Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.75K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"ለጋብቻችሁ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል።

"ለጋብቻችሁ" በሚል ርዕስ በአንጋፋው የትዳር አማካሪ ይመስገን ሞላ የተዘጋጀው መጽሐፍ ዛሬ ነሐሴ 11 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ላምበረት አካባቢ በሚገኘው ኃይሌ ግራንድ ሆቴል ውስጥ እንደሚመረቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"90 ደቂቃ" በሬድዮ ፖድካስት መሰራጨት ጀመረ

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ ለበርካታ ዓመታት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ ሲተላለፍ የቆየው "90 ደቂቃ" የሬድዮ የመረጃ ሠዓት ፕሮግራም በቅርቡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ላይ "የቅዳሜ ልዩ 90 ደቂቃ" መሰናዶውን መጀመሩ ይታወሳል።

ጣቢያው ከቅዳሜ ነሐሴ 4 2016 ዓ.ም ጀምሮ "የቅዳሜ ልዩ 90 ደቂቃ" በፖድካስት አማራጭ ማሰራጫት እንደጀመረ ኤቨንት አዲሰ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህው የሬድዮ ፕሮግራም ወደ ፖድካስት የስርጭት አማራጭ መምጣቱ "ለሬዲዮ ዘርፍ አዲስ ቀለም ነው" ተብሏል።

"የቅዳሜ ልዩ 90 ደቂቃ በፖድካስት" ፕሮግራሙን ለሁለት ሳምንታት በመምራት ጋዜጠኛ ኃይለሱስ መኮንን የታሪኩ ተጋሪ ሆኗል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ዶቃ" የአማርኛ ፊልም በቴሌ ቲቪ የፊልም መተግበሪያ ላይ በይፋ መታየት ጀመረ።

የኢግልይን መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ በሱፍቃድ ጌታቸው ከፈልም ተዋናይት እና ፕሮዲውሰር ማህደር አሰፋ ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት "ዶቃ የተሰኘውን ፊልም በቴሌ ቲቪ ለማስተላለፍ ከስምምነት ደርሰናል ብለዋል።

ይህ "ዶቃ "የተሰኘው አማርኛ ፊልም  የፓን አፍሪካን የፊልም ፌስቲቫል (Best Feature Film) ዘርፍ እና የለዛ ሽልማት የአመቱ ምርጥ ፊልም በመሆን አሸናፊ መሆን የቻለ ነው ተብሏል::

ተዋናይት እና ፕሮዲውሰር ማህደር አሰፋ ፊልሙን ለማዘጋጀት ሦስት አመት እንደወሰደባት እና ጥሩ ነገር ለተመልካች አቅርበናል ብላ እንደምታምን ገልጻለች።

በፊልሙ የሃገራችን የፊልም ባለሙያዎች እንደ ቅድስት ይልማ፣ቤዛ ሃይሉ ፣ ማህደር አሰፋ እና ሌሎችም የፊልም ባለሙያዎች እንደ ተሳተፉበት ታውቋል።

አቶ በሱፍቃድ ተመልካቾች ፊልሙን በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ነሃሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ  መመልከት ይቻላል ያሉ ሲሆን፣ ለመመልከት መመዝገብ እና ከፍያ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል።

አቶ በሱፍቃድ ክፍያው ሁሉን ያገናዘበ መሆኑን ገልጸው ለሀገር ውስጥ 100 ብር፣ለውጭ ደግሞ 5 ዶላር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቴሌ ቲቪ ከፍያን ለመፈፀም ለሃገር ውስጥ ቴሌብርን ፣ ከሃገር ውጭ ለሚኖሩ ተመልካቾች ደግሞ ቪዛ፣ ማስተርካርድ እና አሜሪካን ኤከስፕረስን በመጠቀም መፈጸም እንደሚችሉ ተነግሯል።

📍 መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ነገረ መጻሕፍት" ዛሬ ይካሄዳል!

በልዩ_ዝግጅት ለደብረታቦር ዕለት!

ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል!!

