Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
Event Addis Media
Photo
📌 “ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017" አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት የእንቁጣጣሽ ኤግዚቢሽንና ባዛር ቀጣይ ሳምንት ይከፈታል።

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን እና ሊየን ቢዝነስ ግሩፕ ከአሴነቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር  ያዘጋጁት የእንቁጣጣሽ ዋዜማ ኤግዚቢሽንና ባዛር በሚቀጥለው ሳምንት ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ይከፈታል።

"ሲቢኢ ብር ኤክስT 2017" በሚል ስያሜ የተሰየመው እና ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ሞ ለተከታታይ 21 ቀናት በሚቆየው ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ በዓይነቱ ልዩ የሆነና ደረጃውን የጠበቀ ብሎም ለሻጭ፣ ለጎብኚና ለሸማች ምቹ እንዲሆን ከስነ-ውበታዊ ጉዳዮች ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ሲዘጋጅ መቆየቱን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

በዚህ ኤክስፖ ላይ ከአስር በላይ መንደሮች የተዘጋጁ ሲሆን ከሸመታና ከጉብኝት በተጨማሪ በየቀኑ ከ35 በላይ ተወዳጅ ደሞጻዊያን የሚያቀነቅኑበት ልዩ የሙዚቃና የመዝናኛ ፌስቲቫልም ተዘጋጅቷል።

እስከ እንቁጣጣሽ ዋዜማ ድረስ በተከታታይ በሚከናወነው ፌስቲቫል ላይ የመድረክ የሙዚቃ ክዋኒያቸውን ከሚያቀርቡ ድምጻዊያን መካከል  አብርሃም ገብረ መድህን፣ መሰሉ ፈንታሁን ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ አንዱዓለም ጎሣ፣ ኃይለየሱስ ግርማ፣ ጌቴ አንለይ፣ ሃይማኖት ግርማ፣ ተአምር ግዛው ፣አምሳል ምትኬና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በኤክስፖ መክፈቻ እና መዝጊያ ላይ ከሚኖረው የሙዚቃ ዝግጅት በተጨማሪ ቅዳሜ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ድምጻዊ አብርሃም ገብረ መድህንን ጨምሮ እውቅ ድምጻዊያን በታዋቂ ባንድ በመታጀብ የሚያቀነቅነበትን ልዩ ኮንሰርትን ተዘጋጅቷል።

ከአራት መቶ በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ድርጀቶች የሚሳተፋበት “ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017" ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይጎበኘዋል ተበሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለጎቢኚዎች ወደ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሲቢኢ ብር በኩል በቆረጡት የ100 ብር ትኬት አማካኝነት የሚያገኙትን የዕጣ ቁጥር በመጠቀም እንደ እድላቸው ሀያ የ5 ሺህ ፣አምስት የ10ሺ፣ ሶስት የ50ሺ፣ ሁለት የ100 ሺ ብር ዋጋ ያላቸውን ኩፖኖችን በማሸነፍ ከእግዚቢሽኑ የፈለጉትን ዕቃ መሸመት የሚችሉበት የዕጣ ጨዋታ ተዘጋጅቷል።

ከኩፖኖቹ በተጨማሪ አንድ የኤሌክትሪክ ባይክ እና 2.3 ሚሊዮን ብር ዋጋ የሚያወጣ ቢዋይዲ አዲስ የቤት አውቶሞቢል መኪና ለባለዕድለኞች በሽልማትነት መቅረቡን ተገልጿል።

ለተጨማሪው:@EventAddis1
📌ሁለት አልበሞች በተመሳሳይ ቀን

የሚካኤል በላይነህ እና የቬሮኒካ አዳነ የሙዚቃ አልበሞች በተመሳሳይ ቀን ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል ።

የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ "አንድ ቃል"  እና የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ"መጠሪያዬ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጣቸው ሁለት የሙዚቃ አልበሞች በሚቀጥለው ሳምንት ነሐሴ 17 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቁ ኤቨንት አዲስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ፊልም ይመልከቱ !

