Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.12K photos
14 videos
4 files
4.74K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌አርቲስት ነብዩ እንድሪስ የክብር እንግዳ የሆነበት "ክሬቲቭ ኮኔክት" የተሰኘ ፕሮግራም አርብ ይካሄዳል

አርቲስት ነብዩ እንድሪያስ የክብር እንግዳ የሆነበት "ክሬቲቭ ኮኔክት" የተሰኘ ዝግጅት የፊታችን አርብ ነሐሴ17 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ጎተ ኢንስቲትዩት ውስጥ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አርቲስት ነብዩ እንድሪስ በቅርቡ ለእይታ የበቁቱን 6:00 ከሌሊቱ፣ ጃናሞራ ፊልሞችን ጨምሮ በሌሎችም በበርካታ ፊልሞች ተሳትፏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ጳጉሜን የኢትዮጵያውን መዝናኛና ባህል ማዕከል የዘንድሮ አሸናፊዎቹን ይፋ አደረገ

መቀመጫውን በአሜሪካ ሀገር ያደረገው ጳጉሜን የኢትዮጵያውን መዝናኛና ባህል ማዕከል የዘንድሮ አሸናፊዎቹን ዝርዝር  ይፋ አድርጓል።

ማዕከሉ በሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርንያ ግዛት ጷጉሜ 2/2016 ዓ/ም ለስድስተኛ ግዜ በሚያካሂደው የሽልማት ፕሮግራም ላይ "መልካም የሰሩ ይመስገናሉ" በሚል ዓላማ ለሽልማት የመረጣቸውን ግለሰቦች ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት አንጋፋው የሙዚቃ ባለሙያ እና የሮሀ ባንድ መስራች ጊታሪስት አቶ ሰላም ስዩም (ሰላሚኖ)፣ በታሪክ ጥናት እና ምርምር ዘርፍ የሚታወቁት ፕሮፌሰር ሀይሌ ላሬቦ፣ በበጎ አድራጎት ስራ ዘርፍ ዶ/ር እፀገነት አየለ፣ ትምህርት ቤቶችን በኢትዮጵያ በመገንባት የሚታወቁት የፍሬገነት ፋውንዴሽን መስራች ወ/ሮ ኤልሳቤጥ አስራት እና የመሠረት ሚድያ መስራች ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት ከሚድያ ተሸላሚ ሆነው ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አሁን የአፍሪካ ህብረት ተብሎ የሚጠራው) ባለራዕይ የነበሩት አቶ ከተማ ይፍሩ ደግሞ በስማቸው ልዩ የክቡር የመታሰቢያ ሽልማት ተሸላሚ ሆነው ተመርጠዋል።

📍 መረጃው የመሰረት ሚዲያ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አብርሆት ቤተመጻሕፍት ለምሽት ተገልጋዮች የመጓጓዣ አገልግሎት ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የቤተመፅሀፍቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብ አየሁ ማሞ ለትርታ እንደገለጹት ፣  በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ ለምሽት ተጠቃሚዎቹ የመጓጓዣ አገልግሎትን ለመጀመር ታቅዷል።

አምሽተዉ የሚያነቡ ተገልጋዮች እንዳይቸገሩ በሚል ቤተመፅሐፉ ሊሰጠዉ  ያቀደዉ የትራንስፖርት አገልግሎትን አሁን ላይ ያልጀመረው በክረምቱ ግዜ ቤተ መፅሀፍቱን የሚጠቀሙ ተገልጋዮች ቁጥር ከበጋው ወቅት ተጠቃሚዎች ጋር ሲነጻጸር እምብዛም በመሆኑ ነው ሲሉም ተናግረዋል ።

በክረምቱ ወቅት የአንባቢያን ቁጥር በቀን ዉስጥ ከ5-6 ሺህ እንደሚሆን የጠቀሱ ሲኾን፣ በበጋዉ ግዜ ግን በቀን ዉስጥ በአማካኝ ከ16 እስከ17 ሺህ የሚደርሱ ተገልጋዮች በቤተ-መፅሀፉቱ እንደሚጠቀሙ ነው የገለጹት።