ነሐሴ 13/ 2016 ዓ.ም ሰኞ: ከ8:00 - 10:30

ቆይታ:- ከከበደች ተክለ አብ ጋር
ለውይይት የተመረጡት መጻሕፍት፡- “ሱታፌ” እና “የት ነው?”

አወያይ:-  እንዳለጌታ ከበደ።
አዘጋጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ።

አስተባባሪ ፦ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል

የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡https://maps.app.goo.gl/yb1LFT7PDTwLUP217

ለበለጠ መረጃ እና መገኘትዎን ለማረጋገጥ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
https://news.1rj.ru/str/+VZQIhKm-NoAwYjM0

እንዲሁም 0900651010 ወይም 0777664020 (ሳፋሪ) ይደውሉ፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌''ደብረ ታቦርን በደብረ ታቦር" ልዩ ዝግጅት ተካሄደ

የበርካታ ባሕል እና እሴት መገኛ የኾነችው ደብረ ታቦር ከተማ በየዓመቱ በክረምት ወራት በድምቀት ከሚከበሩ ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል ደብረ ታቦርን በደብረ ታቦር፣ ቡሔ፣ አሸንድዬ እና አድርሽኝ ተጠቃሾች ናቸው።

በደብረ ታቦር ከተማ በዋዜማው ሁለት ሁነቶች በድምቀት ተካሂደዋል። ደብረ ታቦርን በደብረ ታቦር በተመለከተ የቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች፣ ኪነ ጥበባዊ ክንዋኔዎች እና በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ድርሻ ያላቸው የአጼ ምኒልክ እና የባለቤታቸው ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ የእቴጌ ጣይቱ የመታሰቢያ የልደት በዓላቸው በሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ተከብሮ ውሏል።

የጉና የባሕል ቡድን በመድረኩ የተለያዩ ባሕላዊ ሁነቶችን አቅርቧል። የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በዓሉን በተመለከተ ታሪካዊ ዳራውን በመዳሰስ ጥናት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

📍 መረጃው የአሚኮ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የቬሮኒካ አልበም የሚለቀቅበት ቀን ተራዘመ!

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" አልበም በዚህ ሳምንት አርብ ነሐሴ 17 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ በተለያየ መንገድ ሲተዋወቅ የቆየው ቢሆንም የሚለቀቅበት ቀን እንደተራዘመ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ሰምቷል።

የተራዘመበት ምክንያትም" የሰባት ዓመት እድሜ ያላት ህጻን ሔቨን የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ከተፈጸመባት በኋላ ህይወቷ እንዳለፈ ከሰሞኑ ሰምተናል በዚህም በጣም አዝነናል፣ በዚህ ሀዘን ውስጥ እያለን የሙዚቃ አልበሜን መልቀቅ አልፈልግም" ብላለች።

"መጠሪያዬ" አልበም 12 የሙዚቃ ስራዎችን የያዘ ሲሆን አልበሙን ስርቶ ለማጠናቀቅ 3 ዓመት መውሰዱ ተነግሯል።

በአልበሙ ላይ በግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ፣አቡዲ 7 እና ሱራፌል የሺጥላ የተሳተፉ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር ታምሩ አማረ ፤አዲስ ፍቃዱ አብርሃም ከዳኔ'ሮቤል እንዳለ በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ስለሞን ኃ/ማሪያም ተሳትፈውበታል።

አልበሙ ላይ ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች ያሉት ሲሆን ክሊፑ በአሜሪካ አትላንታ መሠራቱን ገልጸዋል።

ይህ አልበም አጠቃላይ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ሲሆን የአልበሙ ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲዩስ ተደርጓል።

ይህ አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ ጋር በ160,000 ዶላር በመላው አለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር ተስማምተዋል፡፡

"መጠሪያዬ" የተሰኘው አልበም በሚቀጥለው  ነሐሴ 23 2016 ዓ.ም በራሷ በቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል እና ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል፡፡

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መልቲቾይስ አፍሪካ ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የስኮላርሺፕ ዕድል አዘጋጀ

