📌የሮፍናን ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል
የሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ"የኔ ትውልድ " ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 23 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
ሮፍናን ኑሪ ከሳምንታት በፊት በሐዋሳ እና ወላይታ ሶዶ ከተሞች ስኬታማ ኮንሰርት እንዳቀረበ ማስታወቁ ይታወሳል።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌"ኪዩስ ጃም" የሙዚቃ ዝግጅት
"ኪዩስ ጃም" የሙዚቃ ዝግጅት ትላንት በሞሶብ የሙዚቃ ማዕከል ተካሄዷል።በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ድምጻዊት ጠረፍ ካሣሁን(ኪያ) እና ድምጻዊት ምንሹ ክፍሌ የሙዚቃ ስራዎቻቸው አቅርበዋል።
ፎቶ: በተክሌ ማርኮን

📌"ዳናሽ” ፊልም ዛሬ ይመረቃል
በአብርሃም ታደሰ ተደርሶ ዳይሬክት የተደረገው "ዳናሽ" ፊልም ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዓለም ሲኒማ ተመርቆ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
በ"ዳናሽ" ፊልም ሔኖክ በሪሁን፣ ኤደን አይሹሽም፣ጌታቸው ስለሺ፣ ምስክር ተስፋዬ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈዋል።
በኢነርጂ ፊልም ፕሮዳክሽን እና በቆንጆ ፒክቸርስ ተዘጋጅቶ በየሚ ፒክቸርስ አማካኝነት ለሕዝብ እንዲቀርብ የተሰናዳው ፊልም በዓይነቱ ለየት ያለ እና ጠንካራ ሃሳብ ይዞ የመጣ መሆኑን የፊልሙ አዘጋጅ አብርሃል ታደሰ ገልጸዋል፡፡
አጠቃላይ 3 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት እና 1 ሰዓት ከ46 ደቂቃ የሚፈጅ ርዝማኔ ያለው ፊልሙ ለኢትዮጵያ ፊልም ተመልካቾች የሚመጥን ሃሳብ በማንሳት የሚሞግት፣ ብሎም ለመልካም እሴቶቻችን ዘብ እንድንቆም የሚያበረታታ ስለመሆኑ አዘጋጁ አብርሃል ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

📌"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት በይፋ ተመረቀ !
በአራዳ ፊሊከስ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ቲያትር በመታየት ላይ ያለውና በአርቲስት ኤልያስ ተስፋዬ ተፅፎ በአርቲስት ካሌብ ዋለልኝ እና በአርቲስት ህብረ ቀለመወርቅ የተዘጋጀው "ሦስቱ አይጦች” ተውኔት ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የኮርፖሬት ተቋማት ሃላፊዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት አንደኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በታላቅ ድምቀት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ተመርቋል።
በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሥነ-ጥበብና ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በቴአትሩ የአንድ ዓመት ጉዞ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሞያዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በተውኔቱ ላይ ካሌብ ዋለልኝ ፣ህሊና ሲሳይ ፣ህብረ ቀለመወርቅ ፤ እንዳለ ብርሃኑ፣ ታሪክ አስተርአየ፣አስመላሽ ታምርአየሁ፣ ቸርነት ፍቃዱ ፣መርዕድ ተስፋዬ፣ ሔኖክ ዘርዓብሩክ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።
"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት ከ20 ዓመታት በፊት "የተከፈለ ልብ" በሚል ርዕስ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመድርኮ ነበር።
@EventAddis1

📌የበዕውቀቱ ስዩም ሶስት መጻሕፍት ድጋሚ ታተሙ
የበዕውቀቱ ስዩም ሶስት ተወዳጅ መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ለአንባቢያን ቀረበዋል።
በአንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉትና ከገበያ ጠፍተው የነበሩ የበዕውቀቱ ስዩም "መግባት እና መውጣት" ፣"ስብስብ ግጥሞች" እና "ከአሜን ባሻገር የተሰኙ ሶስት መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ገበያ ላይ ውለዋል::
ገጣሚና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይህን መልዕክት አስፍሯል"ውድ የመጽሀፍ ወዳጆች! ከገበያ ጠፍተው የነበሩት የበእውቀቱ ስዩም መጻሀፍት መካከል ፥ መግባት እና መውጣት፥ ስብስብ ግጥሞች እና ከአሜን ባሻገር ' በድጋሜ ታትመው ለገበያ ቀርበዋል፤ መግዛት ወይም መሸጥ የምትፈልጉ ፥ ለገሐር አመልድ ህንጻ፥ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አይንአለም መጽሀፍ መደብር ጎራ በሉ፤ ስልክ 0911814536"።
መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

📌"የጣዕም ልኬት" ዝግጅት ወደ አየር ሊመለስ ነው
ሙዚቃና ሙዚቃዊ ጉዳዮችን የሚዳስሰው "የጣዕም ልኬት" የሬድዮ ፕሮግራም በቅርቡ ወደ አየር እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የሬድዮ ፕሮግራሙ የሬድዮ ጣቢያውን ከሸገር 102.1 ወደ አንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ቀይሮ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 6:00 እስከ 8:00 ይተላለፋል ተብሏል።
"የጣዕም ልኬት" አዘጋጆች የሙዚቃ ባለሞያዎቹ ሰርፀ ፍሬስብሃት እና ምዕራፍ ተክሌ ናቸው።
የፕሮግራሙ አዘጋጅና የሙዚቃ ባለሞያው ሰርፀ ፍሬስብሃት ማኀበራዊ ትስስር ገፁ" ምንም ብንዘገይ፣ በመጨረሻ አድርገነዋል። ለበርካታ ዓመታት ከጆሯችሁ ርቃ የቆየችው "የጣዕም ልኬት" ተመልሳ ዐየር ላይ ልትውል ነው።በFM ዐዲስ 97.1 ሬዲዮ ሠርክ ቅዳሜ ከ6:00- 8:00።አዘጋጆች፥ ምዕራፍ ተክሌ እና ሠርፀ ፍሬስብሐ። "በሙዚቃዎቻችን የጣዕም መሠረቶች" ላይ ትኩረቷን ያደረገችው የጣዕም ልኬት ተመልሳለችበቅርብ ቀን" ብሏል።

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

📌የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" መጽሐፍ በድምቀት ተመረቀ።
የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት ተመርቋል።
በዕለቱም ግጥሞና ወጎች ተነበዋል፣ ሥነጽሑፋዊ ዳሰሳዎችና የሙዚቃ ዝግጅት ቀርቧል።
ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ከዚህ ቀደም "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ መጻሕፍት አንባቢያን ማድረሱ አይዘነጋም።