በመሆኑም አብርሆት ቤተ-መፅሐፍ ሊሰጠዉ ያቀደዉ የትራንስፖርት አገልግሎት ከተገልጋዮች ቁጥርና ፍላጎት አንፃር፤ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዉ በሚጀመርበትና ትምህርት ቤቶች ክፍት በሚሆኑባቸዉ ግዜ ለማስጀመር ዕቅድ መያዙን የቤተ-መፅሀፍቱ ዋና ዳይሬክተር ነግረዉናል።

በቀጣይም አብርሆት ቤተ መጽሀፍት በሮቦት በመታገዝ የሚሰሩ ስራዎችን ጨምሮ፣ የፈጠራ ስራዎችንና  የቴክኖሎጂ ዉጤቶችን ለማበረታታት አጋዥ ግብዓቶችን በማሟላት አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ እንደሆነ ነው የተቋሙ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ ለትርታ ያስታወቁት።

📍መረጃው የትርታ 97.6 FM ትባረክ ኢሳያስ ነው።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን!

"መንግሥቱ ኃ/ማርያም:የስደተኛው መሪ ትረካዎች"

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌አዲስ የጃዝ ካፌ በአዲስ አበባ ዛሬ ይከፈታል

በዝነኛው ፒያኒስት ሳሙኤል ይርጋ እና ጓደኞቹ የተቋቋመው "የከርሞ ሰው" የተሰኘ የጃዝ ካፌ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 16 2016 ዓ.ም በይፋ እንደሚከፈት ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

በዚህ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ላይም የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት ተዘጋጅቷል። በጃዝ ሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ድምጻዊ ጌቴ አንለይ እና ድምጻዊት ገነት ማስረሻ በፒያኒስት ሳሙኤል ይርጋ ታጅበው ያቀነቅናሉ ተብሏል።

ዛሬ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ የሙዚቃ መርሐግብር ላይ ጃዝ፣ ባህላዊ ፣ ፊውዥን፣ ፈንክ እና የተለያዩ ሙዚቃዎች ይቀርቡበታል።

ቦሌ ሩዋንድ መንገድ ከዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር አካባቢ የሚገኘው ይህ የጃዝ ካፌ የጃዝ ሙዚቃዎችን ለማቅረብ እና ለማድመጥ የተመቸ እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊት የማ "ስንት ነው ?" ሙዚቃ ድጋሚ ተሰራ

በድምጻዊት የማርያም ቸርነት በመድረክ ስሟ (የማ) "የደጋ ሰው" የሙዚቃ አልበም ውስጥ ከተካተቱ ሙዚቃዎች ውስጥ "ስንት ነው?" የተሰኘው ሙዚቃ በሁለገቡ የሙዚቃ ሰው እዩኤል መንግስቱ ድጋሚ (Remix)ተደርጎ ዛሬ ለአድማጮች ቀርቧል።

ድምጻዊት የማርያም ቸርነት(የማ) በማህበራዊ ትስስር ገጿ "የመጀመሪያ የሙዚቃ ስራዬ ከሆነው "የደጋ ሰው" አልበም ውስጥ አንድ ሙዚቃ ለየት ባለ መልኩ ሪሚክስ ተደርጓል" ብላለች።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ንግስት" የነፍስጡሮች የፋሽን ሾው ሊካሄድ ነው

ታዋቂ ኤቨንትስ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "ንግስት" የተሰኘ የነፍስጡሮች የፋሽን ሾው ውድድር በአዲሱ ዓመት መስከረም 11 2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚህ የነፍስጡሮች ፋሽን ውድድር ለመውለድ የተዘጋጁ ነፍሰ ጡሮች በዲዛይነሮች በተዘጋጁ ቅንጡ አልባሳት የተዘጋጁላቸውን ልብሶች በመጠቀም ተውበው የሚታዩበት ነው ተብሏል።

በውድድሩ ላይ ነፍሰጡር ተወዳዳሪዎች ምቾትን ተጎናጽፈው እራሳቸውን የሚገልጹበት፣ ለተለያዩ ስሜቶች ተጋላጭ የሆነውን ይህንን የእርግዝና ጊዜ በተዝናኖት የሚያሳልፉበት፣ ብሎም ከትዳር አጋራቸው ጋር በሚጠየቁት የእርግዝና ነክ ጥያቄዎቸ አማካኝነት እየተዳኙ ተወዳድረው ሽልማቶችን የሚያገኙበት እንደሆነም ተነግሯል።