የአፍሪካ የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶች አቅራቢው መልቲቾይስ አፍሪካ/ዲኤስቲቪ በየዓመቱ ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የ1 ዓመት የፊልም ጥበብ ስኮላርሺፕ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡ የስኮላርሺፕ ቆይታቸውን በከፍተኛ ውጤት ለሚያጠናቅቁ ተመራቂዎች ደግሞ በኒውዮርክ፣ በሕንድ እና በደቡብ አፍሪካ የፊልም አካዳሚዎችና የፊልም ኢንዱስትሪ መንደሮች ተጨማሪ ስልጠና የሚያገኙ ይሆናል፡፡

በዚህ ታላቅ የመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ የ2024 እኤአ ተመዝጋቢ በመሆን ለ2025ቱ ስኮላርሺፕ ዕድል በማግኘት ኬንያ በሚገኘው የመልቲቾይስ አካዳሚ የፊልም ጥበብ ዕውቀታችሁን ማጎልበት ለሚፈልጉ ዕድሜያቸው ከ18-26 ዓመት የሆኑ ወጣት የፊልም ባለሙያዎች እስከ መስከረም 5 ቀን, 2017 ዓ.ም (September 15, 2024) ድረስ በ https://applications.multichoicetalentfactory.com ላይ እንዲያመለክቱ ጋብዟል፡፡

መልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ ለአንድ ዓመት ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የሚሰጥ ነጻ የስልጠና ዕድል (ስኮላርሺፕ) ሲሆን፤ በስልጠና እና የተግባር ትምህርት ከአንደኛ እስከ ሦሥተኛ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ምሩቃን ወደ ኒውዮርክ፣ ቦሊውድ እና ደቡብ አፍሪካ ለላቀ ከፍተኛ ትምህርት የሚጓዙበትን ሽልማት እንደሚያገኙም ተነግሯል።

አመልካቾች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታና ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት ሊኖራችው እንደሚገባም ተጠቁሟል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሚዲያ አዋርድ የሚደረግበት ቀን ይፋ ሆነ

ላለፉት ሁለት ወራት በዳኞች እና በህዝብ በሶስት ዙር ድምፅ ሲሰጥበት የቆየው "የሚዲያ አዋርድ"የሽልማት ሥነሥርዓት ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከ11 ሰዓት ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።

በዚህ የሽልማት ሥነሥርዓ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣አንጋፋ እና ወጣት ጋዜጠኞች፣አርቲስቶችን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ እና ተፅህኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንደሚገኙ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አርቲስት ነብዩ እንድሪስ የክብር እንግዳ የሆነበት "ክሬቲቭ ኮኔክት" የተሰኘ ፕሮግራም አርብ ይካሄዳል

አርቲስት ነብዩ እንድሪያስ የክብር እንግዳ የሆነበት "ክሬቲቭ ኮኔክት" የተሰኘ ዝግጅት የፊታችን አርብ ነሐሴ17 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ጎተ ኢንስቲትዩት ውስጥ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አርቲስት ነብዩ እንድሪስ በቅርቡ ለእይታ የበቁቱን 6:00 ከሌሊቱ፣ ጃናሞራ ፊልሞችን ጨምሮ በሌሎችም በበርካታ ፊልሞች ተሳትፏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ጳጉሜን የኢትዮጵያውን መዝናኛና ባህል ማዕከል የዘንድሮ አሸናፊዎቹን ይፋ አደረገ

መቀመጫውን በአሜሪካ ሀገር ያደረገው ጳጉሜን የኢትዮጵያውን መዝናኛና ባህል ማዕከል የዘንድሮ አሸናፊዎቹን ዝርዝር  ይፋ አድርጓል።

