Event Addis Media – Telegram
Event Addis Media
9.62K subscribers
6.11K photos
13 videos
4 files
4.73K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
📌"ነገረ መጻሕፍት" ቅዳሜ ይካሄዳል።

በዛጎል የመጻህፍት ባንክ የሚዘጋጀው "ነገረ መጻሕፍት" የመጻህፍት ውይይት የቦታ ለወጥ አድርጎ ነገ ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ምኒልክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው "FSS" አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ መሰናዶ ላይ ዶክተር ዳዊት አሰፋ እና ዶክተር ዮናስ ባህረጥበብ ተጋባዥ እንግዶች ሲሆኑ ለውይይት የሚቀርቡ መጻሕፍት ደግሞ "የሁሉ" እና "ኦቲዝምና አንዳንድ ከያንያን ስለሚያጠቃቸው የአዕምሮ ሕመም" ናቸው።የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው።

ለተጨማሪው:Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Telegram: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አውደ ፋጎስ" የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል

50ኛው ዙር አውደ ፋጎስ የውይይት መድረክ እሁድ ይካሄዳል። በዚህኛው ዙር ተመስገን ዋና " ሳይንስ እና ኃይማኖት:በተዋሥኦ መካከል" በሚል ርዕስ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል።

ይህም ውይይት እሁድ ህዳር 15 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አግልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው:Tiktok:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rbUqppyscx&_r=1

Telegram: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል።

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት "እነሆ ማሟሻ" ቅጽ አንድ እና ቅጽ ሁለት መጻሕፍት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነገ ቅዳሜ ሕዳር 14 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው በኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ስቱዲዮ ሁለት(በተለምዶው ሴጣን ቤት) አዳራሽ ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ሥነሥርዓት ላይም አንጋፋ እና ወጣት የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከወራት በፊት ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

Telegram: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌 የሮፍናን ኮንሰርት በአዳማ  ተሰርዘ

ሁለገቡ ሙዚቀኛ ሮፍናን ኑሪ በአዳማ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ቅዳሜ ህዳር  14 2017 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ ይዞለት የነበረው "የኔ ትውልድ" ኮንሰርት ሙሉበሙሉ እንደተሰርዘ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

እነሆ ዝርዝር መረጃዎን በድምጻችን ይስሙ:
https://vm.tiktok.com/ZMh7w27h3/

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የዕድገት ጉዟችን በዘመናት መካከል"

የዕድገት ጉዟችንን በዘመናት መሐል የሚቃኝ ፓናል ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 14 2017  ዓ.ም ይደረጋል፡፡

በብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና  ቤተ-መጽሀፍት  አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ በሚደረገው በዚህ መርሐግብር ታላላቅ ሰዎች ይታደማሉ፡፡

የታሪክ አደራ ድርጅት ባዘጋጀው በዚህ የአርካይቭ ማዕከል ምረቃ ስነስርአት ላይ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ- መንግስት የተመዘገቡ እድገቶችና ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች በውይይት አቅራቢዎች ይዳሰሳሉ፡፡

በፓናሉ ላይ ንግግር ከሚያደርጉት መካከል በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ከፕላን እና በጀት ጋር ከፍተኛ ኃላፊነት የነበራቸው አቶ በቀለ እንደሻው እና አቶ ተድላ ተሾመ ይገኙበታል፡፡

የታሪክ አደራ ድርጅት  የአርካይቭ ማዕከሉን በሚያስመርቅበት ዕለት  የድርጅቱ መሥራቾች እንዲሁም ደጋፊዎች የሚታደሙ ሲሆን  በዕለቱም በፊልም ባለሙያው የማነ ደምሴ የተዘጋጀ 20 ደቂቃ የጊዜ ፍጆታ ያለው ዘጋቢ ፊልምም ይቀርባል፡፡

የታሪክ አደራ ድርጅት በ2014 የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን  የተለያዩ መታሰቢያዎችን  የማቋቋምና የማስተዳደር ብሎም የማሻሻል ሥራዎችን የሚሠራ ነው፡፡ በተጨማሪም ታሪክ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ጠቃሚ ተግባራትን የሚያከናውን ሲሆን  ነጻ የትምህርት እድሎችንም  ይሰጣል፡፡

