Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መልዕክት‼️
የዚህ ዓመት የበጋ ስንዴ ምርታማነት በጥሩ ሂደት ላይ ይገኛል።
👉“በአፈር ማዳበሪያ እጥረት ምክንያት መሬታችን ፆም እንዳያድር እየሰጋን ነው” -የአማራ ክልል አርሶ አደሮች
👉“በክልሉ የተከሰተውን የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት ለመቅረፍ እየሰራን ነው” -የክልሉ ግብርና ቢሮ
************************
(ኢ ፕ ድ)
በአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት ምክንያት ቀድመው መዘራት ያለባቸው ምርቶችን መዝራት ባለመቻላችን መሬታችን ፆም እንዳያድር ከፍተኛ ስጋት ገብቶናል ሲሉ የአማራ ክልል አርሶ አደሮች ገለጹ።
የክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ የተከሰተውን የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት ለመቅረፍ እየሰራሁ ነው ብሏል።
በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደምበጫ ወረዳ አርሶ አደር አቶ ገደፍ ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በደምበጫ ወረዳ የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት በመኖሩ ምክንያት ቀድመው የሚዘሩ ምርቶችን መዝራት አልቻልንም፤ በመሆኑም መሬታችን ፆም እያደረ ነው ብለዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100567
ፎቶ ከፋይል
ምክረ ሃሳቦቹ ለሀገር ኢኮኖሚ ማንሰራራት ትልቅ ሚና አላቸው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት የሚያቀርባቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክርና ሀሳቦች ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ግብአት በመሆን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ምክር ቤት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ‹የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክር ጥበብና ሳይንስ› በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው አውደ ጥናት ተካሂዷል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዶክተር ፍጹም አሰፋ እንደገለጹት፤ ይህ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100534
የግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ፣ መልካም ዕድል‼️
የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ከህወሃት ታጣቂ ሀይሎች የቡድን መሳሪያዎችን ተረከበ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሕወሓት ታጣቂ ኃይሎች በፕሬቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ዛሬ መቀለ አቅራቢያ በሚገኘው ላጪ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የቡድን መሳሪያዎችን ለመከላከያ ሰራዊት ተወካዮች ዛሬ አስረክበዋል።
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች በእጃቸው የነበረ የቡድን መሳሪያ ማለትም ዲሽቃ፣ አርፒጂ፣ መትረየስና ሞርታር የተባሉ የጦር መሳርያዎችን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል።
በርክክቡ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተወካይ ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ እንዳሉት፤ ርክክብቡ የሰላም ስምምነቱ አንዱ አካል ነው።
የህወሓት ታጣቂ ሀይሎች ተወካይ ብርጋዲየር ጀነራል ምግበይ ሃይለ በበኩላቸው ርክክቡ በሰላም ስምምነት መሰረት መሰረት መፈጸሙን ተናግረዋል። ሰላም የመጀመሪያና የመጨረሻ ግባችን ነውም ብለዋል።
ርክክቡ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ስምምነቱ ክትትል፣ ቁጥጥር እና ማረጋገጥ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ተከናውነናል።
ከቡድን መሳሪያዎቹ ርክክብ በኋላ መግለጫ የሰጡት በአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ እና አረካካቢ ኮሚቴ አባል ብርጋዴር ጀነራል ቴፎ ሰኮሌ የርክክብ ሂደቱ የሰላም ስምምነቱ በጥሩ መልኩ እየሄደ መሆኑን አንዱ ማሳያ ብለዋል።
በጌትነት ምህረቴ
#ከኢፕድ_ማህደር

ሁለት ጠርሙስ አረቄ የሰረቀው 2 ዓመት እስራት ተፈረደበት

ሊጠጣ ገብቶ ጠርሙስ አረቄ የሰረቀው መላኩ ምህረቴ በ2 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡

በሌብነት ወንጀል ተከሶ ስምንት ጊዜ የተቀጣው መላኩ ምህረቴ ዘጠነኛውን የስርቆት ወንጀል ሲፈጽም የተያዘው በደሴ ከተማ ባለፈው ሐምሌ 27 ቀን 1962 ዓ.ም ነው፡፡

ተከሳሹ በዚሁ ቀን እመት የሺ ነዋይ ከተባሉት ሴት መጠጥ ቤት ገብቶ ሁለት ጠርሙስ አረቄ ስረቆ መውሰዱን እራሱም ከማመኑም በላይ በማስረጃም ተረጋግጦበታል፡፡

በዚህ አድራጎቱ ተከሶ በ2 ዓመት እስራት እንዲቀጣ የደሴ ዙሪያ አውራጃ ፈርድ ቤት በዋለው ችሎት ወስኖበታል፡፡

መስከረም 7 ቀን 1963 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ
የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ እግድ መነሳቱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ
ክልሎች በመጋዘን የሚገኘውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ በወቅቱ እንዲያደርሱ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሎች በመጋዘን የሚገኘው ሰባት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ በወቅቱ ማድረስ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ።
የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ እንደገለጹት፤ ለ2015/16 ምርት ዘመን 12 ነጥብ 87 ሚሊዮን ኩንታል በመግዛት እና የከረመውን ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ጨምሮ በምርት ዘመኑ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100618