እነዚህ ሶስት የፊልም ማሳያዎች(ሲኒማ ቤቶች) ዛሬን ጨምሮ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት እነዚህን ፊልሞች ለተመልካቾች ያቀርባሉ: ምስሎቹን ይመልከቱ።

የሲኒማ ቤቶቹ አድራሻ:

✔️ለም ሆቴል አካባቢ: ቫምዳስ ሲኒማ

✔️ጉርድ ሾላ አካባቢ : ሴንቸሪ ሲኒማ

✔️ቦሌ አካባቢ : ዓለም ሲኒማ

መልካም የእረፍት ቀናት ይሁንላችሁ !

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በታይም መጽሔት ‘የዓመቱ ታዳጊ ሳይንቲስት"

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ ተመራማሪ ሄማን በቀለ በታይም መጽሔት ‘የዓመቱ ታዳጊ ሳይንቲስት’ ተብሎ ተሰየመ

የቆዳ ካንሰርን ማከምና መከላከል የሚችል ሳሙና ለመስራት ምርምር በማድረግ ላይ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሄማን በቀለ በታይም መጽሔት የዓመቱ የላቀ ተጽዕኖ ፈጣሪ ታዳጊ ተብሎ ተሰየመ።

ሄማን ባለፈው ጥቅምት ወር ከምርምር ስራው ጋር በተያያዘ በተካሄደ የወጣት ሳይንቲስቶች ውድድር ላይ ተሳትፎ 25ሺ ዶላር መሸለሙን መዘገባችን ይታወሳል።

የ15 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ ሄማን በቀለ በአሜሪካ ቨርጂኒያ የሚኖር ሲሆን፣ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነው።

የአራት ዓመት ልጅ እያለ ከወላጆቹ ጋር ወደ አሜሪካ ያቀናው ሄማን ለስኬቱ በመምህርነት ሙያ ላይ የተሰማሩት እናቱና በዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩት አባቱ ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ለመጽሔቱ ተናግሯል።

ሄማን ከመጽሄቱ ጋር በነበረው ቆይታ ብዙ ሰዎች ሁሉም ነገር ተፈጥሮ እንዳለቀ አድርጎ የማሰብ አዝማሚያ እንደሚያሳዩ ገልጾ፣ እነዚህን ሰዎች ሲመክርም ‘ሀሳብ አያልቅም፤ በፈጠራ ላይ እንበርታ፤ ዓለማችንን የተሻለች ለማድረግ እንጣር’ ብሏል።

ሄማን ከሰባት ዓመቱ ጀምሮ በሚያካሂደው የምርምር ስራና ለጉዳዩ ባለው ከፍተኛ ፍላጎት በተማረኩት ተባባሪ ፕሮፌሰርና ሞለኪዩላር ባዮሎጂስት በሆኑት ቪቶ ሬቤካ ድጋፍና ክትትል ባልቲሞር በሚገኘው ጆን ሆፕኪንስ የማህበረሰብ ጤና  ላብራቶሪ ውስጥ የምርምር ስራውን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝም መጽሔቱ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ነገረ መጻሕፍት" የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል

በልዩ_ዝግጅት ለደብረታቦር ዕለት!

ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል!!

ነሐሴ 13/ 2016 ዓ.ም ሰኞ: ከ8:00 - 10:30

ቆይታ:- ከከበደች ተክለ አብ ጋር
ለውይይት የተመረጡት መጻሕፍት፡- “ሱታፌ” እና “የት ነው?”

አወያይ:-  እንዳለጌታ ከበደ።
አዘጋጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ።

አስተባባሪ ፦ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል

የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡https://maps.app.goo.gl/yb1LFT7PDTwLUP217

ለበለጠ መረጃ እና መገኘትዎን ለማረጋገጥ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
https://news.1rj.ru/str/+VZQIhKm-NoAwYjM0

እንዲሁም 0900651010 ወይም 0777664020 (ሳፋሪ) ይደውሉ፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ዓለምአቀፍ የቦክስ ውድድር ነገ በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ይካሄዳል

