Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
እንጀራ ከማጀት - ወደ ኢንዱስትሪ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ለሚ የእንጀራ ማዕከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተንጣለለ ሥፍራ ላይ በውስጣቸው በርካታ የእንጀራ መጋገሪያ ብሎኮችን ይዞ የተገነባ ማዕከል ነው፡፡ ብሎኮቹ እያንዳንዳቸው እስከ 250 የእንጀራ መጋገሪያ ምጣድ በውስጣቸው ይዘዋል፡፡
ይህ ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንጀራን ወደኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስገባት ብሎም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማዋን ነዋሪዎች ለመደገፍ ከባለሃብቶች በማሰባሰብ የተገነባ ነው፡፡ ማዕከሉ በአሁኑ ወቅትም ሙሉ ለሙሉ ወደስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የማዕከሉ ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100887
በቀጣዩ የመኸር ግብርና ከ508 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል
***********************
(ኢ ፕ ድ)
በአገር አቀፍ ደረጃ በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን ከ508 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የብርዕና አገዳ ሰብሎች ዴስክ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ቢረዳ እንደገለጹት፤ በፌዴራል ደረጃ በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን በክላስተርና በመደበኛ ግብርና ከሚሸፈነው 16 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከ508 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል፡፡
እንደ አቶ ፍቃዱ ገለጻ፤ በዘንድሮው የመኸር ምርት ዘመን አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100850
ኢትዮጵያ ከምስረታው ጀምሮ ለአፍሪካ ሕብረት መጠናከር የጎላ ሚና ተጫውታለች
****************************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ጀምሮ ለአፍሪካ ሕብረት መጠናከር የጎላ ሚና እንዳላት ምሁራን ተናገሩ፡፡
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶክተር ሙሉጌታ ደበበ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከስልሳ አመት በፊት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት እና ከዚያ በኋላም የአፍሪካ ህብረት እውን እንዲሆን፤ እንዲሁም ለህብረቱ ቦታ በመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቷን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በድርጅቱ ምስረታ ወቅት ቀደም ሲል ለፖሊስ አካዳሚ የተሰራውን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100851
የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በ2016 በጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ሥራ ይጀምራል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በ2016 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሙሉ ለሙሉ ወደስራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የንግድ ቀጣናው ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ረሺድ ገለጹ።
የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ረሺድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ነፃ የንግድ ቀጣናውን ሙሉ ለሙሉ ሥራ ለማስጀመር አዋጅ የማስጽደቅ እና የውጭ ገንዘብ አጠቃቀምን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100902
የግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይቱን የጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ለፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል ለአቶ ግርማ የሺጥላ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው።
ኮሚቴው በሚኖረው ቆይታ በሀገራዊ እንዲሁም በፓርቲያዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ለውይይት በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ የጋራ ግምገማ በማድረግም መላው ህዝባችንን በማሳተፍ የሚሳኩ የብልፅግና ጉዞ ትልሞች ላይ የሚመክር መሆኑን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።