📌"ኪዩስ ጃም" የሙዚቃ ዝግጅት
"ኪዩስ ጃም" የሙዚቃ ዝግጅት ትላንት በሞሶብ የሙዚቃ ማዕከል ተካሄዷል።በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ድምጻዊት ጠረፍ ካሣሁን(ኪያ) እና ድምጻዊት ምንሹ ክፍሌ የሙዚቃ ስራዎቻቸው አቅርበዋል።
ፎቶ: በተክሌ ማርኮን
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

📌"ዳናሽ” ፊልም ዛሬ ይመረቃል
በአብርሃም ታደሰ ተደርሶ ዳይሬክት የተደረገው "ዳናሽ" ፊልም ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዓለም ሲኒማ ተመርቆ ለእይታ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።
በ"ዳናሽ" ፊልም ሔኖክ በሪሁን፣ ኤደን አይሹሽም፣ጌታቸው ስለሺ፣ ምስክር ተስፋዬ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈዋል።
በኢነርጂ ፊልም ፕሮዳክሽን እና በቆንጆ ፒክቸርስ ተዘጋጅቶ በየሚ ፒክቸርስ አማካኝነት ለሕዝብ እንዲቀርብ የተሰናዳው ፊልም በዓይነቱ ለየት ያለ እና ጠንካራ ሃሳብ ይዞ የመጣ መሆኑን የፊልሙ አዘጋጅ አብርሃል ታደሰ ገልጸዋል፡፡
አጠቃላይ 3 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት እና 1 ሰዓት ከ46 ደቂቃ የሚፈጅ ርዝማኔ ያለው ፊልሙ ለኢትዮጵያ ፊልም ተመልካቾች የሚመጥን ሃሳብ በማንሳት የሚሞግት፣ ብሎም ለመልካም እሴቶቻችን ዘብ እንድንቆም የሚያበረታታ ስለመሆኑ አዘጋጁ አብርሃል ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

📌"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት በይፋ ተመረቀ !
በአራዳ ፊሊከስ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ቲያትር በመታየት ላይ ያለውና በአርቲስት ኤልያስ ተስፋዬ ተፅፎ በአርቲስት ካሌብ ዋለልኝ እና በአርቲስት ህብረ ቀለመወርቅ የተዘጋጀው "ሦስቱ አይጦች” ተውኔት ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የኮርፖሬት ተቋማት ሃላፊዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት አንደኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በታላቅ ድምቀት በአንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት ተመርቋል።
በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሥነ-ጥበብና ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በቴአትሩ የአንድ ዓመት ጉዞ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሞያዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በተውኔቱ ላይ ካሌብ ዋለልኝ ፣ህሊና ሲሳይ ፣ህብረ ቀለመወርቅ ፤ እንዳለ ብርሃኑ፣ ታሪክ አስተርአየ፣አስመላሽ ታምርአየሁ፣ ቸርነት ፍቃዱ ፣መርዕድ ተስፋዬ፣ ሔኖክ ዘርዓብሩክ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።
"ሦስቱ አይጦች" ተውኔት ከ20 ዓመታት በፊት "የተከፈለ ልብ" በሚል ርዕስ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተመድርኮ ነበር።
@EventAddis1

📌የበዕውቀቱ ስዩም ሶስት መጻሕፍት ድጋሚ ታተሙ
የበዕውቀቱ ስዩም ሶስት ተወዳጅ መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ለአንባቢያን ቀረበዋል።
በአንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉትና ከገበያ ጠፍተው የነበሩ የበዕውቀቱ ስዩም "መግባት እና መውጣት" ፣"ስብስብ ግጥሞች" እና "ከአሜን ባሻገር የተሰኙ ሶስት መጻሕፍት በድጋሚ ታትመው ገበያ ላይ ውለዋል::
ገጣሚና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይህን መልዕክት አስፍሯል"ውድ የመጽሀፍ ወዳጆች! ከገበያ ጠፍተው የነበሩት የበእውቀቱ ስዩም መጻሀፍት መካከል ፥ መግባት እና መውጣት፥ ስብስብ ግጥሞች እና ከአሜን ባሻገር ' በድጋሜ ታትመው ለገበያ ቀርበዋል፤ መግዛት ወይም መሸጥ የምትፈልጉ ፥ ለገሐር አመልድ ህንጻ፥ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አይንአለም መጽሀፍ መደብር ጎራ በሉ፤ ስልክ 0911814536"።
መረጃው የይትባረክ ዋለልኝ ነው።