የፕሮግራሙ ዓላማ የውድድሩ አላማ በኢትዮጵያ በስፋት እየተስተዋለ ስለሚገኘው የእናቶችን በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ህይወት ማለፍን አስመልክቶ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል።

ነፍሰ ጡርነት ውበት መሆኑን ለሌሎች በማስገንዘብ እና የጤና ክትትል የማያደርጉ ነፍሰ ጡር እናቶችን ክትትላቸውን እንዲያደርጉ መንገድን የሚያመላክት መሆኑም ተመላክቷል።

በሀገራችን በዓመት በአማካይ እስከ አስር ሺህ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል።

በዚህ ፋሽን ሾው ላይ ጤነኛ እና ፍቃደኛ የሆኑ ማንኛውም እናቶች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌መብራት በመጥፋቱ ቴአትር ሳይቀረብ ቀረ!

በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቴአትር ቤት ዛሬ ነሐሴ 16 2016 ዓ.ም መብራት በመጥፋቱ ምክንያት ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ይቀርብ የነበረው "ጎዶን ጥበቃ" የተሰኘው ተውኔት ሳይቀርብ እንደቀረ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የ"ጎዶን ጥበቃ " ተውኔት አዘጋጅ የሆነው ዳግም ሲሳይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ " ዛሬ ትርኢት ባለመኖሩ ይቅርታ እንጠይቃለን።ምክንያቱ ምን ይሆን ቢሉ "መብራት የለም" ነው" ብሏል።

አሁን ላይ እንደ ሀገር አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ብቸኛው የቴአትር አግልግሎት ሰጪ "የቴአትር ቤት" እንደሆነ ይታወቃል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አባስሽው" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊ ሻሎም ደሳለኝ "አባስሽው" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ዛሬ አመሻሹን በምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ዩቲዩብ ቻናል በኩል ተለቋል።

የሙዚቃው ግጥምና ዜማ በሻሎም ደሳለኝ የተሰራ ሲሆን አሬንጅመንት ሚክሲንጉን ላይ መኳንንት አዲሱ ተሳትፏል።የሙዚቃው ቪዲዮው በአምሃ ዱግማ ዳይሬክት ተደርጓል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017" ተከፈተ!

ታሜሶል ኮሙኒኬሽን እና ሊየን ቢዝነስ ግሩፕ ከአሴነቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር  ያዘጋጁት "ሲቢኢ ብር ኤክስፖ 2017" ኤግዚቢሽንና ባዛር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል።

በመክፈቻው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሃብቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ተመርቆ ተጀምሯል፡፡

"ሲቢኢ ብር ኤክስT 2017" ኤግዚቢሽን እና ባዛር ከዛሬ ነሐሴ 16 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ሞ ለተከታታይ 21 ቀናት ይቆያል።

በዚህ ኤክስፖ ላይ ከአስር በላይ መንደሮች የተዘጋጁ ሲሆን ከሸመታና ከጉብኝት በተጨማሪ በየቀኑ ከ35 በላይ ተወዳጅ ደሞጻዊያን የሚያቀነቅኑበት ልዩ የሙዚቃና የመዝናኛ ፌስቲቫልም ተዘጋጅቷል።

እስከ እንቁጣጣሽ ዋዜማ ድረስ በተከታታይ በሚከናወነው ፌስቲቫል ላይ የመድረክ የሙዚቃ ክዋኒያቸውን ከሚያቀርቡ ድምጻዊያን መካከል  አብርሃም ገብረ መድህን፣ መሰሉ ፈንታሁን ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ አንዱዓለም ጎሣ፣ ኃይለየሱስ ግርማ፣ ጌቴ አንለይ፣ ሃይማኖት ግርማ፣ ተአምር ግዛው ፣አምሳል ምትኬና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በኤክስፖ መክፈቻ እና መዝጊያ ላይ ከሚኖረው የሙዚቃ ዝግጅት በተጨማሪ ከነገ ስቲያ ቅዳሜ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ድምጻዊ አብርሃም ገብረ መድህንን ጨምሮ እውቅ ድምጻዊያን በታዋቂ ባንድ በመታጀብ የሚያቀነቅነበትን ልዩ ኮንሰርት ተዘጋጅቷል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሙዚቀኞች ጥሪ አቀረበ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን አየር መንገዱ በሚያቀርበው የአውሮፕላን ውስጥ የመዝናኛ ቻናሎች ምርጫ ውስጥ እንዲካተትላችሁ ለሙዚቀኞች ጥሪውን አቅርቧል።