ማዕከሉ በሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርንያ ግዛት ጷጉሜ 2/2016 ዓ/ም ለስድስተኛ ግዜ በሚያካሂደው የሽልማት ፕሮግራም ላይ "መልካም የሰሩ ይመስገናሉ" በሚል ዓላማ ለሽልማት የመረጣቸውን ግለሰቦች ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት አንጋፋው የሙዚቃ ባለሙያ እና የሮሀ ባንድ መስራች ጊታሪስት አቶ ሰላም ስዩም (ሰላሚኖ)፣ በታሪክ ጥናት እና ምርምር ዘርፍ የሚታወቁት ፕሮፌሰር ሀይሌ ላሬቦ፣ በበጎ አድራጎት ስራ ዘርፍ ዶ/ር እፀገነት አየለ፣ ትምህርት ቤቶችን በኢትዮጵያ በመገንባት የሚታወቁት የፍሬገነት ፋውንዴሽን መስራች ወ/ሮ ኤልሳቤጥ አስራት እና የመሠረት ሚድያ መስራች ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት ከሚድያ ተሸላሚ ሆነው ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አሁን የአፍሪካ ህብረት ተብሎ የሚጠራው) ባለራዕይ የነበሩት አቶ ከተማ ይፍሩ ደግሞ በስማቸው ልዩ የክቡር የመታሰቢያ ሽልማት ተሸላሚ ሆነው ተመርጠዋል።

📍 መረጃው የመሰረት ሚዲያ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አብርሆት ቤተመጻሕፍት ለምሽት ተገልጋዮች የመጓጓዣ አገልግሎት ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የቤተመፅሀፍቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብ አየሁ ማሞ ለትርታ እንደገለጹት ፣  በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ ለምሽት ተጠቃሚዎቹ የመጓጓዣ አገልግሎትን ለመጀመር ታቅዷል።

አምሽተዉ የሚያነቡ ተገልጋዮች እንዳይቸገሩ በሚል ቤተመፅሐፉ ሊሰጠዉ  ያቀደዉ የትራንስፖርት አገልግሎትን አሁን ላይ ያልጀመረው በክረምቱ ግዜ ቤተ መፅሀፍቱን የሚጠቀሙ ተገልጋዮች ቁጥር ከበጋው ወቅት ተጠቃሚዎች ጋር ሲነጻጸር እምብዛም በመሆኑ ነው ሲሉም ተናግረዋል ።

በክረምቱ ወቅት የአንባቢያን ቁጥር በቀን ዉስጥ ከ5-6 ሺህ እንደሚሆን የጠቀሱ ሲኾን፣ በበጋዉ ግዜ ግን በቀን ዉስጥ በአማካኝ ከ16 እስከ17 ሺህ የሚደርሱ ተገልጋዮች በቤተ-መፅሀፉቱ እንደሚጠቀሙ ነው የገለጹት።

በመሆኑም አብርሆት ቤተ-መፅሐፍ ሊሰጠዉ ያቀደዉ የትራንስፖርት አገልግሎት ከተገልጋዮች ቁጥርና ፍላጎት አንፃር፤ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዉ በሚጀመርበትና ትምህርት ቤቶች ክፍት በሚሆኑባቸዉ ግዜ ለማስጀመር ዕቅድ መያዙን የቤተ-መፅሀፍቱ ዋና ዳይሬክተር ነግረዉናል።

በቀጣይም አብርሆት ቤተ መጽሀፍት በሮቦት በመታገዝ የሚሰሩ ስራዎችን ጨምሮ፣ የፈጠራ ስራዎችንና  የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ለማበረታታት አጋዥ ግብዓቶችን በማሟላት አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ እንደሆነ ነው የተቋሙ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ ለትርታ ያስታወቁት።

📍መረጃው የትርታ 97.6 FM ትባረክ ኢሳያስ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን!

"መንግሥቱ ኃ/ማርያም:የስደተኛው መሪ ትረካዎች"

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አዲስ የጃዝ ካፌ በአዲስ አበባ ዛሬ ይከፈታል

በዝነኛው ፒያኒስት ሳሙኤል ይርጋ እና ጓደኞቹ የተቋቋመው "የከርሞ ሰው" የተሰኘ የጃዝ ካፌ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 16 2016 ዓ.ም በይፋ እንደሚከፈት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

በዚህ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ላይም የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት ተዘጋጅቷል። በጃዝ ሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ድምጻዊ ጌቴ አንለይ እና ድምጻዊት ገነት ማስረሻ በፒያኒስት ሳሙኤል ይርጋ ታጅበው ያቀነቅናሉ ተብሏል።