የዚህ መርሀ ግብር ሁነት አዘጋጅ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ሲሆን መድረኩን በመምራት ደግሞ ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ  ድርሻውን እንደሚወጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የሕይወት ተፈራ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ለንባብ ይበቃል

የደራሲ ሕይወት ተፈራ "ተድባብ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ቅዳሜ ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደሚደረስ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከዋልያ መጻሕፍት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የመጽሐፉ አሳታሚና አከፋፋይ ዋልያ መጻሕፍት እንደሆነ ተገልጿል።

ሕይወት ተፈራ ከዚህ ቀደም "ማማ በሰማይ" "ምንትዋብ" እና "ኅሠሣ" የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማቅረቧ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
የጋዜጠኛ የኑስ መሐመድ መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የጋዜጠኛ የኑስ መሐመድ "የነፍስያ ድምጾች" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።

በዚህ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ አንጋፋ እና ወጣት የሥነጽሑፍ ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የፍቅር ካቴና" ተውኔት በልዩ ዝግጅት ነገ ይቀርባል

ድርሰት እና ዝግጅቱ የአለልኝ መኳንት ፅጌ የሆነው "የፍቅር ካቴና" ተውኔት ነገ እሁድ ህዳር 15 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት ጀምሮ በልዩ ዝግጅት በዓለም ሲኒማ ይታያል።

በተውኔቱ ላይ ድርብወርቅ ሰይፉ፣ ሚኪ ተስፋዬ ፣ወይንሸት አበጀ፣ አሸናፊ ማህሌት ይተውኑበታል።

የቴአትር ወዳጆች ዓለም ሲኒማ መጥታችሁ  የእረፍት ቀናችሁን በፍቅር ካቴና ቲያትር እየተዝናናችሁ ጥሩ ጊዜን እንድታሳልፉ ተጋብዛችኋል ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በአሜሪካ ኤምባሲ

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በፕሪስቴጅ አዲስ ዝግጅት ላይ እንግዳ በመሆን ይቀርባል።

የተለያዩ የጥበብ ባለሞያዎችን እየጋበዝ ልምዶቻቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ያለው ፕሪስቴጅ አዲስ መርሐግብር በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ፕሮግራሙ በተወዳጅ የፍቅር ዘፈኖቹ የሚታወቀውን ስመ-ጥር እና በአዲሱ የሙዚቃ አልበሙ ደግሞ ተወዳጅነትን ያተረፈውን ድምፃዊ የግጥም እና ዜማ ደራሲ አርቲስት ሚካኤል በላይነህን ጋብዟል::

የፕሪስቴጅ አዲስ አዘጋጆች "ከሚኪ ጋራ በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ ማክሰኞ ሕዳር 17 2017 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ገለጸዋል።

በዕለቱ ከአርቲስቱ ጋር የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃግብር ይኖራል ተብሏል::

ፕሪስቴጅ አዲስ ከሚካኤል በላይነህ ጋር  የሚያደረገው አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ነገ ማክሰኞ ሕዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ( ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ ) ይካሄዳል።

በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ:https://bit.ly/SatchmoCenterMembership

መታወቂያ መያዝ እንዳይረሳ፣ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ያደርጋል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩም ተብላችኋል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ይህ "Event Addis Media" ነው 💥

የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይወዳጁ+ያጋሩ!

ቴሌግራም:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1

ቲክቶክ:https://www.tiktok.com/@eventaddis1?_t=8rgsgcVSeW7&_r=1

Website:https://eventaddis.com/

Facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851

አስተያየትዎን ይጻፉልን: @Tmanaye
📌"መንግሥቱ ኃይለማርያም:የስደተኛው መሪ ትረካዎች"መጽሐፍ ሁለተኛ እትም ለንባብ በቃ

በደራሲ ይታገሱ ጌትነት የተዘጋጀው "መንግሥቱ ኃይለማርያም:የስደተኛው መሪ ትረካዎች"መጽሐፍ ሁለተኛ ህትመት ለንባብ በቅቷል።

የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያው እትም በሀገር ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሽጦ ከገበያ ጠፍቶ ነበር። ዳግም ህትመቱ ከዛሬ አንስቶ በዋልያ አሳታሚ አማካኝነት በሁሉም የመጽሐፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል።