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ "ክቡራን መንገደኞቹ አዝናኝ የበረራ ቆይታ ይኖራቸው ዘንድ የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችን የሚያቀርበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሙዚቃ ስራዎች 140 ወደሚጠጉ ዓለም-አቀፍ መዳረሻዎቹ ለሚጓዙ መንገደኞቹ ተደራሽ የሚሆኑበትን አማራጭ ይዞ ብቅ ብሏል።

በመሆኑም የሙዚቃ ስራዎቻችሁ አየር መንገዱ በሚያቀርበው የአውሮፕላን ውስጥ የመዝናኛ ቻናሎች ምርጫ ውስጥ እንዲካተትላችሁ የምትፈልጉ የጥበብ ባለሙያዎች በሙሉ ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ሙዚቃዎቻችሁን ይዛችሁ በመቅረብ የዕድሉ ተሳታፊ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

ለተጨማሪ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ በስልክ ቁጥሮቻችን 0115178079 እና 0115178097 ይደውሉ። አሊያም በኢሜል አድራሻዎቻችን HiwotGe@ethiopianairlines.com ወይም  
HilinaBel@ethiopianairlines.com ይፃፉልን " ብሏል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ከ31 ዓመታት በኃላ ለንባብ የሚበቃው መጽሐፍ

የረ/ፕ ሙሉጌታ ጀዋሬ "ወጀብ" የተሰኘ ልቦለድ መጽሐፍ ከሰላሳ አንድ ዓመታት በኃላ ከነገ ስቲያ ለንባብ ሊበቃ እንደሆነ ኤቨንት ድረገፅ ሰምቷል።

በ1980ዎቹ አጋማሽ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የነበረውን የተማሪዎች እንቅስቃሴ መሰረት አድርጎ የተፃፈው መፅሀፉ የሕትመት ሂደቱን አጠናቆ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2016ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል ተብሏል።

"ወጀብ" የተሰኘው ቀዳሚው መፅሀፍ የመጀመሪያው ቅፅ ሲሆን ሁለተኛው የመፅሀፉ ቅፅ የአንባቢያኑን ግብረ መልስ ጠብቆ ለንባብ እንዲበቃ ይደጋል ተብሏል።

"ወጀብ" መጽሐፍ በ399 ገፆች የተቀነበበው በ550 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ድርሰቱ የተመሠረተበት እውነተኛ ታሪክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተከሰተበት ወቅት የነበረውን የተማሪዎች አካዳሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ የሕይወት እውነታዎችን በተራቀቀ አቀራረብ እንዲሁም በግልጽ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

በዋናነትም በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች እንቅስቃሴ ሂደት ውስጥ እምብዛም ትኩረት ያልተሰጠውን የ1980ዎቹን ጉልህ የታሪክ ክፍተት እንደሚሞላም ተጠቁሟል።

በመፀሀፉ ውስጥ ያለውን ታሪክ መነሻ ያደረገ አዲስ ሙዚቃም መሰናዳቱ የተገለፀ ሲሆን በግጥም ሙሉጌታ ጀዋሬ እንዲሁም በዜማ አለማየሁ ደመቀ እንደተሳተፉበትና የፊታችን እሁድ ከመጽሐፉ ምርቃት ጎን ለጎን ሙዚቃው እንደሚለቀቅ ተገልጿል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌“መንግስቱ ኃ/ማርያም: የሥደተኛው መሪ ትረካዎች” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ነገ ለንባብ ይበቃል

በደራሲ ይታገሱ ጌትነት የተዘጋጀው "መንግስቱ ኃ/ማርያም:የሥደተኛው መሪ ትረካዎች" የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ነሐሴ 18 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደሚቀርብ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