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ከዓለም አቀፉ የቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለምአቀፍ የቦክስ ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ቅዳሜ ነሐሴ 11 2016 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑ ቦክሰኞቹ ዛሬ ነሐሴ 10 2016 ዓ.ም የክብደት ምዘና እና ትውውቅ አከናዉነዋል።

ነገ በሚከናወነው ውድድር ከሩሲያ፣ ከኡስቤክስታን፣ከዛኪስታን፣ከሜክሲኮ፣ከሴኔጋል፣ ከሞሮኮ የተወጣጡ ከአስር በላይ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች እንደሚፋለሙ ተነግሯል።

ኢትዮጵያም ሁለት ቦክሰኞችን ታሳትፋለች። ኢትዮጵያን በመወከል አቡበከር ሰፋን በ60ኪግ ከሴኔጋል አቻው እንዲሁም ተመስገን ምትኩ በ75ኪግ ከሞሮኮ አቻው ይፋለማሉ።

ዉድድሩ በሰባት የተለያዩ የክብደት እርከኖች ሲካሄድ ጋናዊዉ ቲዮፒለስ አሉተይ እና ዛምቢያዊዉ ፓትሪክ ችኔምባ የአይቢኤ ቀበቶን ለመዉሰድ የቡጢ ፍልሚያቸዉን ያከናዉናሉ።

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ፅሕፈት ቤት በነገ ዕለት የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ይመረቃል ተብሏል።

የአፍሪካ ቦክስ ኮፌዴሬሽን ዋና መስርያ ቤት በኢትዮጵያ መከፈትን ምክንያት በማድረግ እንደሚካሄድም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሥራዎቹን እንዲያቀርብ ዕድል ተሰጠው

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በጤና እክል ምክንያት ከኪነጥበቡ ርቆ የቆየው ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ወደ ጣቢያው ተመልሶ ሥራዎቹን እንዲያቀርብ ዕድል መስጠቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋገጡ።

ይህ የተገለጸው የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ባደረጉለት ጥሪ ሸጎሌ ወደሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት ለመጣው ኮሜዲያን ልመንህ አቀባበል በተደረገለት ወቅት ነው።

የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ ልመንህ ካጋጠመው የጤና እክል በመውጣቱ መደሰታቸውን ገልጸው፤ እርሱ ወደ ጤናው እንዲመለስ ያደረጉ ወገኖችም ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው እና የጥበብ፣ የዕውቀት እና የመረጃ ቤት የሆነው ኢቢሲ እንደ ልመንህ ላሉት የሀገር ባለውለታዎች ትልቅ ቦታ እንዳለው አቶ ጌትነት ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፉ የነበሩት የልመንህ ሥራዎች የሁላችንም የልጅነት ትዝታዎች መሆናቸውን ያወሱት አቶ ጌትነት፤ ወደ ቤቱ ተመልሶ በመምጣቱ ደስተኞች ነኝ ብለዋል።

ኢቢሲ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ከነፍሱ ጥሪ ጋር መገናኘት እንዳለበት ያምናል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ለዚህም ዝግጅቶቹን በኢትዮጵያ ቴሌቪዢን እንዲያቀርብ ዕድል እንደሚሰጠው ተናግረዋል።

ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ፥ በተደረገለት አቀባበል ደስተኛ መሆኑን ገልጾ፣ አሁን ከምናገረው በላይ በቀጣይ የሚቻለኝን ሠርቼ የሚጠበቅብኝን አበረክታለሁ ብሏል።

የልመንህ ባልደረቦች በበኩላቸው፥ ኢቢሲ የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ባለውለታ መሆኑን አውስተው፤ ለኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ስለተሰጠው ዕድልም አመስግነዋል።

📍መረጃው የኢቢሲ ነው ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የ12ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የመጨረሻ እጩዎች

የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት “በጎ ሰዎችን በመሸለምና እውቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፍራ” በሚል መርህ ላለፉት 11 ዓመታት ለሀገር እና ለህዝብ አርአያነት ያለው ተግባር ለፈጸሙ አትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዕውቅና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ለ12ኛ ጊዜ በዚህ ዓመትም ጳጉሜ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከ 8 ሰዓት ጀምሮ መርሃግብሩን ያከናውናል፡፡