በውጭ ሀገር መጽሐፉን ለማግኘት አማዞን ላይ በ https://a.co/d/6V7LBpt መጠቀም ይችላሉ።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

የጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ "ጠይም ጤዛ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 10:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ይመረቃል ተብሏል።በዕለቱም አንጋፋው እና ወጣት የሥነጽሑፍ ባለሞያዎች ሀሳቦቻቸውን እንደሚያገሩ ተገልጿል።

"ጠይም ጤዛ" መጽሐፍ ሐምሳ የግጥም ስራዎችን በውስጥ የያዘ ሲሆን 94 ገፆች ተቀንብቦ በ300 የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።ጋዜጠኛና ገጣሚ ተሾመ ብርሃኑ ከዚህ ቀደም በ2011 ዓ.ም በሆሄ የሥነጽሑፍ ሽልማት ላይ የዓመቱ ምርጥ የግጥም መደብል አሸናፊ የሆነበት "ኮብላይ ዘመን" መጽሐፍን ለአንባቢያን አድርሷል።

በተጨማሪም በጀርመን ባህል ማዕከል (ጎተ)አወዳዳሪነት ከተለያዩ ደራሲዎች ጋር በጋራ በተሰናዳው "ሠላሳዎቹ" የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ውስጥም ስራው ታትሞለታል።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"አሚን አሚንዬ" መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል

የገጣሚ መሐመድ እድሪስ ካሣ"አሚን አሚንዬ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የግጥም መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ይካሄዳል።

በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ላይ ሀሴን ከድር ፣ቴዎድሮስ ካሣ፣ረድኤት አሰፋ፣እሱባለው አበራ፣ሚካኤል ምናሴ፣መስፍን ወንድወሰን ፣ዮሴፍ ይድነቃቸው ፣ያስሚን ሰፋ፣ፈይሰል አሚን፣ሐብታሙ ሀደራ የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

ሙኒራ አብዱራህማን መድረኩን ትመራዋለች።

ለተጨማሪው:https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"መሀል ከተማ" ዛሬ ለእይታ ይበቃል

በኤርሚያስ ታደሰ የተዘጋጀውና "መሀል ከተማ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የአማርኛ ፊልም ዛሬ ሕዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ይበቃል።

ይህ ፊልም ሕዳር 20፣ 21፣ 22 በይፋ ይመረቃልም ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ደራሲና ተዋናይ ደሞዝ ጎሽሜ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም የሀሳብ ውይይት ዝግጅት እሁድ ይካሄዳል።

ደራሲና ተዋናይ ደሞዝ ጎሽሜ የክብር እንግዳ የሆነበት ስብሐቲዝም 79ተኛ መድረክ "ኢትዮጵያዊ ጥበብ" በሚል የሀሳብ ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ እሁድ ሕዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም  ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍጻሜ ውድድር

የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍጻሜ ውድድር ነገ እሁድ ህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ስድስት ኪሎ በሚገኘው ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ፕ/ር አሸናፊ ከበደ የሙዚቃ ማዕከል ውስጥ ይካሄዳል።

የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ አይዶል ዝነኞች ከአዳዲሶቹ ምርጦች ጋር እሁድ በዓመቱ ኮከብ ልዩ ፕሮግራም ላይ ይገናኛሉ ተብሏል።

ዳግማዊት ፀሀዬ፣ ዳዊት አለማየሁ፣ ተመስገን ታፈሰ፣ አዝመራው ሙሉሠውና ሌሎች የአይዶል ፈርጦች አዳዲሶቹን ኮከቦች ያገኟቸዋል።

እሁድ ህዳር 22 በሚካሄደው የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ ኘሮግራም ላይ አርቲስቶቹ ልዩ ቆይታ ይኖራቸዋል።

1 ሚሊየን ብር በሚያሸልመው የዓመቱ የፍፃሜ ውድድር በሙዚቃ ድግስ ደምቆ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሁሉም ቻናሎች በመላው ዓለም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በቀጥታ ይተላለፋል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የ"ቅኔ ሰርከስ"የሰርከስ ድግስ ዛሬ ይካሄዳል