መጽሐፉ የቀድሞው የኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ከልጅነት አንስቶ ዛሬ እስካሉበት የስደት ዘመን ድረስ የተጓዙባቸውን ግላዊ ታሪኮች፣ የሕይወት ገጠመኞች እና ወቅታዊና ነባር ፖለቲካዊ ግምገማዎችን አካትቶ ይዟል፡፡

የዚህ መጽሐፍ ዐቢይ ትኩረቱም እንደሰው የኮሎኔል መንግሥቱ  ኃይለ ማርያምን ማንነነት መመልከትና ያልተደመጠውን ድምጽ መሥማት ነው ተብሏል።

የመጽሐፉ ጸሐፊ ይታገሱ ጌትነት"በሕይወቴ ፈጸምኳቸው ከምላቸው በርካታ ቁም ነገሮች ውስጥ ምናልባት ይኽኛው ዐብዩ ይሆናል ብዬ አምናለሁ"በማለት ተናግሯል።

በተጨማሪም"በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ቁምነገሮች ለታሪክ አጥኚዎች ግብአት፣ ለከያንያን የመነሻ ሀሳብ፣ ለፖለቲከኞች ትምህርት፣ ለጋዜጠኞች መረጃ፣ ለወጣቶች የሕይወት ልምድን፣ ለሌችም እንደሙያቸውና ማንነታቸው የሚወስዱት ቁምነገር አያጡበትም" ብሏል።

የመጽሐፉ አሳታሚና አከፋፋይ ዋሊያ መጽሐፍ መደብር ሲሆን ከነገ ጀምሮ በበርካታ መጻሕፍት መደብሮች ልታገኙ ትችላላችሁ ተብላችኋል።

ለተጨማሪው :https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !

አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር  እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።

📍 የፍቅር ካቴና

ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ

📍 "እሳት ወይ አበባ"

ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባሎች እና ሚስቶች

ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ባቡሩ

ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 ሸምጋይ

ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

📍 እምዩ ብረቷ

ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር

የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የድምጻዊ መሳይ ተፈራ የሙዚቃ አልበም ምርቃት !

የድምጻዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን" የሙዚቃ አልበም የምርቃት ሥነሥርዓት በርካታ ዝነኛ ሙዚቀኞች በተገኙበት ዛሬ አመሻሹን በማርዮት ሆቴል ውስጥ እንደሚካሄድ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጁፒተር ብራና ንባብ ቡድን ውይይት

ዛሬ በጁፒተር ብራና የንባብ ቡድን "በትውልዶች መካከል የሚደረግ ወግ " በሚል አብይ ርዕስ ውይይት ይካሄዳል። የዕለቱም እንግዳ የህግ ባለሙያ ታምራት ኪዳነማርያም ናቸው።

ቀን፡ ቅዳሜ ነሀሴ 18 ፣ 2016
ሰዓት፡ ከቀኑ 9፡45 – 12፡00
ቦታ፡ ጁፒተር ሆቴል ካዛንቺስ ቅርንጫፍ

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ !

ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ ዛሬ ነሐሴ 18 2016 ዓ.ም በተለያየ የሙያ ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎችን በአምባሳደር ቴአትር ቤት አስመርቋል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ማዕከል ስራ አስፈጻሚ ሃሰን ሁሴን (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም የኮሌጁ ዲን ቴዎድሮስ አበበ (ረዳት ፕሮፌሰር) እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

የኮሎጁ ዲን ቴዎድሮስ አበበ (ረዳት ፕሮፌሰር) የ"እንኳን ደስ ያላችሁ" መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ "ኮሌጃችን በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ በዲግሪ መርሃ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን አስመርቋል" ብለዋል። አያይዘውም ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች ነጻ የትምሕርት ዕድል እየሰጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወቅት ትምሕርት ላይ የነበሩ፣ በኋላም በሌሎች ተጽዕኖዎች መሃል ሆነው ለተማሩ ተማሪዎች ምስጋናቸውን አቅረበዋል።

