TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.11K subscribers
910 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።

ከ25 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡

ተመራቂዎቹ በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃ እና የስፔሻሊቲ ፕሮግራም ሰልጣኞች ናቸው፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ!

ምስል፦ መቀሌ፣ጅማ፣ ባህርዳር፣ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲዎች

@TEMARI_Net1
በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።

ከ25 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡

ተመራቂዎቹ በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃ እና የስፔሻሊቲ ፕሮግራም ሰልጣኞች ናቸው፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ!

ምስል፦ መቀሌ፣ጅማ፣ ባህርዳር፣ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲዎች

@TEMARI_Net1
2
መንትዮች ተመራቂዎች 🎉

ዮሐንስ ደረጀ እና ያዕቆብ ደረጀ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሶፍትዌር ምህንድስና ዛሬ ተመርቀዋል።

መንትዮቹ ከልጅነታቸው ጀምረው በአንድ ክፍል ፊደል ቆጥረው፣ በአንድ ሁለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረው በጅማ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በተመሳሳይ ውጤት እና ደረጃ ለማጠናቀቅ ችለዋል። #JiT

#tikvahuniversity
3
Fully Funded Leadership Conference in the USA 2025

Conference Dates: Oct. 30 - Nov. 2, 2025

Location: Harvard Kennedy School

Link: https://scholarshipscorner.website/harvrd-public-policy-leadership-conference/

Benefits: All expenses are covered by Harvard Kennedy School — including travel, accommodation, and meals during the conference.

Deadline: 7 July, 2025.

Credit: The President and Fellows of Harvard College. Harvard Kennedy School
The content is based on and adapted from information available on the official website. Details are subject to change. For any credit or content inquiries, please contact us

@TEMARI_Net1
ይህ ተመራቂ ለእናቱ ያለውን ፍቅርለመግለፅ የሞከረበት ምስል ነው።እናት ከሰል ሽጣ ልጇን አስተምራ ዛሬ አስመረቀች። እሱም በምርቃት ቦታው በጓደኞቹ ፊት አመሠግንሻለሁ ብሎ ክሰል ራሱ ላይ አድርጎ ፍቅሩን መግለፁ ከምስሉ ጋር የወጣው ሃሳብ ያስረዳል።።


@TEMARI_NET1
7
#DillaUniversity
#ClassOf2025
#CommencementPhotos

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት ማለፋቸውን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1,576 ተማሪዎች አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ ሁለት ተማሪዎች በሦስተኛ ዲግሪ እና 100 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።

በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ምሩቅ የሆነው ዳንኤል ግርማ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.96 በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

#tikvahuniversity
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የፈተና አገልግሎት ክፍያ (Exam Service Payment) የከፈሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤት ዛሬ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የተለቀቀ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጠናል።

በዚህም የፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈሉ ተቋማት የተፈታኞቻቸውን ውጤት እንዲያውቁት የተደረገ ሲሆን፤ የግል ተፈታኞች ወደ ተማሩበት ተቋም በመሔድ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል። 

#tikvahuniversity

@TEMARI_Net1
42 A+ ያመጣው ተመራቂ

ደሲ መሀመድ ይባላል። በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

ቤተሰቦቹ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቢሆንም የሚችሉትን ያህል ደግፈውታል። ወደ ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላ ጎን ከትምህርቱ ጎን ለጎን ልጆችን በማስጠናት በሚያገኘው ገቢ ራሱን ደጉሟል። ከሚያስጠናቸው ልጆች ቤተሰብ ጋርም የጠበቀ ወዳጅነት መፍጠሩን ተናግሯል።

ደሲ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.94 ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም የማዕረግ ተመራቂ ሆኗል።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 596 ተማሪዎች አስመርቋል።

#tikvahuniversity
1