📌"የጣዕም ልኬት" ዝግጅት ወደ አየር ሊመለስ ነው
ሙዚቃና ሙዚቃዊ ጉዳዮችን የሚዳስሰው "የጣዕም ልኬት" የሬድዮ ፕሮግራም በቅርቡ ወደ አየር እንደሚመለስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የሬድዮ ፕሮግራሙ የሬድዮ ጣቢያውን ከሸገር 102.1 ወደ አንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ቀይሮ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 6:00 እስከ 8:00 ይተላለፋል ተብሏል።
"የጣዕም ልኬት" አዘጋጆች የሙዚቃ ባለሞያዎቹ ሰርፀ ፍሬስብሃት እና ምዕራፍ ተክሌ ናቸው።
የፕሮግራሙ አዘጋጅና የሙዚቃ ባለሞያው ሰርፀ ፍሬስብሃት ማኀበራዊ ትስስር ገፁ" ምንም ብንዘገይ፣ በመጨረሻ አድርገነዋል። ለበርካታ ዓመታት ከጆሯችሁ ርቃ የቆየችው "የጣዕም ልኬት" ተመልሳ ዐየር ላይ ልትውል ነው።በFM ዐዲስ 97.1 ሬዲዮ ሠርክ ቅዳሜ ከ6:00- 8:00።አዘጋጆች፥ ምዕራፍ ተክሌ እና ሠርፀ ፍሬስብሐ። "በሙዚቃዎቻችን የጣዕም መሠረቶች" ላይ ትኩረቷን ያደረገችው የጣዕም ልኬት ተመልሳለችበቅርብ ቀን" ብሏል።

📌በእረፍት ቀንዎ ቴአትር ይመለከቱ !
አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና የቦሌው ዓለም ሲኒማ ሐሙስ፣ አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እነዚህን ተውኔቶች ለታዳሚያን ያቀርባሉ።
📍 ጎዶ'ን ጥበቃ
ድርሰት: ሳሙኤል ቤኬት
ትርጉም: ሀይከል ሙባረክ
አዘጋጅ: ዳግም ሲሳይ
ቀን: ሐሙስ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 የፍቅር ካቴና
ድርሰትና ዝግጅት: አለልኝ መኳንት ፅጌ
ቀን: አርብ
ሰዓት: 12:00
ቦታ: ዓለም ሲኒማ
📍 "እሳት ወይ አበባ"
ድርሰት: ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እንደጻፈው
ዳንስና ዳንስ ቅንብር: ሽፈራው ታሪኩ ቢረጋ
ቀን: አርብ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባሎች እና ሚስቶች
ድርሰት: ውዱ አለን
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ባቡሩ
ድርሰት: አርኖልድ ሪድሊ
አዘጋጅ:ራሔል ተሾመ መሐመድ
ቀን: ቅዳሜ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 ሸምጋይ
ድርሰት:ታደለ አያሌው
አዘጋጅ: ሳሙኤል ተስፋዬ
ቀን: እሁድ
ሰዓት: 8:00
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
📍 እምዩ ብረቷ
ድርሰት: ቤልቶልት ብሬሽት
አዘጋጅ: ማንያዘዋል እንዳሻው
ቀን: እሁድ
ሰዓት:11:30
ቦታ: ብሔራዊ ቴአትር
የእናንተው ኤቨንት አዲስ ድረገፅ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ ይላል !

📌የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" መጽሐፍ በድምቀት ተመረቀ።
የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት ተመርቋል።
በዕለቱም ግጥሞና ወጎች ተነበዋል፣ ሥነጽሑፋዊ ዳሰሳዎችና የሙዚቃ ዝግጅት ቀርቧል።
ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ከዚህ ቀደም "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ መጻሕፍት አንባቢያን ማድረሱ አይዘነጋም።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የገጣሚ ዮሐንስ ሞላ "በከንፈርሽ በራ'ፍ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት ተመርቋል።
በዕለቱም ግጥሞና ወጎች ተነበዋል፣ ሥነጽሑፋዊ ዳሰሳዎችና የሙዚቃ ዝግጅት ቀርቧል።
ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ከዚህ ቀደም "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ መጻሕፍት አንባቢያን ማድረሱ አይዘነጋም።
ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ማህበር የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመቱን ሊያከብር ነው
ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ማህበር ሰላሰኛ አመት የምስረታ በዓሉን ለተከታታይ አስር ቀናቶች እንደሚያከብር አስታወቀ።
ከጥቅምት 25 አስከ ህዳር 5 2017 ዓ.ም ሠላሰኛ ዓመቱን በተለያዩ ዝግጅቶች የሚያከብረው ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ይህ ጊዜ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የምንከፍትበት ይሆናል ብሏል።
የማህበሩ ፕሬዚዳንት ምህረት ንጉሴ
በዓሉ የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት ፣ ለመብታቸው ለመሟገት እና አካታችነትን ለመፍጠር ምን ያህል እንደተጋን እንድንገመግም ያስችለናል ብለዋል።
በሶስት አሰርት ዓመታት ውስጥ በጤና ፣ በትምህርት፣በማህበራዊ ጥበቃ እድሎችን ከማሳደግ፣ዜጎችን በራስ በመደገፍ እና ድምፃቸው እንዲሰማ በማድረግ አመርቂ ውጤት ማምጣታችን ግን እሙን ነው " ብለዋል።
ስኬታችንን ስናከብር ብዙ የሚቀሩን ስራዎች እንዳሉብንም እንገነዘባለን ሲሉም ፕሬዚዳንቷ ተናግረዋል።
የ30ኛ ዓመት የምስረታ ክበረ በዓሉ ለሁሉም ጎብኝዎች ክፍት በሆነው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ/ም በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚዘጋጅ ኤግዚቢሽንና የመዝናኛ ፕሮግራም ተጀምሮ ህዳር 05 ቀን 2017ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ይጠናቀቃል፡፡