በዘንድሮው የእጩዎች ጥቆማ ሂደት 516 ጠቋሚዎች 109 የሚሆኑ እጩዎችን ጠቁመዋል፡፡ የበጎ ሰው በጎ አድራጎት ቦርድ እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ ጥቆማዎቹን በየተጠቆሙበት ዘርፍ ካደራጀ እና ያልተሟሉ የእጩዎች ግለ-ታሪክ እና አበርክቶ ካሰባሰበ በኋላ በየዘርፉ የመጨረሻዎቹን 3 እጩዎች መርጧል፡፡ በመቀጠልም ቦርዱ የእጩዎችን ግለ-ታሪክ እና አበርክቶ በየዘርፉ ለተመረጡ ዳኞች ከመምረጫ መስፈርቶች ጋር ይሰጣል፡፡ የዳኞችን ውሳኔም ያለምንም ማሻሻያ በመቀበል በጳጉሜ 3 /2016 ዓም በሚካሄደው መርሃ ግብር ለህዝብ እንዲገለጽ ያደርጋል፡፡

በዚሁ መሠረት የ12ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በየዘርፉ የመጨረሻ እጩዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

የ12ኛው የበጎ ሰው ሽልማት እጩዎች

1.መምህርነት

መምህር ብርሃኑ በላይ፡ ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ትምህርት በማመቻቸት ይታወቃሉ።

መምህር ማሞ መንገሻ ፡ በመምህርነት ያገለገሉ፤ በትምህርት ሴክተሩ ላይ የፖሊሲ ግብዓት ጥናቶችን ያበረከቱ 

አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ፡በአርክቴክቸር መምህርነታቸው እና በዚሁ ሙያ ላይ ህዝብን በማንቃት ይታወቃሉ

2.መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት

ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ፡ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚ/ር ዲኤታ ሆነው ያገለገሉ

ኮ/ል ስምረት መድኀኔ ፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ያገለገሉ።

ዶ/ር 0ቢይ ታደሰ፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከአንገት በላይ ቀዶ ጥገና ህክምና በርካታ ህጻናትን በመርዳት ይታወቃሉ።

3.ሚዲያ እና ጋዜጠኝነት

ጋዜጠኛ ሄኖክ ሥዩም ፡ በተጓዡ ጋዜጠኛ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎችን እና ቅርሶችን ያስተዋወቁ፤ መጻሕፍትም ያሳተሙ 

ጋዜጠኛ የምወድሽ በቀለ ፡ ከ40 ዓመታት በላይ በጋዜጠኝነት እና በደራሲነት እያገለገሉ የሚገኙ

ጋዜጠኛ ብርሃኑ ገ/ማርያም ፡  በኢትዮጵያ ሬዲዮ አገልግሎት ለረጅም ዓመታት በማገልገል ይታወቃሉ

4.ኪነ ጥበብ (የኪነጥበብ ማሰልጠኛ ተቋማት )

አቢሲኒያ ሥነጥበብ ትምህርት ቤት ፡ በግሉ ዘርፍ ለረጅም ዓመታት በርካታ ሙያተኞችን ያፈራና ለውጤት ያበቃ የሥነጥበብ ማሰልጠኛ ተቋም

ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዘመናዊ የሙዚቃ ትምህርት  ቤት

አለ የሥነጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ፡በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሥዕል ትምህርት ቤት

5.ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ

ዶ/ር ባዩሽ ፀጋዬ ፡ በሰብል ዘረ መል ሀብት ጥበቃ ፤ በኦርጋኒክ ግብርና እና በአርሶአደሮች መብት ላይ ጥናትና ምርምር ያከናወኑ፤ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ለሚገኙ አርሶ አደሮች እውቀታቸውን በማካፈል የሚታወቁ ተመራማሪ ናቸው፡፡  