ዛሬ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ የሙዚቃ መርሐግብር ላይ ጃዝ፣ ባህላዊ ፣ ፊውዥን፣ ፈንክ እና የተለያዩ ሙዚቃዎች ይቀርቡበታል።

ቦሌ ሩዋንድ መንገድ ከዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር አካባቢ የሚገኘው ይህ የጃዝ ካፌ የጃዝ ሙዚቃዎችን ለማቅረብ እና ለማድመጥ የተመቸ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊት የማ "ስንት ነው ?" ሙዚቃ ድጋሚ ተሰራ

በድምጻዊት የማርያም ቸርነት በመድረክ ስሟ (የማ) "የደጋ ሰው" የሙዚቃ አልበም ውስጥ ከተካተቱ ሙዚቃዎች ውስጥ "ስንት ነው?" የተሰኘው ሙዚቃ በሁለገቡ የሙዚቃ ሰው እዩኤል መንግስቱ ድጋሚ (Remix)ተደርጎ ዛሬ ለአድማጮች ቀርቧል።

ድምጻዊት የማርያም ቸርነት(የማ) በማህበራዊ ትስስር ገጿ "የመጀመሪያ የሙዚቃ ስራዬ ከሆነው "የደጋ ሰው" አልበም ውስጥ አንድ ሙዚቃ ለየት ባለ መልኩ ሪሚክስ ተደርጓል" ብላለች።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ንግስት" የነፍስጡሮች የፋሽን ሾው ሊካሄድ ነው

ታዋቂ ኤቨንትስ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "ንግስት" የተሰኘ የነፍስጡሮች የፋሽን ሾው ውድድር በአዲሱ ዓመት መስከረም 11 2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚህ የነፍስጡሮች ፋሽን ውድድር ለመውለድ የተዘጋጁ ነፍሰ ጡሮች በዲዛይነሮች በተዘጋጁ ቅንጡ አልባሳት የተዘጋጁላቸውን ልብሶች በመጠቀም ተውበው የሚታዩበት ነው ተብሏል።

በውድድሩ ላይ ነፍሰጡር ተወዳዳሪዎች ምቾትን ተጎናጽፈው እራሳቸውን የሚገልጹበት፣ ለተለያዩ ስሜቶች ተጋላጭ የሆነውን ይህንን የእርግዝና ጊዜ በተዝናኖት የሚያሳልፉበት፣ ብሎም ከትዳር አጋራቸው ጋር በሚጠየቁት የእርግዝና ነክ ጥያቄዎቸ አማካኝነት እየተዳኙ ተወዳድረው ሽልማቶችን የሚያገኙበት እንደሆነም ተነግሯል።

የፕሮግራሙ ዓላማ የውድድሩ አላማ በኢትዮጵያ በስፋት እየተስተዋለ ስለሚገኘው የእናቶችን በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ህይወት ማለፍን አስመልክቶ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል።

ነፍሰ ጡርነት ውበት መሆኑን ለሌሎች በማስገንዘብ እና የጤና ክትትል የማያደርጉ ነፍሰ ጡር እናቶችን ክትትላቸውን እንዲያደርጉ መንገድን የሚያመላክት መሆኑም ተመላክቷል።

በሀገራችን በዓመት በአማካይ እስከ አስር ሺህ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል።

በዚህ ፋሽን ሾው ላይ ጤነኛ እና ፍቃደኛ የሆኑ ማንኛውም እናቶች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መብራት በመጥፋቱ ቴአትር ሳይቀረብ ቀረ!

በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቴአትር ቤት ዛሬ ነሐሴ 16 2016 ዓ.ም መብራት በመጥፋቱ ምክንያት ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ይቀርብ የነበረው "ጎዶን ጥበቃ" የተሰኘው ተውኔት ሳይቀርብ እንደቀረ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የ"ጎዶን ጥበቃ " ተውኔት አዘጋጅ የሆነው ዳግም ሲሳይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ " ዛሬ ትርኢት ባለመኖሩ ይቅርታ እንጠይቃለን።ምክንያቱ ምን ይሆን ቢሉ "መብራት የለም" ነው" ብሏል።

አሁን ላይ እንደ ሀገር አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ብቸኛው የቴአትር አግልግሎት ሰጪ "የቴአትር ቤት" እንደሆነ ይታወቃል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አባስሽው" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊ ሻሎም ደሳለኝ "አባስሽው" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ አመሻሹን በምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ዩቲዩብ ቻናል በኩል ተለቋል።

የሙዚቃው ግጥምና ዜማ በሻሎም ደሳለኝ የተሰራ ሲሆን አሬንጅመንት ሚክሲንጉን ላይ መኳንንት አዲሱ ተሳትፏል።የሙዚቃው ቪዲዮው በአምሃ ዱግማ ዳይሬክት ተደርጓል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017" ተከፈተ!

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን እና ሊየን ቢዝነስ ግሩፕ ከአሴነቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር  ያዘጋጁት "ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017" ኤግዚቢሽንና ባዛር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል።

በመክፈቻው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሃብቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ተመርቆ ተጀምሯል፡፡

"ሲቢኢ ብር ኤክስT 2017" ኤግዚቢሽን እና ባዛር ከዛሬ ነሐሴ 16 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ሞ ለተከታታይ 21 ቀናት ይቆያል።

በዚህ ኤክስፖ ላይ ከአስር በላይ መንደሮች የተዘጋጁ ሲሆን ከሸመታና ከጉብኝት በተጨማሪ በየቀኑ ከ35 በላይ ተወዳጅ ደሞጻዊያን የሚያቀነቅኑበት ልዩ የሙዚቃና የመዝናኛ ፌስቲቫልም ተዘጋጅቷል።

እስከ እንቁጣጣሽ ዋዜማ ድረስ በተከታታይ በሚከናወነው ፌስቲቫል ላይ የመድረክ የሙዚቃ ክዋኒያቸውን ከሚያቀርቡ ድምጻዊያን መካከል  አብርሃም ገብረ መድህን፣ መሰሉ ፈንታሁን ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ አንዱዓለም ጎሣ፣ ኃይለየሱስ ግርማ፣ ጌቴ አንለይ፣ ሃይማኖት ግርማ፣ ተአምር ግዛው ፣አምሳል ምትኬና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በኤክስፖ መክፈቻ እና መዝጊያ ላይ ከሚኖረው የሙዚቃ ዝግጅት በተጨማሪ ከነገ ስቲያ ቅዳሜ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ድምጻዊ አብርሃም ገብረ መድህንን ጨምሮ እውቅ ድምጻዊያን በታዋቂ ባንድ በመታጀብ የሚያቀነቅነበትን ልዩ ኮንሰርት ተዘጋጅቷል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሙዚቀኞች ጥሪ አቀረበ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን አየር መንገዱ በሚያቀርበው የአውሮፕላን ውስጥ የመዝናኛ ቻናሎች ምርጫ ውስጥ እንዲካተትላችሁ ለሙዚቀኞች ጥሪውን አቅርቧል።

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ "ክቡራን መንገደኞቹ አዝናኝ የበረራ ቆይታ ይኖራቸው ዘንድ የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን የሚያቀርበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሙዚቃ ስራዎች 140 ወደሚጠጉ ዓለም-አቀፍ መዳረሻዎቹ ለሚጓዙ መንገደኞቹ ተደራሽ የሚሆኑበትን አማራጭ ይዞ ብቅ ብሏል።

በመሆኑም የሙዚቃ ስራዎቻችሁ አየር መንገዱ በሚያቀርበው የአውሮፕላን ውስጥ የመዝናኛ ቻናሎች ምርጫ ውስጥ እንዲካተትላችሁ የምትፈልጉ የጥበብ ባለሙያዎች በሙሉ ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ሙዚቃዎቻችሁን ይዛችሁ በመቅረብ የዕድሉ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በስልክ ቁጥሮቻችን 0115178079 እና 0115178097 ይደውሉ። አሊያም በኢሜል አድራሻዎቻችን HiwotGe@ethiopianairlines.com ወይም  
HilinaBel@ethiopianairlines.com ይፃፉልን " ብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ከ31 ዓመታት በኃላ ለንባብ የሚበቃው መጽሐፍ