በመጀመሪያ ዲግሪ፤ አካውንቲንግና ፋይናንስ፣ ማኔጅመንት፣ በማስተርስ፤ ቢዝነስ ማኔጅመንትና ሂዩማን ሪሶርስ ማኔጅመንት፣ እንዲሁም በደረጃ 4 በሰባት የቴክኒክ እና ሞያ ስልጠና ዘርፎች 850 ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 54 በመቶ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

በዛሬ በተካሄደው የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት ከኮሌጁ ዲን እና ከዕለቱ የክብር ዕንግዳ ተበርክቷል።

ኮሌጁ በማኔጅመንት 418 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 315ቱ ሴቶች፣203ቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው።

በማስተርስ ደረጃ  በኤክስቴንሽንና በመደበኛ ትምህርት ወንድ 109 ሴት 82 ተማሪዎችን አጠቃላይ 191 ተማሪዎች ማስመረቁን ተቋሙ ገልጿል።

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 ደራሲው የላዳ ሹፌር ነገ መጽሐፉን ያስመርቃል!

ጌታቸው ከበደ ይባላል። የላድ ታክሲ ሹፌር ነው። ከስራውም ጎን ለጎን በሥነጽሑፉም ላይ ተሳትፎ ያደርጋል።

ለረጅም ጊዜያት ሲጽፍው የቆየው የልቦለድ መጽሐፉ ቀኑ ደርሶለት ለህትመት ብርሃን በቅቷል።መጽሐፉንም ነገ እንደሚያስመርቅ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የጌታቸው ከበደ አዲስ መጽሐፍ "የወርቅ መርዝ" የተሰኘ ርዕስ ያለው ሲሆን በዘውግ ደረጃ ረጅም ልቦለድ ነው።

በ236 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ በ413 ብር ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።በውስጡም 18 ምዕራፎችን ይዟል።

"የወርቅ መርዝ" ነገ ነሐሴ 19 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) አዳራሽ ውስጥ በድምቀት ይመረቃል።

በዚህ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣አርቲስት ሽፈራው ታሪኩ፣ገጣሚ መንበረማርያም ኃይሉ እና ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል።

ደራሲው ስለመጽሐፉ ርዕስ በመግቢያው የሚከተለውን ብሏል" ይህ መጽሐፍ "የወርቅ መርዝ" ተብሎ ሲሰየም በወርቅ የተመሰለው ፍቅር ሲሆን በመርዝ የተመሰለው ደግሞ ፍቅርን ተከትለው የመጡትን አሉታዊ ተፅእኖዎች ነው"።

የሥነጽሑፍ ቤተሰብ የሆነ ሁሉ በነገው የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ እንዲገኙለት ጥሪውን አስተላልፏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የወጣቷ ድምጻዊት ሔለን አበራ የሙዚቃ ድግስ!

ወጣቷ ድምጻዊት ሔለን አበራ በመድረክ ላይ በቀጥታ የሙዚቃ ስራዎቿን የምታቀርብበት የሙዚቃ ድግስ ነገ ነሐሴ 19 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው ተምሳሌት ኪቺን ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ልዩ ልዩ የሙዚቃ ስራዎችን እንደምታቀርብ ድምጻዊት አስታውቃለች።

ድምጻዊት ሔልን አበራ በአዲሱ ዓመት የጃዝ ጣዕም ያለው የሙዚቃ አልበሟን ለአድማጮች እንደምታደርስ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ የተናገረች ሲሆን ነገ የሚካሄደው የሙዚቃ ዝግጅትም የአልበሟ መደረሻ እንደሆነ ገልጻለች።

https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የባቡጂ የቀብር ሥነሥርዓት

አርቲስት ጌታቸው እጅጉ (ባቡጂ) ከትላንትና በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ባቡጂ ሼፉ 2፣ ወደ ልጅነት፣ ጀማሪ ሌባ፣ እድሜ ለሴት የተሰኙና ሌሎች ከ60 በላይ ፊልሞች ላይ በመተወን በሙያው የራሱን አስተዋፅዖ ያበረክተው አርቲስት ጌታቸው እጅጉ (ባቡጂ) ነሐሴ 18 2016 ዓ.ም በመኖሪያ ቤት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

የአርቲስት ጌታቸው እጅጉ(ባቡጂ) የቀብር ሥነሥርዓት 
ዛሬ ነሐሴ 20 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ላይ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ይፈፀማል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1