ዶ/ር በዳዳ ግርማ ፡ በሰብል ሳይንስ ምርምር በተለይም በስንዴ ዘር መሻሻል እና  መቋቋም ላይ ምርምር ያካሄዱ፤ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭም ከፍተኛ ሽልማቶችን ያገኙ ተመራማሪ ናቸው፡፡

ፕ/ር የማነብርሃን ገ/እግዚአብሔር፡ በኢፒዲዮሞሎጂ እና በህብረተሰብ ጤና ሳይንስ ዘርፍ ተጠቃሽ ተመራማሪ ሲሆኑ  የአዲስ ኮንቲኔንታል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት መስራች ናቸው፡፡ 

6.በጎ አድራጎት

አቤኔዘር ሳፖርቲንግ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ፡ በተለይ በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በርካታ ወላጅ ያጡ ፤ ትኩረት የሚሹ ህጻናትን በማገዝ፤ በማስተማር እና በማቋቋም ይታወቃል ።

ዶ/ር ፈቀደ አጉዋር ፡ የልብ ቀዶ ጥገና ሐኪም ሲሆኑ ከመደበኛ አገልግሎታቸው ባሻገር ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም አቋቁመው በበጎ ፈቃድ የልብ ህሙማንን ይረዳሉ።

ማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የካንሰር ህሙማን መርጃ ማኅበር ሲሆን ለበርካታ ህጻናት እና አዋቂ ታማሚዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል 

7.ቅርስ ባህል እና ቱሪዝም

ዞማ ፡ ሀገራዊ ጥበብን ከዘመናዊ የሥነ ጥበብ ክህሎት ጋር በማቀናጀት መዝናኛን፤ መናፈሻን ፤ የእንስሳት እርባታን እና የህጻናት ትምህርትን በማቀናጀት ሀገራዊ ክህሎቶች እውቅና እንዲያገኙ የሚሠራ ተቋም ነው

ጌትነት ይግዛው፡ በጎንደር ቤተመንግሥት እና በባህል ሚ/ር በተለያዩ ዘርፎች ያገለገሉ ፤ ቅርሶች የተሟላ መረጃ እንዲኖራቸው የሠሩ፤ የቱሪስት መዳረሻዎችን እና ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ አብርክቶ ያላቸው ባለሙያ ናቸው።

ዮድ አቢሲኒያ፡ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦችን ፤ ውዝዋዜዎችን እና ባህላዊ እሴቶችን ለቱሪስቶች እና ማህበረሰቡ  የሚያቀርብ ተቋም ነው ።

8.በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን

ሰዓሊ እና ገጣሚ ከበደች ተክለአብ ፡ ሰዓሊ ፤ ገጣሚ እና በአሜሪካ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ ።

ፕ/ር አየለ በከሪ ፡ ፓን አፍሪካኒዝምን በተመለከተ ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣ ጥረት የሚያደርጉ የታሪክ ምሁር ናቸው

ፕ/ር አቻምየለህ ደበላ፡ በታዋቂ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል አርት እና ግራፊክስ መምህር ፤ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር በበጎ አድራጎት ሥራ ላይ አበርክቶ ያላቸው ምሁር ናቸው ።

9.ንግድ ፤ ኢንዱስትሪ እና ሥራ ፈጠራ

ዋሪት  ሙሉጥላ  ኢንተርናሽናል ዝ! ፡ ከቤተሰብ የንግድ ተቋምነት ባለፈ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች በመሰማራት ለረጅም ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የንግድ ተቋም ነው።

በላይ አብ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፡ በሰፋፊ የንግድ ሥራዎች ላይ የተሰማራ ተቋም ሲሆን ለበርካታ ኢትዮጵያውያንም የሥራ ዕድል የከፈተ ተቋም ነው

ፍቃዱ ፀጋዬ፡ በስደተኛ ካምፕ ውስጥ ራስን ከማስተማር ጀምረው ንግዳቸውን በማስፋፋት ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ሰፊ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ናቸው

