Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጡት ካንሰር ሞትን ለመቀነስ ምዕናባዊው ሆስፒታል ወደ ትግበራ እየገባ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ )
የጡት ካንሰር ሞትን ለመቀነስ እንደሚያስችል የታመነበት ምዕናባዊው ሆስፒታል ወደ ትግበራ እየገባ ነው ሲል የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ:: የምናባዊ ሆስፒታሉ ህክምና በጡት ካንሰር የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር ይቀንሰዋል ተብሏል::
ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ቆይታ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99647
ከአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የወጪ ንግድ 514 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የወጪ ንግድ 514 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከሚኒስቴሩ በተገኘው የዘጠኝ ወር ሪፖርት መሰረት፤ በ2015 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 381 ሺህ 543 ነጥብ 43 ቶን የሆርቲካልቸር ምርቶችን ወደውጭ ሀገራት በመላክ 549 ነጥብ 46 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99633
መልካም ዕድል ለሥራ ፈላጊዎች🙏
አፍሪካ ህብረት የተመሰረተበትን 60ኛ አመት ምክንያት በማድረግ ኤክስፖ ሊዘጋጅ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሜጋ ሰፕሊ ኢንጂነሪንግ ጋር በመተባበር አፍሪካ ህብረት የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ “አንድ አፍሪካ ኤክስፖ” በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 17 እስከ 19 በሳይንስ ሙዚየም ኤክስፖ ሊያዘጋጅ ነው።
ኤክስፖውን አስመልክቶ ጋዜጣው መግለጫ የሰጡት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር አብዱ ያሲን እንደገለጹት፣ በነጮች ግንቦት 25 አፍሪካ ክብረት የተመሰረተበትን 60ኛ አመት ያከብራል። በኤክስፖው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ይበልጥ ታጸናለች ብለዋል።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከ60 አመት በፊት ሲመሰረት ዋና አላማው አፓርታይድን ማስወጣት ነው ያሉት አምባሳደሩ፣ ስሙን ወደ አፍሪካ ህብረት ከለወጠ ወዲህ ደግሞ አፍሪካውያን በኢኮኖሚ ጠንካራ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል። አፍሪካውያን እርስ በርስ በንግድና በገበያ እንዲተሳሰሩ በፖሊሲ የተደገፍ ስራ እየተሰራ ነው። የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ ተግባራዊ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጠንክራ እየሰራች ነው።
በኤክስፓውን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ዲፕሎማሲዋን የምታጠናክርበት ይሆናል ብለዋል።
የአንድ አፍሪካ ኤክስፖ አዘጋጅ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል መብራቱ በበኩላቸው፣ የሚዘጋጀው ኤክስፖ የአፍሪካን የ60 አመት ጉዞ የሚገመግም ነው። አፍሪካ ነጻ ከወጣች በኋላ በአለም መድረክ ያላትን ተቀባይነትና አፍሪካውያን ያላቸውን የባህል፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነትም እንዲጠንክር ያደርጋል ሲሉ ገልጸዋል።
የሚዘጋጀው ኤክስፖ አዲስ አበባ የፖለቲካ ዲፕሎማ ማእከልነቷን እንድታጸና ያግዛል ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው፣ ኤክስፖው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ፣ አፍሪካ ከአለም ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያጠናክራል። የተጀመረውን ነጻ የንግድ ቀጠናን ያጠናክራል ብለዋል።
በሞገስ ጸጋዬ
አቶ ጥራቱ በየነ የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽንና የአርሶአደርና የከተማ ግብርና ውጤትን ጉበኙ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ከቤተ ሙከራ እስከ አዝመራ" በሚል መሪ ሀሳብ ለህዝብ ይፋ ሆኖ የተከፈተውን የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽንና "ምግባችን ከደጃችን" በሚል መሪ ቃል በከተማ ደረጃ የተጀመረውን የአርሶአደርና የከተማ ግብርና ውጤት ዛሬ ጎብኝተዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት፣ የተፈጥሮ ሀብትን በመጠቀም ዜጐችን በአግባቡ ወደ ስራ በማስገባት መበልጸግ እንደሚቻል በኤግዚቢሽኑ ላይ የታዩ ውጤቶች ማሳያ ናቸው።
ከ2014 አ.ም በወረዳዎችና ክፍለከተሞች በንቅናቄ መልክ መተግበር የጀመረው " ምግባችን ከዳጃችን" የከተማ ግብርና በርካቶችን ተጠቃሚ ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።
የከተማ ግብርና የዜጐችን ኑሮ በማሻሻልና የስራ እድልን በመፍጠር ተጨባጭ ውጤት እያሳየ እንዳለም ጥቅሰዋል።
የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው፣ ግብርና የአገሪቱ የጀርባ አጥንት መሆኑንና ከእጅ ወደ አፍ የነበረው የግብርና ስራ በአሁን ወቅት ወደ ዘመናዊነት በመሸጋገር የከተማ ዜጐችን ጭምር ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በግብርና ሚኒስቴር አዘጋጅነት "ከቤተ ሙከራ እስከ አዝመራ" በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም ይፋ የሆነው የግብርና ሳይንስ ኤግዚቢሽን ከሳምንት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መከፈቱ ይታወሳል።
በአሁን ወቅትም ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ዜጐች እየጐበኙ ይገኛሉ።
በአዲሱ ገረመው
መልካም ዕ ድል🙏