የቅኔ ሰርከስ የሰርከስ ደግስ ልዩ ዝግጅት ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ጎሮ አካባቢ በሚገኘው በቅኔ ሰርከስ ማዕከል ይካሄዳል።

ይህ የሰርከስ ዝግጅት መግቢያው ለአዋቂ 400 ብር ሲሆን ለህፃናት 200 ብር እንደሆነም ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ ሆኗል

የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ በመሆን ልዩ ዋንጫ፣ አንድ ሚሊዮን ብር እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ነፃ የትምህርት እድል አሸናፊ ሆኗል።

2ኛ ሚኪያስ ጌቱ

3ኛ ማቲያስ አንበርብር

4ኛ ብዙአየሁ ሰለሞን

ውጤቱ የ2 ዙር የዳኞች ውጤት እና ተመልካቾች በ8600 በፅሁፍ መልእክት የሰጡት ድምፅ ተደምሮ ነው አሸናፊው የተለየው ።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌"የዱር አበባ" መጽሐፍ ቅዳሜ ይመረቃል

የገጣሚ ቴዎድሮስ ካሣ "የዱር አበባ" የተሰኘ አዲስ የግጥም መፅሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 28 ከቀኑ 11:00 ጀምሮ መገናኛ(24) በሚገኘው ሞሰብ የሙዚቃ ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ በድምቀት ይመረቃል ።

በዕለቱም በዝግጅቱ ላይ ረድኤት ተረፈ፣ግሩም ተበጀ፣አልዳ ግዛቸው ፣ሰለሃዲን አሊ፣ምግባር ሲራጅ፣ፍቃዱ አየለኝ፣ሰይፉ ወርቁ ፣መዘክር ግርማ፣አንተነህ አክሊሉ፣አንዱ ጌታቸው፣እልፋገድ እምሻው ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ተወዳጇ አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ በሲትኮም ድራማ እየመጣች ነው

በተለያዩ የቴሌቪዥንና ሬድዮ ድራማዎች እንዲሁም ፊልሞችና ተውኔቶች ላይ የምናውቃትና ከቴሌቪዥን ድራማዎች ጠፍታ የቆየችው አንጋፋው አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ በአዲስ የቴሌቪዥን ሲትኮም ድራማ እየመጣች እንደሆነ ተሰምቷል።

አርቲስት ሙሉዓለም ታደሰ የምትሳተፍበት ሲትኮም ድራማ "ዞሮ መውጫዬ"የተሰኘ ርዕስ ያለው እንደሆነም ተገልጿል።

ይህ ሲትኮም ድራማ አርቲስት ሙሉዓለም ታደስ እና አርቲስት ሚካኤል ታምሬ የተጣምሩበት እንደሆነም ተነግሯል። ድራማው በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንደሚተላለፍም ተሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1
📌ለሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ህክምና የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ የአንድ ቀን አውደርዕይና ጨረታ ተዘጋጀ

የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "ነፃነት" የተሰኘና ለአንድ ቀን  ብቻ የሚቆየ የሥዕል አውደርዕይና ጨረታ የፊታችን ህዳር 26 ቀን 2017 ይካሄዳል ተብሏል።

ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ በቅርቡ በስዊድን ለሚያደርገው ህክምና ወጪን ለመሸፈን ነጻነት የተሰኘ የስዕል ኤግዚብሽን ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

በመጪው ሃሙስ ሕዳር 26 ቀን በሸራተን አዲስ ሆቴል ውስጥ በሚካሄደው የሥዕል አውደርዕይና የሥዕል ጨረታ ፕሮግራም የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የጥበብ ሰዎችና ሠአሊዎች ይገኛሉ ተብሏል።

ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ እንደገለፀው ከዚህ የሥዕል አውደርዕይና የሥዕል ጨረታ ፕሮግራም የሚገኘው ገቢ በቅርቡ ስዊድን ሀገር ለሚያደርገው የእግር ህክምና ወጪው 3 ሚልየን ብር እንደሆነ ተናግሯል።

ለተጨማሪው: https://news.1rj.ru/str/EventAddis1