10.ማኅበራዊ ዘርፍ

በቀለች ቶላ፡ ባህላዊ የበሽታ መከላከያ ህክምናን ፤ የእጽዋት አጠቃቀም እና የእጽዋት መጠሪያዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች በማዘጋጀት ማኅበራዊ እሴትነታቸውን አጉልተው የሚያሳዩ መጻሕፍትን አሳትመዋል  ።

ረ/ፕ ደረጄ ገብሬ ፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ፤ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር በአመራርነት ያገለገሉ ፤ በማህበረሰቡ በተለይም በህጻናት ውስጥ የንባብ ባህል እንዲዳብር ያገዙ ናቸው።

ለተጨማሪው:@EventAddis1
📌"ሜሎሪና- ሕይወቴ" የተሠኘው ሶስተኛ መጽሐፍ ቅዳሜና እሑድ በራስ አምባ ሆቴል ይመረቃል።

ቀን: ነሐሴ 11 ( ከጠዋት 2 - ምሽቱ 2 ሰዓት ) እና ነሐሴ 12 (ከጠዋቱ 4- ምሽቱ 2 ሰዓት) ባመቻችሁ ሰዓት በመገኘት መጽሐፉን ከደራሲው በአካል ማግኘት ትችላላችሁ።

ቦታ: ራስ አምባ ሆቴል ( ከ4 ኪሎ ወደመገናኛ በሚወስደው መንገድ ላይ፣ የመጨረሻ ፎቅ ላይ) https://maps.app.goo.gl/V6u4r8vMw2m5cxPH8?g_st=ac

መጽሐፉን በብዛት ለምትፈልጉ 0912664084 መደወል ትችላላችሁ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ነብያት እና ፈላስፎች" የተሰኘ ውይይት

42ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ደራሲ መሐመድ አሊ ቡርሃን "ነቢያት እና ፈላስፎች" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።

ይህም ውይይት እሁድ ነሐሴ 12 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ለጋብቻችሁ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል።

"ለጋብቻችሁ" በሚል ርዕስ በአንጋፋው የትዳር አማካሪ ይመስገን ሞላ የተዘጋጀው መጽሐፍ ዛሬ ነሐሴ 11 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ላምበረት አካባቢ በሚገኘው ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ውስጥ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"90 ደቂቃ" በሬድዮ ፖድካስት መሰራጨት ጀመረ

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ ለበርካታ ዓመታት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ ሲተላለፍ የቆየው "90 ደቂቃ" የሬድዮ የመረጃ ሠዓት ፕሮግራም በቅርቡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ላይ "የቅዳሜ ልዩ 90 ደቂቃ" መሰናዶውን መጀመሩ ይታወሳል።

ጣቢያው ከቅዳሜ ነሐሴ 4 2016 ዓ.ም ጀምሮ "የቅዳሜ ልዩ 90 ደቂቃ" በፖድካስት አማራጭ ማሰራጫት እንደጀመረ ኤቨንት አዲሰ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህው የሬድዮ ፕሮግራም ወደ ፖድካስት የስርጭት አማራጭ መምጣቱ "ለሬዲዮ ዘርፍ አዲስ ቀለም ነው" ተብሏል።

"የቅዳሜ ልዩ 90 ደቂቃ በፖድካስት" ፕሮግራሙን ለሁለት ሳምንታት በመምራት ጋዜጠኛ ኃይለሱስ መኮንን የታሪኩ ተጋሪ ሆኗል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ዶቃ" የአማርኛ ፊልም በቴሌ ቲቪ የፊልም መተግበሪያ ላይ በይፋ መታየት ጀመረ።

የኢግልይን መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ በሱፍቃድ ጌታቸው ከፈልም ተዋናይት እና ፕሮዲውሰር ማህደር አሰፋ ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት "ዶቃ የተሰኘውን ፊልም በቴሌ ቲቪ ለማስተላለፍ ከስምምነት ደርሰናል ብለዋል።

ይህ "ዶቃ "የተሰኘው አማርኛ ፊልም  የፓን አፍሪካን የፊልም ፌስቲቫል (Best Feature Film) ዘርፍ እና የለዛ ሽልማት የአመቱ ምርጥ ፊልም በመሆን አሸናፊ መሆን የቻለ ነው ተብሏል::