የረ/ፕ ሙሉጌታ ጀዋሬ "ወጀብ" የተሰኘ ልቦለድ መጽሐፍ ከሰላሳ አንድ ዓመታት በኃላ ከነገ ስቲያ ለንባብ ሊበቃ እንደሆነ ኤቨንት ድረገፅ ሰምቷል።

በ1980ዎቹ አጋማሽ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የነበረውን የተማሪዎች እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ የተፃፈው መፅሀፉ የሕትመት ሂደቱን አጠናቆ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2016ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል ተብሏል።

"ወጀብ" የተሰኘው ቀዳሚው መፅሀፍ የመጀመሪያው ቅፅ ሲሆን ሁለተኛው የመፅሀፉ ቅፅ የአንባቢያኑን ግብረ መልስ ጠብቆ ለንባብ እንዲበቃ ይደጋል ተብሏል።

"ወጀብ" መጽሐፍ በ399 ገፆች የተቀነበበው በ550 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ድርሰቱ የተመሠረተበት እውነተኛ ታሪክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተከሰተበት ወቅት የነበረውን የተማሪዎች አካዳሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ የሕይወት እውነታዎችን በተራቀቀ አቀራረብ እንዲሁም በግልጽ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

በዋናነትም በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች እንቅስቃሴ ሂደት ውስጥ እምብዛም ትኩረት ያልተሰጠውን የ1980ዎቹን ጉልህ የታሪክ ክፍተት እንደሚሞላም ተጠቁሟል።

በመፀሀፉ ውስጥ ያለውን ታሪክ መነሻ ያደረገ አዲስ ሙዚቃም መሰናዳቱ የተገለፀ ሲሆን በግጥም ሙሉጌታ ጀዋሬ እንዲሁም በዜማ አለማየሁ ደመቀ እንደተሳተፉበትና የፊታችን እሁድ ከመጽሐፉ ምርቃት ጎን ለጎን ሙዚቃው እንደሚለቀቅ ተገልጿል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌“መንግስቱ ኃ/ማርያም: የሥደተኛው መሪ ትረካዎች” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል

በደራሲ ይታገሱ ጌትነት የተዘጋጀው "መንግስቱ ኃ/ማርያም:የሥደተኛው መሪ ትረካዎች" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ነሐሴ 18 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

መጽሐፉ የቀድሞው የኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ከልጅነት አንስቶ ዛሬ እስካሉበት የስደት ዘመን ድረስ የተጓዙባቸውን ግላዊ ታሪኮች፣ የሕይወት ገጠመኞች እና ወቅታዊና ነባር ፖለቲካዊ ግምገማዎችን አካትቶ ይዟል፡፡

የዚህ መጽሐፍ ዐቢይ ትኩረቱም እንደሰው የኮሎኔል መንግሥቱ  ኃይለ ማርያምን ማንነነት መመልከትና ያልተደመጠውን ድምጽ መሥማት ነው ተብሏል።

የመጽሐፉ ጸሐፊ ይታገሱ ጌትነት"በሕይወቴ ፈጸምኳቸው ከምላቸው በርካታ ቁም ነገሮች ውስጥ ምናልባት ይኽኛው ዐብዩ ይሆናል ብዬ አምናለሁ"በማለት ተናግሯል።

በተጨማሪም"በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ቁምነገሮች ለታሪክ አጥኚዎች ግብአት፣ ለከያንያን የመነሻ ሀሳብ፣ ለፖለቲከኞች ትምህርት፣ ለጋዜጠኞች መረጃ፣ ለወጣቶች የሕይወት ልምድን፣ ለሌችም እንደሙያቸውና ማንነታቸው የሚወስዱት ቁምነገር አያጡበትም" ብሏል።

የመጽሐፉ አሳታሚና አከፋፋይ ዋሊያ መጽሐፍ መደብር ሲሆን ከነገ ጀምሮ በበርካታ መጻሕፍት መደብሮች ልታገኙ ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1