Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የቀደምት አፍሪካውያን መሪዎችን ራዕይ እውን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆን ይገባል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ ህብረትን 60ኛ ዓመት ስናከብር ቀደምት የአፍሪካ መሪዎች ጠንካራና አንድነቷ የተጠበቀ አህጉር ለመፍጠር የነበራቸውን ራዕይ እውን ለማድረግ መትጋት እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው የአፍሪካ ህብረት የተመሠረተበትን 60ኛ ዓመት በማስመልከት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት፤ ቀደምት የአፍሪካ ....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02zJkGnvJKHtLLFTFZXiSBfEgNu8N8d8yxgfrWwqri5Lwju1ZpyYqYtWvJ8neQdiKfl
የጊቤ 1 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ9 ወራት ውስጥ ከሰባት መቶ ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል አመንጭቷል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጊቤ 1 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ውስጥ 701 ነጥብ 6 ጊጋ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ ማመንጨቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡
ሥራ አስኪያጁ አቶ ደሳለኝ ንጉሴ እንደገለፁት ማመንጫ ጣቢያው በዘጠኝ ወራት ውስጥ ለማመንጨት ካቀደው....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid02K5u9Y7XjWruPG38bLd4c9qnTNiq59bJCwPm8sutmaRw6F2XEJKawGLrHoK7PcvcAl
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
በዴንቨር በነበረን ቆይታ በጋራ ለመስራት የለየናቸው ዘርፎች ወደ ተግባር በሚለወጡባቸው መንገዶች ዙሪያ ከከንቲባ ማይክል ሃንኮክ፣ ከከተማው አመራሮች እና የንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
ለዴንቨር ከተማ የንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎችና አባላት ስለ ከተማችን ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገንላቸዎል። ኃላፊዎቹ አዲስ አበባን ውብ ለማድረግ የጀመርናቸውን ስራዎችን አድንቀው ለከተማ እድገት የግሉን ዘርፍ ከመንግስት ጋር በቅንጅት መስራት ስላለው ትልቅ ፋይዳ ልምዳቸዉን አካፍለውናል።
በከተማችን አዲስ አበባ ብዛት ያለው የተማረ ወጣት እንደመኖሩ በዴንቨር ያሉ ተቋማትን በማስተባበር ለወጣቱ የስራ እድል የሚፈጥሩ አገልግሎቶቻቸውን ወደ አዲስ አበባ ማምጣትና ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም በተለዩ ዘርፎች ላይ በቅርበት መስራት ለሁለቱም ከተሞች በሚያስገኘው ፋይዳ ዙሪያ በዝርዝር ተወያይተናል።
በዴንቨር ከተማ ከአቀባበል ጀምሮ ለቆይታችን ስኬታማነት፣ በተለይም ለተደረገልን ልዩ መስተንግዶ ሁሉ ከንቲባ ሃንኮክን እና ባልደረቦቻቸውን በድጋሚ ላመሰግን እወዳለሁ።
ጤፍን በዘመናዊ መንገድ በመዝራት ብክነትን የሚከላከል ቴክኖሎጂ እየለማ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ )
ጤፍን በማሽን በመዝራት በአበባ ወቅት የሚከሰተውን የምርት ብክነት ለመከላከል የሚያስችል ቴክኖሎጂ እየለማ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በግብርና ሚኒስቴር የአግሮኖሚስት ባለሙያው አቶ ምትኩ በጅጋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እንደ አገር ጤፍ በባህላዊ መንገድ ሲዘራ በአበባ ወቅት መሬት ላይ ወድቆ የሚበሰብስበት ሁኔታ ይስተዋላል። የጤፍ ሰብል መሬት ላይ የሚወድቀው ዋናው ምክንያት የዘር መጠኑ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ነው። በመሆኑም ይህንን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100393
«ኢትዮጵያ ለሱዳን ሰላምና መረጋጋት አዎንታዊ ሚና የምትጫወት አገር ናት»
- ዶክተር ወሂበእግዜር ፈረደ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ለሱዳን ሰላምና መረጋጋት አዎንታዊ ሚና የምትጫወት አገር ናት ሲሉ የስትራቴጂክ ጉዳይ ተመራማሪው ዶክተር ወሂበእግዜር ፈረደ ገለጹ።
የስትራቴጂክ ጉዳዮች ተመራማሪው ለኢፕድ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሠላምና መረጋጋት ወሳኝ አገር መሆኗ በግልጽ የሚታወቅ ነው። ኢትዮጵያ ለሱዳንም መረጋጋት አዎንታዊ ሚና የምትጫወት አገር ናት። በሱዳን ያለው ቀውስም በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ኢትዮጵያ ጥሪ ማቅረቧ ይታወቃል።
በሱዳን ያለውን አሁናዊ ሁኔታ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100362
ሚኒስቴሩ ለመጽሐፍት ተደራሽነት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራ ምክርቤቱ አሳሰበ
***************
(ኢ ፕ ድ)
የሥርዓተ ትምህርት የለውጥ ትግበራ እና የትምህርት ቤቶች ደረጃ እና ጥራት ማሻሻል ለትምህርት ጥራት አስፈላጊ ጉዳዮች መሆናቸውን በመገንዘብ ትምህርት ሚኒስቴር በቀጣይ ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ ሊተገብራቸው እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ።
ምክር ቤቱ የትምህርት ሚኒስቴርን የ2015 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ትናንት ባካሄደበት ወቅት የሰው ሀብት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶክተር)፤
ለትምህርት ዘርፉ ችግር በተግባር የሚገለጹ በርካታ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100354
የጭነት ተሽከርካሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ በባቡር ተጓጉዘው እንዶዴ ባቡር ጣቢያ ደርሰዋል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ በባቡር ተጓጉዘው እንዶዴ ባቡር ጣቢያ መድረሳቸውን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አሰታወቀ።
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር በጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ ....https://www.facebook.com/ethiopianpressagency/posts/pfbid0ud2squRCwXz1UfREaEwRQitEjaf2oZt45noT7JkDakSrjwgUDS3MWGAqza1QnnJGl