ተዋናይት እና ፕሮዲውሰር ማህደር አሰፋ ፊልሙን ለማዘጋጀት ሦስት አመት እንደወሰደባት እና ጥሩ ነገር ለተመልካች አቅርበናል ብላ እንደምታምን ገልጻለች።

በፊልሙ የሃገራችን የፊልም ባለሙያዎች እንደ ቅድስት ይልማ፣ቤዛ ሃይሉ ፣ ማህደር አሰፋ እና ሌሎችም የፊልም ባለሙያዎች እንደ ተሳተፉበት ታውቋል።

አቶ በሱፍቃድ ተመልካቾች ፊልሙን በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ነሃሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ  መመልከት ይቻላል ያሉ ሲሆን፣ ለመመልከት መመዝገብ እና ከፍያ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል።

አቶ በሱፍቃድ ክፍያው ሁሉን ያገናዘበ መሆኑን ገልጸው ለሀገር ውስጥ 100 ብር፣ለውጭ ደግሞ 5 ዶላር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቴሌ ቲቪ ከፍያን ለመፈፀም ለሃገር ውስጥ ቴሌብርን ፣ ከሃገር ውጭ ለሚኖሩ ተመልካቾች ደግሞ ቪዛ፣ ማስተርካርድ እና አሜሪካን ኤከስፕረስን በመጠቀም መፈጸም እንደሚችሉ ተነግሯል።

📍 መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ነገረ መጻሕፍት" ዛሬ ይካሄዳል!

በልዩ_ዝግጅት ለደብረታቦር ዕለት!

ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል!!

ነሐሴ 13/ 2016 ዓ.ም ሰኞ: ከ8:00 - 10:30

ቆይታ:- ከከበደች ተክለ አብ ጋር
ለውይይት የተመረጡት መጻሕፍት፡- “ሱታፌ” እና “የት ነው?”

አወያይ:-  እንዳለጌታ ከበደ።
አዘጋጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ።

አስተባባሪ ፦ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል

የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡https://maps.app.goo.gl/yb1LFT7PDTwLUP217

ለበለጠ መረጃ እና መገኘትዎን ለማረጋገጥ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
https://news.1rj.ru/str/+VZQIhKm-NoAwYjM0

እንዲሁም 0900651010 ወይም 0777664020 (ሳፋሪ) ይደውሉ፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌''ደብረ ታቦርን በደብረ ታቦር" ልዩ ዝግጅት ተካሄደ

የበርካታ ባሕል እና እሴት መገኛ የኾነችው ደብረ ታቦር ከተማ በየዓመቱ በክረምት ወራት በድምቀት ከሚከበሩ ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል ደብረ ታቦርን በደብረ ታቦር፣ ቡሔ፣ አሸንድዬ እና አድርሽኝ ተጠቃሾች ናቸው።

በደብረ ታቦር ከተማ በዋዜማው ሁለት ሁነቶች በድምቀት ተካሂደዋል። ደብረ ታቦርን በደብረ ታቦር በተመለከተ የቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች፣ ኪነ ጥበባዊ ክንዋኔዎች እና በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ድርሻ ያላቸው የአጼ ምኒልክ እና የባለቤታቸው ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ የእቴጌ ጣይቱ የመታሰቢያ የልደት በዓላቸው በሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ተከብሮ ውሏል።

የጉና የባሕል ቡድን በመድረኩ የተለያዩ ባሕላዊ ሁነቶችን አቅርቧል። የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በዓሉን በተመለከተ ታሪካዊ ዳራውን በመዳሰስ ጥናት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

📍 መረጃው የአሚኮ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የቬሮኒካ አልበም የሚለቀቅበት ቀን ተራዘመ!

