP-day) ተንተርሶ ይህን የእግር ጉዞ መርሐ-ግብር ለማዘጋጀት መዘጋጀቱን የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘቢባ አህመድ ገልጸዋል።

ወ/ሮ ዘቢባ አክለው እንደገለጹት ህብረተሰቡ በሐገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም ሴሬብራል ፓልሲ ቀንን በማስመልከት በተዘጋጀው በዚህ የእግር ጉዞ መርሐግብር ላይ በመሳተፍ ለአካል ጉዳተኛ ህጻናት በተለይም ለሲፒ ጉዳተኛ ህጻናት አለኝታ በመሆን ከድርጅቱ ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮፕላስ የተሰኘ ስልክ ለተጠቃሚዎች ቀረበ

አምስተኛ ትውልድ(5ጂ) ኢንተርኔት ማስጠቀም ይችላል የተባለው አዲሱ የኢንፊኒክስ ምርት ለተጠቃሚዎች ነሐሴ 4 2016 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።

ኢንፊኒክስ ያስተዋወቀው አዲስ ስልክ “ኖት 40 ፕላስ” የሚባል ሲሆን፣ 5G ኔትዎርክን የሚያስጠቅም፤ 108 ሜጋ ፒክስል ጥራት ያለው ካሜራና 100 ዋት ፈጣን ቻርጀር፣ እንዲሁም 20 ዋት ያለገመድ ቻርጅ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ እንዳለው ተነግሯል።

በተጨማሪም፣ በጌመሮችና ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ስራዎችን  በስልካቸው በሚከውኑ ሰዎች ተመራጭ የሆነው ”ሜዲቴክ ዲመንሲቲ 7020” የተሰኘ ፕሮሰሰር የተገጠመለት “ፈጣን ስልክ ነው” ተብሏል።

እንደዚሁም 100 ዋት ፈጣን ቻርጀር እና 20 ዋት ያለገመድ ቻርጅ ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነውም ተብሏል።

የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ ስልክ የዘመኑ የመጨረሻ የኔትዎርክ ቴክኖሎጂ የሆነው 5G ማስጠቀም የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል።

በምርቱ ይፋ ማድርጊያ ዝግጅት የተለያዩ የመዝናኛ መርሃግብሮች ተካሂደዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ በተዘጋጁ ውድድሮችም አዲሱን የ”ኖት 40 ፕሮ ፕላስ” ስልክን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶች ለተሳታፊዎች እንደተበረከቱ ለማወቅ ተችሏል።

ኢንፊኒክስ ቲቪ፣ ላፕቶፕ፣ ኤርፖድ፣ ብሉቱዝ ስፒከር፣ ስማርት ዋች እና አዲሱ “ኖት 40” ስልኮች ለዝግጅቱ ታዳሚ ለዕይታ ቀረበዋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ዛሬ በኢትዮጵያ ቡክ ፎረም

ዛሬ ነሐሴ 5 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 እስከ 4:00 በኢትዮጵያ ቡክ ፎረም መቼቱን በ1990ዎቹ መጀመሪያ በተካሄደው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ላይ በማድረግ ከጦርነቱ የተመለሰ ታዳጊን ሕይወት በቤተሰቡ እንዲሁም አጠቃላይ ማህበራዊ ሕይወቱ በኩል ሀገራዊ ሁነትን በሚዳስሰው የይፍቱሥራ ምትኩ ሁለተኛ የልቦለድ ሥራ “ወድቆ የተገኘ ሐገር” ላይ የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም አሰናኞች እና ተሳታፊዎች ውይይት ያደርጋሉ። ።

የውይይቱ ሊንክ :
https://www.clubhouse.com/invite/aXOcqz2XL8Xa4gAjZloWJwwDBE4u2jvaKb:i17x1sSmUCL6GgF-BVAMSOBYYNniedPZSK-uPINmSsc

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ከበደች ትቀኛለች የግጥም ሠርክ"

በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ቅዳሜ ነሐሴ 11 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ “ከበደች ትቀኛለች” በሚል ርዕስ ገጣሚ፣ ቀራጺ እና ሠዓሊ ከበደች ተክለአብ ስራዎቿን የምታቀርብበት የግጥም ሠርክ ዝግጀት ይካሄዳል፡፡

ሁላችሁም በአክብሮት ተጋብዛችኋል!

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከቡሉምበርግ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ አፍሪካ ጋር በመተባበር የፋይናሻል ጋዜጠኝነት ስልጠና ሊሰጡ ነው፡፡

ስልጠናውን በተመለከተ የፕሮግራም ትውውቅ በዛሬው ዕለት የተካሔደ ሲሆን፤ ስልጠናው በዩኒቨርሲቲዎቹ የጋዜጠኝነት ተማሪዎች እንዲሁም በሥራ ላይ ላሉ ጋዜጠኞች የፋይናሻል ዘገባ ግንዛቤያቸውን የሚያሳድግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ የካፒታል ገበያ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርገው ስልጠናው፤ ፍላጎት ላላቸው ጋዜጠኞች ለተከታታይ ስድስት ወራት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ወንደወሰን ሙሉጌታ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው በተለይ ወቅቱ የሚጠይቀውን የፋይናንሻል ጋዜጠኝነት ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ለማፍራት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

የፋይናሻል ጋዜጠኝነት ቁጥራዊ መረጃን በትክክል መርምሮ ከመዘገብ ባለፈ የኢኮኖሚ መረጃን በግልጽ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

📍መረጃው ኢፕድ ነው

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1