📌በሲኒማ ቤቶች የፊልም ስርቆት መከላከያ ሲስተምን ጨምሮ ከ140 በላይ ችግር ፈቺ የሆኑ ኘሮጀክቶችን ይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ኤስ አር ኢ ኢትዮጵያ አስታወቀ
ኤስ አር ኢ ኢትዮጵያን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የላቀ ለማድረግ ከ140 በላይ ችግር ፈቺ የሆኑ ኘሮጀክቶችን ይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገለጸ።
ከአስር አመት በፊት በሀገረ አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ የተመሠረተው ኤስ አር ኢ የተሰኘ መሠረቱን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና እውቀት ላይ አድርጎ የሰው ልጆችን ህይወት ለመቀየር በማሰብ የተመሰረተ ተቋም ሲሆን በቀጣይ አለምን በሳይንስ ቴክኖሎጂ ለመቀየር ዓላማን ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ የድርጅቱ መስራች አቶ ሳመኤል ከፈለኝ ገልጸዋል።
ተቋሙ ከሰራቸው አበይት የፈጠራ ስራዎች መካከል በሲኒማ ቤቶች የፊልም ስርቆት መከላከያ ሲስተም ፣ ከ250 በላይ ትምህርት ቤቶች ፣ ከ10 በላይ ኮሌጆች፣ ከአስራ ስድስት በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የአፍ ላይን ዲጂታል ላይብረሪ ማሽን ተጠቃሚ ከማድረጉም በላይ ለጎርፍ አደጋና ለመሬት መንቀጥቀጥ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ቴከኖሎጂ፣ የግለሰቦችን ማንነት እራሱ ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ሰው ሰራሽ አስተውሎት ( አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ) ቴከኖሎጂ እንዲሁም ከ15 በላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማበርከቱን ተቋሙ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።
ተቋሙ ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የቴክኖሎጂ ምርቶችን ሀገር ውስጥ በማምረት ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር በኩል ጉልህ ድርሻ ያበረከተ ሲሆን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚታገዝና የሚመራ የትራፊክ መብራቶችን ፣ ባዩሜትሪክ ፣ ለቱሪስቶች መረጃ የሚሰጥ የመረጃ ማዕከል ጨምሮ በርካታ የፈጠራ ስራዎችን ሰርቷል።

📌ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ የ2024 የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት ( AFAA ) ተሸላሚ ሆነ
ላለፉት 25 ዓመታት ከፋሽን ሰዎች ታዋቂዎችን እነ ቺኒዋ አቼቤ፣ አለን ፔተን፣ የሚ አላዴ፣ ብሬንዳ ፋሴ እና ከሰዓሊያን እነ ቼሪ ሳምባ፣ አብዱላሂ ኮንቴ እና ኢብራሂም አል ሳላሂ በተለያዩ ዓመታት የሸለመው የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት ( AFRICAN FASHION & ART AWARD -AFAA ) ዘንድሮው ከሚሸልማቸው 100 አፍሪካዊያን የፋሽን እና የሥነ-ጥበብ ሰዎች ውስጥ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ ኾኗል።
ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ ለሽልማቱ ቀጥታ ተመራጭ እንዲሆን ያበቃው፤ በአፍሪካ ስልጣኔ፣ ባህል እና ፓን አፍሪካኒዝም እንዲሁም በኢትዮጵያ ስልጣኔ ፣ ባህል እና ማንነት ላይ በሠራቸው የስዕል ሥራዎች እና በተለያዩ ዓለማት በተሳተፈባቸው ዐውደ ርዕዮች ባገኛቸው እውቅናና ሽልማቶች ነው።
ሠዓሊ እና የታሪክ ባለሙያ ወንድወሰን፤ በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፂያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ ፤ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሥነ-ጥበብ አማካሪ፣ በኢቲ - ሜትሮፖሊታን ጋለሪ ዳይሬክተር እና ኩሬተር፣ የሀገር አማን እና ሆርን ሪቪው መጽሔቶች ካርቱኒስት እና አምደኛ፣ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሕክምና ማኅበር አምባሳደር በመሆን እያገለገለ ይገኛል።
የዘንድሮውን የአፍሪካዊያን የፋሽን እና የሥነ-ጥበብ ሽልማት ከNovember 6th - 8th /2024 በዋና ጽሕፈት ቤቱ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያካሂድ አፋ (AFAA) ባወጣው መግለጫ አሳውቋል ።