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" አልበም በዚህ ሳምንት አርብ ነሐሴ 17 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ በተለያየ መንገድ ሲተዋወቅ የቆየው ቢሆንም የሚለቀቅበት ቀን እንደተራዘመ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ሰምቷል።

የተራዘመበት ምክንያትም" የሰባት ዓመት እድሜ ያላት ህጻን ሔቨን የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ከተፈጸመባት በኋላ ህይወቷ እንዳለፈ ከሰሞኑ ሰምተናል በዚህም በጣም አዝነናል፣ በዚህ ሀዘን ውስጥ እያለን የሙዚቃ አልበሜን መልቀቅ አልፈልግም" ብላለች።

"መጠሪያዬ" አልበም 12 የሙዚቃ ስራዎችን የያዘ ሲሆን አልበሙን ስርቶ ለማጠናቀቅ 3 ዓመት መውሰዱ ተነግሯል።

በአልበሙ ላይ በግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ፣አቡዲ 7 እና ሱራፌል የሺጥላ የተሳተፉ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር ታምሩ አማረ ፤አዲስ ፍቃዱ አብርሃም ከዳኔ'ሮቤል እንዳለ በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ስለሞን ኃ/ማሪያም ተሳትፈውበታል።

አልበሙ ላይ ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ያሉት ሲሆን ክሊፑ በአሜሪካ አትላንታ መሠራቱን ገልጸዋል።

ይህ አልበም አጠቃላይ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ሲሆን የአልበሙ ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲዩስ ተደርጓል።

ይህ አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ ጋር በ160,000 ዶላር በመላው አለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር ተስማምተዋል፡፡

"መጠሪያዬ" የተሰኘው አልበም በሚቀጥለው  ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በራሷ በቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል እና ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መልቲቾይስ አፍሪካ ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የስኮላርሺፕ ዕድል አዘጋጀ

የአፍሪካ የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶች አቅራቢው መልቲቾይስ አፍሪካ/ዲኤስቲቪ በየዓመቱ ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የ1 ዓመት የፊልም ጥበብ ስኮላርሺፕ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡ የስኮላርሺፕ ቆይታቸውን በከፍተኛ ውጤት ለሚያጠናቅቁ ተመራቂዎች ደግሞ በኒውዮርክ፣ በሕንድ እና በደቡብ አፍሪካ የፊልም አካዳሚዎችና የፊልም ኢንዱስትሪ መንደሮች ተጨማሪ ስልጠና የሚያገኙ ይሆናል፡፡

በዚህ ታላቅ የመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ የ2024 እኤአ ተመዝጋቢ በመሆን ለ2025ቱ ስኮላርሺፕ ዕድል በማግኘት ኬንያ በሚገኘው የመልቲቾይስ አካዳሚ የፊልም ጥበብ ዕውቀታችሁን ማጎልበት ለሚፈልጉ ዕድሜያቸው ከ18-26 ዓመት የሆኑ ወጣት የፊልም ባለሙያዎች እስከ መስከረም 5 ቀን, 2017 ዓ.ም (September 15, 2024) ድረስ በ https://applications.multichoicetalentfactory.com ላይ እንዲያመለክቱ ጋብዟል፡፡

መልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ ለአንድ ዓመት ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የሚሰጥ ነጻ የስልጠና ዕድል (ስኮላርሺፕ) ሲሆን፤ በስልጠና እና የተግባር ትምህርት ከአንደኛ እስከ ሦሥተኛ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ምሩቃን ወደ ኒውዮርክ፣ ቦሊውድ እና ደቡብ አፍሪካ ለላቀ ከፍተኛ ትምህርት የሚጓዙበትን ሽልማት እንደሚያገኙም ተነግሯል።

አመልካቾች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታና ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት ሊኖራችው እንደሚገባም ተጠቁሟል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሚዲያ አዋርድ የሚደረግበት ቀን ይፋ ሆነ

ላለፉት ሁለት ወራት በዳኞች እና በህዝብ በሶስት ዙር ድምፅ ሲሰጥበት የቆየው "የሚዲያ አዋርድ"የሽልማት ሥነሥርዓት ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከ11 ሰዓት ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ የሽልማት ሥነሥርዓ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣አንጋፋ እና ወጣት ጋዜጠኞች፣አርቲስቶችን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ እና ተፅህኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንደሚገኙ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1